Get Mystery Box with random crypto!

እመሰክራለሁ! ።።። ተዕለሙ ያ ረቢ፣ማካነ ወየኩን ወለው ማላ የኩን፣ከይፈ ካነ የኩን ልዕልናህ ዘ | በርዘንጅ Media

እመሰክራለሁ!
።።።
ተዕለሙ ያ ረቢ፣ማካነ ወየኩን
ወለው ማላ የኩን፣ከይፈ ካነ የኩን

ልዕልናህ ዘውታሪ፣ልቅናህ ዘላለም
አንተን ተመክቶ፣የከሰረ የለም

ዓሊሙል አስራሪ፣ሳሚዑል አስዋቲ
ሙሚቱል አህያኢ፣ባዒሱል አምዋቲ

የጠሩ የፀዱ፣አስማኡም ሲፈቱ
ዋጂበል ዉጁዱ፣አይነካህ ጥፋቱ

ዋጂብ ሳይኖርብህ፣ከረምህ ይፈሳል
ዘመን አያልፍብህ የት? እንዴት? አትባል

በኡስታዝ ሰዒድ አህመድ ብዕር