Get Mystery Box with random crypto!

ዱዓህን አላህ እንዲቀበልህ ትሻለህ ታላላቅ ዑለማዎች አላህን ከመጠየቅ ይልቅ አላህን ማስታወስን | Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

ዱዓህን አላህ እንዲቀበልህ ትሻለህ

ታላላቅ ዑለማዎች አላህን ከመጠየቅ ይልቅ አላህን ማስታወስን ያስበልጣሉ።

ለምን መሰላችሁ?
አላህን ካስታወስከው እንደት ይረሳሃል? «አስታውሱኝ፣ አስታውሳችኋለሁ!» ብሎን የለ!
ስለዚህ አንተ ካስታወስከው እርሱ አይረሳህምና፤ የሚያስፈልግህንና የሚጠቅምህን ነገር ካንተ በላይ ላንተ እርሱ ያውቃልና አንተ ባትጠይቀውም እርሱ ስለሚያውቅ ይሰጥሃል። አስታዋሹ ከሆንክ እንኳን ጠይቀኸው ባትጠይቀውም የልብህን፣ የውስጥህን ያውቃል።
‏( من أسباب استجابة الدعاء )

جاءت أم سُليم إلى النبي ﷺ فقالت:
ኡሙ ሱለይም ወደ ነቢያችን ﷺ ዘንድ መጣችና፤

يا رسول الله عَلِّمْنِي كَلِمَاتٍ أَدْعُو بِهِنَّ،
«አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! አላህን የምለምንበትን ቃካት አስተምሩኝ?» አለቻቸው፤
قال ﷺ:
"تُسبحين الله عَشْرًا، وتحمدينه عَشْرًا وَتُكَبِّرِينَهُ عَشْرًا، ثُمَّ أسالي حاجتك فَإِنَّهُ يَقُولُ:
قَدْ فَعَلْتُ، قَدْ فَعَلْتُ"
አላህን 10 ጊዜ ታጠሪያለሽ (ሱብሐነልሏህ)፣ 10 ጊዜ ታመሰግኒዋለሽ (አልሐምዱ ሊላህ)፣ 10 ጊዜ ታልቂዋለሽ (አላሁ አክበር)፣ ከዚያም ጉዳይሽን ጠይቂው። እርሱም «በርግጥ ፈጽሚያለሁ፣ በርግጥ ፈጽሚያለሁ!» ይላል።
- أخرجه الترمذي .

||
t.me/MuradTadesse