Get Mystery Box with random crypto!

የቤት ሰራተኛዋ ሁለት ህፃናት ልጆች ላይ አሰቃቂ የግድያ ወንጀል ፈፀመች !! በአዲስ አበባ ለሚ | Natinael Mekonnen

የቤት ሰራተኛዋ ሁለት ህፃናት ልጆች ላይ አሰቃቂ የግድያ ወንጀል ፈፀመች !!

በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ቦሌ አራብሳ ኮንዶሚንየም ብሎክ 51 ላይ ሁለት ህፃናት በአንዲት በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ጃጉ ጆርናል ለማወቅ ችሏል፡፡

እድሜያቸው ያልተገለጸው ህፃናቱ ወንድምና እህት ሲሆኑ ሰራተኛዋ አንዷን በስለት አርዳ ፤ ወንድሟን ደግሞ በማነቅ የሁለቱም ህፃናት ህይወታቸው አጥፍታለች ፡፡

ወንጀሉን የፈጸመችው ግለሰቧ እጇን ለፖሊስ እንደሰጠች የተነገረ ሲሆን እስከ አሁን የአዲስ አበባ ፖሊስ በጉዳዩ ዙሪያ ያለው ነገር ባይኖርም የአካቢው ነዋሪዎች ወንጀሌ ወደተፈጸመበት ስፍራ ማቅናታቸውን ከስፍራው ያሉ የአይን እማኞች ለዳጉ ጆርናል ገልፀዋል፡፡

በቀጣይ ዳጉ ጆርናል ዝርዝር ጉዳዩን በቅርበት እየተከታለ መረጃውን እንደሚያደርስ ለመግለፅ እንወዳለን፡፡