Get Mystery Box with random crypto!

ሚስት ባሏ መታጠቢያ ቤት ሲገባ ጠብቃ የባሏን ሞባይል መበርበር ስትጀምር እነዚህን ስሞች አገኘች፣ | ሙድ እንያዝ በእኛ

ሚስት ባሏ መታጠቢያ ቤት ሲገባ ጠብቃ የባሏን ሞባይል መበርበር ስትጀምር እነዚህን ስሞች አገኘች፣
1. Super Woman
2. My Love
3. Woman of my Dream
4. princess
5. Second Mom
በጣም ተናደደችና የመጀመሪያውን ስትደውል የባሏ እናት አነሱ፣ ሁለተኛውን ስትደውል የባሏ ታላቅ እህት አነሳች፣ ሶስተኛውን ስትደውል የተይዟል ምልክት አሳያትና ቀጥሩን ስታጣራ የራሷ መሆኑን አረጋገጠች፣ አራተኛውን ስትደውል የሴት ልጇ ቁጥር ሆነ፣ አምስተኛውን ስትደውል የራሷ እናት ቁጥር ሆነ።
#ባሏ_ከመታጠቢያ_ቤት ሲወጣ ሞባይሉን ስትጎረጉር በመድረሱ "ምን ፈልገሽ ነው?" ሲላት
"ስለተጠራጠርኩህ ይቅርታ አድርግልኝ። 5 ስልኮች ላይ ደውዬ ታማኝነትህን አረጋግጫለሁ" ብላ የደስ ደስ 5000ብር ሰጠችው። ባልየው ብሩን ተቀብሎ "Abebe Mechanic" በሚል ስም ለተመዘገበችው ውሽማው ሥጦታ ገዝቶላት ሄደ