Get Mystery Box with random crypto!

#ክብር ክብር ምንድር ነው? መከበር የማይፈልግ ያለ አይመስለኚም እና መከበር ትፈልጋለህ? በአከባ | ገፅ _ማህደር

#ክብር

ክብር ምንድር ነው? መከበር የማይፈልግ ያለ አይመስለኚም እና መከበር ትፈልጋለህ? በአከባቢህ በሰዎች መከበር ትፈልጋለህ? እነዚህን ጥያቄዎች እራስህን/ሺን ጠይቀህ/ሽ ታውቃለህ/ታውቂያለሽ?

ክብር የማይፈልግ ሰው የለም ሁላችንም ባለንበት ስፍራና ቦታ መከበር እንፈልጋለን ክብር አስፈላጊ እንደሆነ እናወራለን ሰው አክብር እንባባላለን ታዲያ ስለክብር ያለን አመለካከት ልክ ይመስላችዋል ክብር እንፈልጋለን ነገር ግን አፈላለጋችን ልክ አይደለም ክብርን ፈልገነዋል ግን እያገኘን አይደለም ታዲያ ክብር እንዴት ነው ሚገኘው? ትል ይሆናል ታዲያ መከበር ፈልገህ ከሆነ አንድ ነገር እወቅ:-

ክብር ፈልገህ ከሆነ መጀመሪያ እራስህን አክብር ሰው ሊያከብርህ የሚችለው አንተ እራስህን በምታከብረው ልክ ነው ሰው ሊወድህ የሚችለው አንተ እራስህን በምቶደው ልክ ነው ለራስህ ዋጋ ስጥ ትልቅ ነህ ሰው ነህ ሰው መሆን ደግሞ ትልቅነት ነው። ያለህን ካላከበርክ የሚኖርህን ነገር ማንም ሊያከብርልህ አይችልም ለራስህ ከፍ ያለ ግምት ይኑርህ ያ ግምት የሌሎችን ግምት ይቀይራል እራስህን ባከበርከው ቁጥር ሰዎች ያከብሩሀል ታዲያ ግን ለራስህ ያለህ ክብር ባዶነት ድፍረት መሆን የለበትም በእውቀት መሆን አለበት ጉራ መሆን የለበትም ለራስህ ያለህ ክብር በእውቀት መሰረት ደካማ ጎንህን እያስተካከልክ ብርቱሁን ጎንህን ደግሞ እያጠነከርክ መሆን አለበት ለራስህ ትክክለኛ እውቀት ያዝ።

#ላንተ_ክብር_እንደሚገባህ_ሁሉ_ለሌላውም_ሰው_ክብር_ይገባል

SHARE & SUPPORT



#babi




ከ Yoseph

@amazing_generation



የደስታ ቀን ተመኘንላችሁ
#babi