Get Mystery Box with random crypto!

መንታ መንገድ ክፍል ስድስት (ፉአድ ሙና) . . አዲስ አበባ በመጣሁ በመጀመሪያዉ ቀን ተጣልቼ ጣቢ | 🦋᭄᭓ ͜͡ Ķhäĺì Đ ͜͡࿐𝄟᭄͢ 𝐈𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐥𝐨𝐯𝐞᭄ 𝐂𝐨𝐮𝐩𝐥𝐞𝐬 𝄟᭄͢ 🦋🦋™™

መንታ መንገድ
ክፍል ስድስት
(ፉአድ ሙና)
.
.
አዲስ አበባ በመጣሁ በመጀመሪያዉ ቀን ተጣልቼ ጣቢያ መግባቴ ለራሴም ገረመኝ። ጣቢያ ዉስጥ ትንሽ እንደቆየሁ አባዬ ሲከንፍ ደረሰ። ለመርማሪዉ የተፈጠረዉን ነገር በሙሉ ሳስረዳዉ ወደ ልጁ እየዞረ "እኔ ብሆን አንገትህን ነበር የምቆርጥልህ!" አለዉ። ሳቄ መጣ። መርማሪዉ ወደ ክስ ሳይሄድ ነገሩን በእርቅ እና በምክር ለመፍታት ያሰበ ይመስላል። መርማሪዉ መርየምን ከዚህ በኋላ በተመሳሳይ ጉዳይ ቢያገኛት እንደማይለቃት አስፈራርቷት ሸኘን። ልጁን ትንሽ እጃቸዉን አፍታተዉበት የሚለቁት ይመስለኛል። ያዉ የኛ ሀገር ፖሊሶች አመል የታወቀ ነዉ። በስህተት መርማሪ ቢሮ የገባ ፖሊስ ሳይቀር ነዉ እንደ ቡናቁርስ አገላብጦህ የሚወጣዉ።
.
ቤት እንደገባን መርየም ቀና ብላ ልታየን አፈረች። ልቧ እንዳይሰበር ቀስ ብዬ ወደ መኝታ ክፍል ወስጄ ለረዥም ሰዓት መከርኳት። እሷም ይቅርታ ጠየቀችኝ። ለሻከረዉ ግንኙነታችን መሻሻል መልካም ዕድል የተፈጠረ መሰለኝ። ከችግር ጋር ምቾት አለ። ከሰዉ ጋር መደባደቤ ፣ እህቴ በባዳ ወንድ ስትነካ ማየቴ ቢያቆስለኝም በሱ ምክንያት ከእህቴ ጋር ያለኝ ቅርርብ መሻሻሉ አስደሰተኝ። ፈጣሪ መልካም ነገርን የትኛዉ ብልቃጥ ዉስጥ እንደሚያስቀምጥ አይታወቅም። ብዙ ጊዜ ደሞ ጣፋጭ ነገሮች በእሾህ የተከበቡ ናቸዉ። አባዬን እንዳይቆጣት እና ሁሉንም እኔ እንደማስተካክለዉ ነግሬ የመርየምን ጭንቀት አቀለልኩላት። ከእህት ጋር እንደወንድም መወያየት መቻልን የመሰለ ምን ደስታ አለ? ምንም!!
.
ከባህርዳር ከተመለስኩ ሁለት ሳምንት ሞላኝ። ራሄል ሳትደዉል አድራ አታዉቅም። የኔ ቀዉስ!
ከሀያት ጋር አንዴ በአካል ተገናኝተናል። ለቤተሰቦቿ ተናግራ ኺጥባዉን እንድንጀምረዉ ጠይቃኝ ነበር። እኔ ግን ትንሽ እንድናርፍ ስለጠየቅኳት አስቤበት ስዘጋጅ እንድነግራት ነግራኝ ተለያየን። ሰሞኑን ከአባቴ ጋር የስራ ቦታዉ ነዉ የምዉለዉ። የአባቴን ስራ ማስተዳደር እንድችል አባዬ እያለማመደኝ ነዉ።
የአባዬ ቢሮ ተቀምጬ ሀዩ ደወለች። አነሳሁትና "ወዬ ሀዩና!" አልኩ።
"ባክህ ደስ የማይል ዜና አለ!" አለችኝ ድምጿ ዉስጥ ድብርት አለ።
"ምነዉ ሀዩ ችግር አለ?" አልኩ ስለደበራት እየደበረኝ። ሀያት ስትስቅ ነዉ የምታምረዉ ፣ ፍልቅልቅ ስትል። በሳቋ ዉስጥ የሚንቆረቆር የሆነ ለየት ያለ ዜማ አለ። ስትስቅ ሌላዉንም እንዲስቅ የሚያስገድድ ልዩ ሀይል አላት።
"አኩዬ ብራዘር ካልዘየራችሁኝ ብሎ ቲኬት ልኳል። ክረምቱን ስዊዘርላንድ ላሳልፍ ነዉ።" አለችኝ። ድብርቷ በክረምት እንድናደርገዉ ያሰበችዉ መተጫጨት ስለከሸፈ መሆኑ ገባኝ። እኔ ግን ትንሽ እረፍት ተሰማኝ።
"ወይኔ ሀዩዬ ልትናፍቂን ነዋ!" አልኩ ክረምቱን ሙሉ እንደማናገኛት እያሰብኩ
"አዎ በአላህ አክረሜ! በጣም ነዉ የምትናፍቀኝ እሺ ሁቢ!" አለች ድምጿን ሳግ እያፈነዉ! ሁቢ ማለት በአረብኛ ዉዴ ማለት ነዉ። ሁሌም ሀዩ አማርኛዉን ከመጠቀም ይልቅ አረብኛዉን ትመርጣለች።
"ሀዩዬ ስታለቅሺ አያምርብሽም! አይዞን ሁለት ወር ቅርብ ናት። ደሞ በስልክ እንገናኛለን።"አልኩ ላፅናናት በማሰብ
"እሺ አኩዬ በስልክ ግን እንዳትጠፉብኝ። ለማንኛዉም ከነገ ወዲያ ነዉ የምበረዉ።" አለችኝ የመለየት ስጋት በወገረዉ ድምፅ። ስልኩን እንደዘጋሁት ሀዩን አሰብኳት። የሀይማኖት ዕዉቀቷ ገራሚ ነዉ። ሁሌም የምትለብሳቸዉ ሰፋፊ ዉብ ቀሚሶች ፣ ቀይነቷን የሚያንቦገቡጉት ሁሌም የምትለብሳቸዉ ጥቁር ሂጃቦች በሷዉ ተለብሰዉ በአይኔ ላይ ዉል አሉ። ሳቋ አይኔን ሞላዉ። ስነ ስርዓቷ ትዝ አለኝ። ስታኮርፍ ሳልኳት በጣም ደስ ትላለች። ቆይ ምንድነዉ?! ሳትሄድ ልትናፍቀኝ ነዉ እንዴ? "ሄይ አኩ ተረጋጋ" አልኩት ለራሴ።
.
የሀያት ስዊዘርላንድ መሄድ ትንሽ ዉጥረቴን አረገበልኝ። በርግጥ ናፍቆቷ ሊያሳብደኝ ምንም አልቀረዉም። በስልክ ባንገናኝ ኖሮ ምን እንደምሆን እኔንጃ! የሰዉን ልክ የምታዉቀዉ ከአጠገብህ ሲርቅ ነዉ። ሀጅራም ንፍቅ ብላኛለች። የኮምቦልቻዋ ጨዋ! ርጋታዋ በፍፁም ከአይኔ አይጠፋም። ከራሄል ጋር እሁድ እሁድ እንገናኛለን። ከራሄል ጋር ስገናኝ ልቤ ሀሴት ታደርጋለች። ከእሁድ ዉጪም ትርፍ ጊዜ ሲኖረኝ አገኛታለሁ። የጥበብ ጥማቴንም የሰዉ ረሀቤንም በአንዴ ስለምታስታግስልኝ ደስ ይለኛል። ከእሁድ ዉጪ ያለዉን ሌላዉን ቀን ከአባቴ ጋር በስራ ነዉ የማሳልፈዉ። ራሄል "እኔ አይንህን ካየሁ ይበቃኛል፤ እንዴት የኔ እንደማደርግህ እኔ አዉቃለሁ!" ትላለች ሁሌም ስንገናኝ።
.
ወራቱ እንደ አንድ ቀን እየተጠቀለሉ ክረምቱ ተጠናቆ አዲስ አመት ተበሰረ። "ሄይ አኩዬ የት ነህ?" አለችኝ ሀያት ደወለችና
"ስዊዘርላንድ ሱፐርማርኬቱ ጋር!" አልኩ እየሳቅኩ መቸስ ስዊዘርላንድ ሱፐር ማርኬት አይጠፋም በሚል ግምት
"አኩዬ አትቀልድ በአላህ ላገኝህ እፈልጋለሁ ናፍቀኸኛል።" አለችኝ እየተነጫነጨች
ስልኬን ከጆሮዬ ላይ አንስቼ ቁጥሩን አየሁት። የኢትዮጵያ ስልኳ ነዉ። የሆነ ደስታ ዉርር አደረገኝ።
"ሀዩዬ የፈለግሽበት ልምጣ በአላህ የት ነሽ?" አልኩ ድምጼ ዉስጥ ናፍቆት አለ።
"ቤት ነኝ። የት እንገናኝ?" አለች ሀዩ!
ከሰፈራችን አማካይ ላይ ያለ አንድ ካፌ ተቀጣጠርን። ሀዩዬ የኔ ቀዉስ ከሁለት ወራት ናፍቆት በኋላ ላገኛት ነዉ!
.
ሀዩ ለራሄልም ደዉላላት ስለነበር ሶስታችንም አብረን ተገናኝተን ደስ የሚል ጊዜ አሳለፍን። አብረን ሆነንም ሀጅራ ጋር ደዉለን አወራናት። ሀጁ ናፍቆታችን ሊያሳብዳት ደርሷል። ለነገሩ ከአስር ቀናት በኋላ ወደ ግቢ ተጠርተናል።
.
ወደ ግቢ ተመልሰን የአመቱ ትምህርት ተጀመረ። በነገራችን ላይ ዉጤትም ተቀብለናል። ሀያት የክፍላችን ሰቃይ ሆናለች። አራት ነጥብ ነዉ በሁለቱም ሴሚስተር ያስመዘገበችዉ። እኔና ራሄል ሶስት ነጥብ ዘጠኝ ፣ሀጁ ደግሞ ሶስት ነጥብ ስምንት አስመዝግበናል። የክፍሉ ትልቁ ዉጤት በአራታችን መያዙ በጣም አስደስቶኛል።
ጠዋት ላይ ራሄል ክፍል ዉስጥ እየተማርን "አንተን የኔ ለማድረግ ምን ያህል መስዋዕትነት የምከፍል ይመስልሀል?" ብላ በወረቀት ፅፋ ሰጠችኝ። ወረቀቱ ላይ ልክ እንደሷ የምታምር ሴት ስዕል ስላበታለች! ሀይማኖታችን ቢመሳሰል ኖሮ እሷን ለማግባት አይኔን አላሽም ነበር። እብድ ሴት እወዳለሁ። ግልፅነቷ በጣም ደስ ይለኛል።
የሰጠችኝ ወረቀት ላይ "አንዳንዴ ሰዉ ዝም የሚለዉ ማዉራት ስላልፈለገ ሳይሆን ጊዜዉ ስላልሆነ ነዉ።" ብዬ ፅፌ መለስኩላት።
.
ከክፍል እንደወጣን ምሳ ለመብላት ወደተለመደዉ ቤት ሄድን። ሀያት ምግቡን አዛ እጇን ታጥባ ተቀመጠች። ምግቡ ሲደርስ እኔና ራሄል እጃችንን ለመታጠብ ተነሳን! ሀዩ አንድ ወረቀት ከጠረጴዛዉ ላይ አንስታ ማንበብ ጀመረች። እኔና ሪቾ ክፍል ዉስጥ የተፃፃፍንበት ወረቀት ነበር። ሀያት እንባዋ ዱብ ዱብ አለ። እኔናራሄል ታጥበን ስንመለስ ሀያት ከመቀጫዋ ተፈናጥራ ተነሳች።
"ይሄ ነበር እስካሁን እንዳትወስን ያደረገህ?" አለች ወረቀቱን ፊቴ ላይ እየወረወረች! እንባዋ መንታ መንታ እየሆነ መፍሰስ ጀመረ!
ራሄል ግራ ተጋብታ ዝም ብላ ታየናለች።
"መምረጡ ነበር ወይ ያስቸገረህ?" አለች ሀያት ቁጣዋ እየተቀጣጠለ!
ከዚህ በላይ አብሬያት መቆሙ መልካምነቱ ስላልታየኝ ንዴቷ እስኪበርድ ከአጠገቧ መራቅ ፈለግኩ። ሁለቱንም ባሉበት ትቼ ወደ ዶርም ሄድኩ።
.
ወደ ማታ ሀጅራን ለብቻዋ ጠርቼ አገኘኋት።
"ተቃቅፈዉ እየተላቀሱልህ ነዉ!" አለችኝ ሀጅራ እየሳቀች! ጥቁርሰማያዊ ሂጃብ ለብሳለች።
በጣም ግራ ገብቶኛል በዚህ ሰበብ እንዳላጣቸዉ ፈርቼያለሁ "ሀጁ ፕሊስ ሁለቱንም የሚያስማማ መንገድ ፈልጊ