Get Mystery Box with random crypto!

ዘወትር የኦሮሞ ጥያቄ ይመለስ በማለት የሚጮሁ ፣ የኦሮሞ ጥያቄን ለመመለስ ትንሽ ሙከራ ሲጀመር ሙከ | freedom

ዘወትር የኦሮሞ ጥያቄ ይመለስ በማለት የሚጮሁ ፣ የኦሮሞ ጥያቄን ለመመለስ ትንሽ ሙከራ ሲጀመር ሙከራውን ማናናቅ ከፍ ሲል ደግሞ ጥያቄያችን ይህ አይደለም ብሎ መሸምጠጥ ፣ እንዲሁም እኔ የምፈልገው ሰው ብቻ ነው የኦሮሞ ጥያቄን መመለስ ያለበት ሌላ ሰው እንዲመልሰው አልፈልግም የማለት አባዜ ።

ፅሁፉ ከታች ነው የሚጀምረው ከላይ የፃፍኩት ርዕሱ ብቻ ነው። ምናልባት በርዕስ ታሪክ የመጀመሪያ ረጅሙ ርዕስ ሊሆን ይችላል ግን ከዚህ ባጠረ ቃላት ልገልፀው ስለማልችል ነው። ሀቅ ሀቋን ከታች አፈርጠዋለሁ ብቻ ጨርሳችሁ አንብቡት። የደበራችሁ ደግሞ ገፁን እየለቀቃችሁ የመውጣት መብታችሁ ይጠበቃል።
.................................................

በመጀመሪያ የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄዎችን ልዘርዝር

1ኛ:- የፊንፊኔ የባለቤትነት ጥያቄ
2ኛ:- አፋን ኦሮሞ የፌደራል ቋንቋ የማድረግ ጥያቄ።
3ኛ:- በሁሉም የስልጣን እርከን ውስጥ ኦሮሞ በብዛቱ ልክ እንዲወከል የማድረግ ጥያቄ።
4ኛ:- ከቀዬው ሳይገፋ ፣ ባመለካከቱ ሳይሳደድ ፣ ሳይታሰር እና ሳይገደል መኖር
5ኛ:- ኦሮሞ የራሱን እድል በራሱ የመወሰን መብቱን መጠቀም ናቸው።

ከነዚህ ጥያቄዎች መሀል አንደኛው ጥያቄ የፊንፊኔ የባለቤትነት ጥያቄ ነው። ፊንፊኔ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ሆነች ሊባል የሚችለው የኦሮሚያ ተቋማቶች መአከላቸውን ፊንፊኔ ውስጥ ሲያደርጉ እና ሲሰሩ ብቻ ነው።

ዛሬ የኦሮሚያ ቤተመንግስት ፊንፊኔ ሲመጣ " የኛ ጥያቄ የኦፒዲዮ ቤተመንግስት ፊንፊኔ ይምጣልን አይደለም" የሚሉ ብዙ የኦሮሞ ልጆችን እየታዘብኩ ነው። ብልፅግና እኮ እስከተወሰነ ጊዜ ነው ስልጣን ላይ የሚቆየው ከዛ እሱ ሲሄድ ሌላው ነው የሚተካበት ዋናው ተቋማቶቹ ወደሚገባቸው ቦታ መመለሳቸው ነው የሚፈለገው።

የኦሮሚያ ቤተመንግስት ፊንፊኔ ከሆነ በስሩ ያሉት የኦሮሚያ ፖሊስ ፣ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ፣  እና ሌሎች የኦሮሚያ ክልል ተቋማት ወደ ፊንፊኔ ይመለሳሉ ልክ በ97 እንደነበረው። የኦሮሚያ ክልል ተቋማት ደግሞ የሚያገለገሉት በአፋን ኦሮሞ ነው። ስለዚህ የቋንቋው ጥያቄም ከዚሁ ጋር ተያይዞ ይመለሳል ማለት ነው።

ምስጋና ለኦሮሞ ህዝብ ላለፉት 5 አመታት በነፍጠኛ አማራዎች ቁጥጥር ስር ሆኖ ሲጋለብ የነበረውን የብልፅግና መንግስት በእልህ አስጨራሽ የውጭ እና የውስጥ ትግል አማራን ከብልፅግና በትክክል መለያየት ተችሏል። አሁን ላይ ብልፅግና ወደ ትክልልለኛው ሀዲድ ገብቷል። በተቻለ መጠን የሚሰሩ መልካም ነገሮችን ዝም ብለን በጭፍን አንቃወም። አሁን ከኦሮሞ የሚጠበቀው ዳግም አማራ ብልፅግናን ወደራሱ እንዳይስበው ማድረግ ፣ መልካም ነገሮች ሲሰሩ ማበረታታት ፣ መጥፎ ነገር ሲሰራ መቃወም ፣ በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት እና በብልፅግና መካከል የሚደረገው ድርድር ፍሬ እንዲያፈራ አሉባልታ ወሬዎችን እና ድርድሩን የሚያፈርስ ማንኛውንም ወሬ አለማዳመጥ። በተቻለ መጠን የኦሮሞ አንድነት መጠናከር ጉዳይ ላይ በትኩረት መስራት ( ጅማ ፣ ወለጋ፣ አርሲ ባሌ ምናምን እያሉ ለሚከፋፍሉ ጆሮ አለመስጠት) ።

በዋናነት ደግሞ ዘወትር ጥያቄያችን ይመለስ እያሉ የሚጮሁ ግን ጥያቄያቸው ሊመለስ መንገዱ ሲጀመር " ሴራ ነው ፣ ሊያታልለን ነው" እያሉ ከሚጃጃሉ ቆሞቀሮች ራሳችሁን አርቁ። ጥያቄያችን በብልፅግና ሊመለስ አይችልም ብላችሁ ካመናችሁ ለምን ዘወትር "ጥያቄያችን ይመለስ" ብላችሁ ትጠይቃላችሁ ? ጥያቄ እኮ የሚጠየቀው ለመላሽ ነው እኛው እንመልሰዋለን ካላችሁ ጥያቄ አትጠይቁ።

የኛ አቋም ግልፅ ነው ኦሮሞ ከሌሎች ፌደራሊስት ብሄርብሄረሰቦች ጋር ሆኖ በዱር በገደሉ ተዋድቆ ታግሎ የሀይል ሚዛኑን በማጋደል ብልፅግና ከ አንድ አመት በፊት ከነበረበት የአማራ ግርድና ሊላቀቅ ችሏል። አሁን ብልፅግና ወደ አማራ ፈረስነቱ እንዳይመለስ ኦሮሞ በርትቶ ጥንካሬውን ማጎልበት ብቸኛ አማራጩ ነው። ለኦሮሞ ያለው አማራጭ አንድነት ብቻ ነው ስንከፋፈል የማንም መጫወቻ ነው የምንሆነው።

ብልፅግና ማለት የብሄር ፓርቲ አይደለም የሀይል ሚዛኑ ወዳጋደለበት የሚያዘነብል መሳሪያ ነው። ላለፉት አመታት የሀይል ሚዛኑ ወደ አማራ አዘንብሎ አማራ ብልፅግናን እንደ ጦር መሳሪያ ሲጠቀምበት ኖሯል አሁን የሀይል ሚዛኑ ያለው በብሄር ብሄረሰቦች እጅ ነው ብልፅግናም ወደዚሁ ካምፕ አጋድሏል። ጥያቄዎቻችንን አንድ በአንድ ለመመለስ ይሄን ልንጠቀምበት ይገባል።

እዚህ ድረስ ሳትደክሙ አንብባችሁ ከጨረሳችሁ እና መልዕክቱን ከወደዳችሁት ሼር አድርጉት። ቅሬታ ካላችሁ ኮመንት አድርጉ። ከተናደዳችሁ ውጡ
@my_oromia