Get Mystery Box with random crypto!

ጥሩ እንቁላል ጣይ ዶሮ እንዴት መለየት እንችላለን!! ጥሩ እንቁላል ጣይ ዶሮ ቀጭንና ጠንካራ መስ | Negate farms ንጋት ዶሮ እርባታ

ጥሩ እንቁላል ጣይ ዶሮ እንዴት መለየት እንችላለን!!

ጥሩ እንቁላል ጣይ ዶሮ ቀጭንና ጠንካራ መስላ ትታያለች። የጀርባዋን ረጅምነትና ሰፊነት፣ የዓይኗ ትልቅነትና ብሩህነት፣ የኩክኒዋ ትልቅነትና ብሩህ ቀይ መሆን፣ የእግሯ ቀለም ከቢጫነት ወደ ደብዛዛ ቢጫ ቀለምነት፣ ኩስ መጣያዋ ሰፊና ብሩህ ቢጫ ቀለም ያለው መሆኑን፣ የፔልቪክስ አጥንቶቿ ቀጭን ልስልስና የተራራቁ መሆናቸውን መመልከትና መምረጥ ያስፈልጋል።
ጥሩ እንቁላል ጣይ ዶሮ የፔልቪክስ አጥንቶቿ ርቀት ከ3-4 ጣቶች የሚያስቀምጥ መሆን አለበት። በዚህ ዓይነት የሚመርጡ ዶሮዎች ትልልቅ እንቁላል የሚጥሉና በዓመት ከ270-300 እንቁላል ሊሰጡን የሚችሉ ናቸው። ከነዚህ ውጪ የሚገኙትን ሴት ዶሮዎች ሰብስቦ መቀለብ ትርፍ ሳይሆን ኪሳራን ያስከትላሉ።

እንቁላል ጣይ ዶሮዎች በዓመት አንድ ጊዜ ላባቸውን አራግፈው አዲስ ላባ ያወጣሉ። በዚህ ወቅት እንቁላል ከመጣል የሚቆጠቡ መሆኑን ዶሮ አርቢው ማወቅ ያስፈልጋል።

እንቁላል ጣይ ዶሮዎች በመጀመሪያው ዓመት የእንቁላል መጣያ ዘመናቸው ብዙ እንቁላል ይጥላሉ። በደንብ የተያዙ ዶሮዎች ከሆኑ በሁለተኛው አመታቸውም እንደ መጀመሪያው አመት ብዙ እንቁላል ሊጥሉ ይችላሉ። በደንብ ካልተያዙ ግን በሁለተኛው አመት ምርታቸውን ይቀንሳል።

አዋቂ አርቢዎች እንቁላል ጣይ ዶሮዎቻቸውን በየሁለት አመቱ በአዲስ እንቁላል ጣይ ዶሮዎች ይተኳቸዋል።

አንድ ዶሮ አርቢ በደንብ የተያዙ 100 እንቁላል ጣይ ዶሮዎች ቢኖሩት በቀን ከ75 እስከ 85 እንቁላል ለማግኘት እንደሚቻል ይገመታል።


በቅንነት ሼር አድርጉት

——————————————————————
Negate farms ንጋት ዶሮ እርባታ
https://t.me/Negatefarms
ለአሰተያየትዎ ፦ @Negatefarms_bot
——————————————————————