ላፕቶፓችን ላይ ያለውን ኢንተርኔት እንዴት ያለምንም ሶፍት ዌር በሞባይላችን መጠቀም እንችላለን? 1. cmdን በአንድሜኒስትሬተር ይክፈቱት (right click በማድረግ run as administrator የሚለውን መጫን) 2. ላፕቶፓችን ኔትዎርክ ሼር ለማድረግ ብቁ መሆኑን ለማረጋገጥ: netsh wlan show drivers የሚለውን ጽፎ ከሚመጣልን ዝርዝር ውስጥ Hosted network supported :Yes ይህ ከመጣ ላፕቶፓችን ይችላል ማለት ነው 3. በመቀጠል ይህንን ኮማንድ ማስገባት: netsh wlan set hostednetwork mode=allow ssid=Hotspotname key=password ማሳሰቢያ: SSID የሚለውን በፈለግነው ስም መቀየር እንችላለን: KEY የሚለው የዋይ ፋይ ፓስዎርዳችን ስለሆነ የምንፈልገውን መስጠት እንችላለን 4. በመቀጠል የኔት ዎርክ አዳፕተራችንን በመክፈት እና እሱላይ right click በማድረግ : Allow other network users to connect through this computers internet connection የሚለውን እንመርጥያ ከስር ካለው ሊስት ውስጥ የፈጠርነውን የዋየርለስ ኔትዎርክ እንመርጥለታለን::ከዛም OK በለን እንወጣለን 5. በመጭረሻ ወደ CMD ተመልሰን: ለማስጀመር netsh wlan start hostednetwork የሚለውን ኮማንድ እናስገባለን ለማቆም netsh wlan stop hostednetwork የሚለውን እናስገባለን 6. አሁን ሞባይላችንን wifi ከፍትን SSID ላይ ያስገባነውን የኔትዎርክ ስም መርጠን ለሚለው KEY ላይ ያስገባነውን በመስጠት መጠቀም መጀመር እንችላለን። 8.0K viewsedited 05:41