Get Mystery Box with random crypto!

#poem_325 (ነሱሀ አወል) እኔ እንደጠበብኩ አንተ እንደሰፋህ፣ በራህመት አቀፍከኝ በጥጋብ | NESUHA calligraphy and poems

#poem_325

(ነሱሀ አወል)


እኔ እንደጠበብኩ
አንተ እንደሰፋህ፣
በራህመት አቀፍከኝ
በጥጋብ ስገፋህ።

አለቀልኝ እንዳልኩ
ተስፋ ትጭራለህ
አንሼ እንድተልቅ፣
ምን እዝነት ይገኛል
ከራህማህ የሚልቅ።

እናም አምላኬዋ...!

ፊቱን ብቻ ለማይ
ለእንደኔ አይነቷ
እንዳተወኝ የትም፣
ያለ መምሪያ ዱላህ
አልመለከትም።

http://t.me/Nesuhaawel_poem