Get Mystery Box with random crypto!

የአቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረድየሏሁ ዐንሁ) ታሪክ                      ክፍል ዘጠኝ | የአረብ ገንዳ መስጂድ ወጣቶች

የአቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረድየሏሁ ዐንሁ) ታሪክ

                     ክፍል ዘጠኝ
 
  «አንቱ የአላህ መልዕክተኛ እኛ በቀጥታ የመጣነው ፈጅር ለመስገድ ነው በዚህ ሰዓት እንዴት የታመመን ልንጠይቅ እንችላለን፡፡» በማለት ዕይድ ዑመር መለሱ፡፡ አቡበክርም(ረ.ዐ) «አንቱ የአላህ መልዕክተኛ እኔ ወደ መስጅድ ለመሄድ ከቤቴ ስወጣ ትላንት ወንድሜ አብዱራህማን ቢን ዐውፍ መታመሙን አስታወስኩ፡፡ የርሱ ቤትና የእኔ ቤት በመስጅዱ መካክል ይገኝ ነበር፡፡ ለሪጅር ሶላት መንቃቱን ስላወቅኩ  አንድ አፍታ ገብቼ ጠየቅሁትና ወደዚህ ለሶላት መጣሁ» አሏቸው፡፡

    ረሱል (ሰዐ,ወ) ቀጠል አደረጉና «ዛሬ ምሽት ከናንተ ውስጥ ሶደቃ የሰጠው ማነው?» ብለው ጠየቁ፡፡ ዑመርም “በዚህ ምሽት ሶደቃ የሰጠነው ማንም ደሃ የለም” ብለው መለሱ፡፡ «አንቱ፡ የአላህ መልዕክተኛ ቢን ዓውፍን ከጠየቅሁ በኋላ ወደ መስጂድ ስገባ ድሃ አገኘሁና በእጄ የተጋገረ ዳቦ ይዤ ስለነበር ለርሱ ሰጠሁት» በማለት አቡበክር ተናገሩ፡፡

   ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ “አንተ አቡበክር ዛሬ አንተን በጀነት
አብስሬሃለሁ ይህን ሁሉ ሥራ የሠራ ሰው ጀነት ሊበሰር ይገባዋል፡፡”
ዑመርም ደንገጥ አሉና “አቡበክር ሆይ! በምንም ነገር አንተን ቀድሜህ አላውቅም" አሏቸው።

                   ከባዱ ዘመቻ

   ሰይድ ዑመር(ረ.ዐ) እንዲህ ይላሉ፡- «በተቡክ ዘመቻ ጊዜ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ወደኛ መጡና ለዘመቻው ግልጋሎት ይውል ዘንድ እንድንወድቅ (እንድንመጸውት) ቅስቀሳ እደረጉልን። ይህ ሀሳብ በጣም ተስማማኝ፡፡ የተወሰነ ገንዘብ ስለነበረኝ ዛሬ እበበክርን በመብለጥ አለብኝ ብዬ ወሰንኩ፡፡ ወደ ቤቴ ሄድኩና ካለኝ ገንዘብ ውስጥ ግማሹን ይዤ ተመለስኩና ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ፊት ዘረጋሁት፡፡ እሳቸውም «ለቤተሰቦችህ ምን ያህል
እስቀረህላቸው ብለው ጠየቁኝ። እኔም "ከገንዘቤ ግማሹን ትቼላቸዋለሁ::" አልኳቸው። አቡበክርም(ረ.ዐ) ምንም እንኳ ከዑመር ያነሰ ቢሆንም ቤታቸው ሄደው ገንዘባቸውን ሁሉ አንዲትም ሳያስቀሩ ጠራርገው በማምጣት ነብዩ(ሲ.ዐ.ወ) ፊት ዘረገፉት ነብዩም (ሰዐ,ወ) ለቤተሰቦችህ ምን ያህል አስቀረህላቸው አቡበክር? በማለት ጠየቋቸው:: አበበክርም «ለቤተሰቦቼ ከአላህና ከርሶ በስተቀር ምንም የተውኩላቸው ነገር የለም፡፡"  በማለት መልስ ሰጡ። እኔም እንዲህ አልኩኝ "አቡበክር ሆይ! ወላሂ
ከአሁን በኋላ ካንተ ገር ለመፎካከር አልሞክርም።"  ሃብት ንብረታቸውን በመሉ ለአላህ (ሱ.ወ) ዲን ሲሉ ለሶስት ጊዜያት ያህል የሰጡት ብቸኛ ጀግና አቡበክር አስ-ሲዲቅ ናቸው፡፡

   እስቲ ጥቂት ቆም ብለን ራሳችንን እንጠይቅ! ማነው እስቲ ከኛ
ውስጥ ለአላህ (ሱ.ወ) ብሎ የተቸገሩ ወገኖቹን ለመርዳት ገንዘቡን ሁሉ የሚሰጥ ሰዎች አሁንም ሞልተዋል፡፡ እኔ ራሴ በዐይኔ አንድ በጣም ደካማ ሰው የቦስኒያ ሙስሉሞችን ለመርዳት ራሱ የሚጠቀምበትን ዊልቸር ሲቸር ተመልክቻለሁ፡፡ አንዲት ሴትም ምንም ነገር ስላልነበራት ሙስሊሞችን ለመርዳት የራሷን ጌጣ ጌጦች ስትሰጥ አይቻለሁ፡፡ በዚህ ኡማ ውስጥ የአቡበክርን ዓርአያነት የሚከተል ሰው ሞልቶናል፡፡ ይህ ዓይነቱ ድንቅ ዓርአያነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንመኛለን፡፡

  አቡበክር ገንዘባቸውን ሁሉ ለአላህ (ሱ.ወ) ሲሉ ሶስት ጊዜያት
ያህል መጽውተዋል ብለናል፡፡ እነርሱም፡-
-አንዲት ሚስኪን ሴት ከባርነት ነጻ ሲያወጡ፣
- ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ወደ መዲና ሲሰደዱና
- አሁን እንዳልነው በተቡክ ዘመቻ ወቅት ናቸው፡፡

          ለአላህህ (ሱ.ወ) የነበራቸው ፍራቻና ክብር

    ከዕለታት አንድ ቀን የአስ-ሲዲቅ አገልጋይ ለአቡበክር ምግብ
ያቀርብላቸዋል፡፡ አቡበክርም ትንሽ ቀመስ ያደርጉለታል፡፡ አንድ ምግብ ሲቀርብላቸው የምግቡ አመጣጥ ከየት እንደሆነ የመጠየቅ ልምድ ነበራቸው፡፡ በዚህም መሠረት አገልጋያቸውን የምግቡን ምንጭ ይጠይቁታል፡፡ ‹‹ሙስሊም ከመሆኔ በፊት ለስዎች እጠነቁል ነበር፡፡›› በወቅቱ አንድ የጠነቆልኩለት ሰው የነበረበትን ዕዳ ኣሁን ስለከፈለኝ በዚሁ ገንዘብ ነው ይህን ምግብ የገዛሁት ይላቸዋል፡፡

   አቡበክርም በጣም ተደናግጠው «አጥፍተኸኝ ነበር›› ይሉና
ጣታቸውን ወደ ጉሮሮዋቸው ሰድደው የገባውን ለማውጣት ከራሳቸው ጋር መታገል ይጀምራሉ፡፡ ይህን የተመለከቱ ሰዎች በላዩ ላይ በብዛት ውሃ ጠጥተው ካልሆነ ሊወጣሳቸው እንደማይችል ይነግሯቸዋል። ውሃ አምጣልኝ ብለው ያዛሉ፡፡ የመጣላቸውን ውሃ በደንብ ከጠጡ በኋላ እንዲያስታውካቸው በማድረግ የቀመሱትን ጥቂት ጉርሻ ነቅለው ያወጡታል፡፡ ሁኔታውን የሚመለከቱት ሰዎች ‹‹አላህ ይዘንሎት! ትንሽ ነበርች›› ይሏቸዋል፡፡ እርሳቸውም «ወላሂ  ነፍስህ ካልወጣች በስተቀር አትወጣም ነበር ብባል እንኳ ጎልገዬ አወጣት ነበር” ይላሉ፡፡

              አስገራሚ ትህትናቸው

በመዲና ከተማ ውስጥ ባጋደለ ደሳሳ ጎጆ ውስጥ የምትኖር
አንዲት ድሃ አሮጊት ሴትዮ ነበረች፡፡ አቡበክር አስ-ሲዲቅ(ረ.ዐ) በየሳምንቱ ወደ ቤቷ እየሄዱ ቤቱን አጽድተውላት ይመለሱ ነበር፡፡

     ከዕለታት አንድ ቀን ሰይድ ዑመር (ረ.ዐ) የባልቴቷን ደካማነት ይሰሙና ሊጠይቁዋት ቢሄዱ ቤቷ ጥርት ባለ ንጽህና መያዙን ያዩና እንዲህ አድርጎ የሚያጸዳላት ማን እንደሆነ ይጠይቋቸዋል፡፡ ሴትየዋም ማንነቱን የማያውቁት አንድ ሰው በየሳምንቱ እየመጣ እንደሚያጸዳላቸው ይነግሯቸዋል፡፡

    ሰይድ ዑመርም የዚህን ደግ ሰው ማንነት ማወቅ ይኖርብኛል
በማለት በሳምንቱ ተደብቀው መጠባበቅ ይጀምራሉ፡፡ ዑመር(ረ.ዐ) ሁኔታውን እንዲህ ይተርካሉ፡፡ «አቡበክር(ረ.ዐ) መጥተው ቤቱን አንኳኩ፡፡ በሩ እንደተከፈተላቸው አሮጊቷን ወደ ውጪ ደግፈው አወጧቸውና ቤቱን ካጸዱ በኋላ ሴትየዋን ወደ ነበሩበት መልስው ወዲያው በመውጣት ወደ መጡበት አቅጣጫ ይሄዳሉ፡፡››

  ኧረ ለመሆኑ ! እስኪ ማነው ከእኛ ውስጥ ሃቃቸው የማያልቀውን
እናት አባቱን እንኳ እንዲህ አድርጎ የሚያገለግለውና የሚያግዘው?
ራሳችንን መጠየቅ አለብን፡፡

       ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ስስል ሲዲቅ የነበራቸው ውዴታ

  አንድ ቀን ሶሀባዎች በተሰበሰቡበት ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ወደ መስጂድ ገቡና ‹‹አቡበክርስ የታለ?›› ሲሉ ጠየቁ፡፡ አቡበክር ቆም አሉ "ና አጠገቤ ሁን” አሏቸው፡፡ “ዑመርስ የት አለ” ሲሉ አስከተሉ፡፡ እርሳቸውም ቆም ሲሉ ‹‹ና አጠገቤ ሁን›› አሉና የሁለቱንም ሶሀቦች እጅ ይዘው ከፍ
በማድረግ እንዲህ አሉ “በዕለተ ትንሳኤ ልክ እንደዚህ ነው
የምንቀሰቀሰው፡፡”

   ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ከሰው ሁሉ ማንን ይበልጥ እንደሚወዱ ሲጠየቁ ‹‹ዓኢሻን› አሉ፡፡ ከወንዶችስ ሲባሉ ‹‹አባቷን አቡበክርን›› አሉና እንዲህአሉ «አቡበክር ሆይ! በዋሻው ውስጥ ጓደኛዬ እንደነበርከው ሁሉ የጀነትን መጠጥ (ሐውድ) ሳከፋፍልም የቅርብ ጓደኛዬ ትሆናለህ፡፡»

  ከዕለታት አንድ ቀን ሰይድ ዑመር በአንዲት ንግግር አቡበክርን ያኮርፏቸውና ጥለዋቸው ይሄዳሉ፡፡ አቡበክርም(ረ.ዐ) ከኋላ እየተከተሉ "ዑመር እባክህ አትቆጣ ይቅር በለኝ” ቢሏቸው ዑመር(ረ.ዐ) ዝም ብለዋቸው ሄዱ፡፡

  ሰይድ አቡበክር(ረ.ዐ) ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሄዱና እንዲህ አሏቸው «ዑመርን ይቅርታ አድርግልኝ፣ ታረቀኝ ብለው እንቢ አለኝ ከዚያም ዑመር ትንሽ ቆይተው...
http://t.me//@arebgendamesjid
--------ኢንሻአላህ ይቀጥላል.......

የአረብገንዳ መስጂድ ወጣቶች የመረጃ ዘርፍ