Get Mystery Box with random crypto!

ከመረጃ ይዳኘን ቁ2 የኢብኑ ተይሚያህ ንግግር የቀጠለ 9:አንድ ሰው ሃጀተል ኢስላም (የሃጅግዴታ) | ሙዓዝ ሀቢብ || Muaz Habib

ከመረጃ ይዳኘን ቁ2 የኢብኑ ተይሚያህ ንግግር የቀጠለ
9:አንድ ሰው ሃጀተል ኢስላም (የሃጅግዴታ) ያለበት ሆኖ የሃጁን ግዴታ ሳይወጣ ከሞተ እና የሱ ቅርብ ሰው (ወሊዩ) ሃጅ ካደረገለት ከሞተው ሰው የሃጁ ግዴታ ይወድቅለታ, ይህ ማለት አንድ ሰው ሌላ ሰው ለሱ ነይቶ በሚሰራለት ስራ እንደሚጠቀም በግልፅ ያስቀምጣል. በዚህ ጉዳይ በግልፅ የመጣውም ሐዲስ ይታወቃል.
10: አንድ ሰው ብቻውን እየሰገደ ነቢዩ(ሰ.አ.ወ)አይተዉት እንዲህ አሉ :እስኪ ማን ነው ለዚህ ሰውዬ የሚሰደቀው (ሰደቃ የሚሰጠው)አሉ ይህ ማለት የሰደቃው አሰጣጥ መንገድ ከሱ ጋር ሁለት ሆኖ በመስገድ ሰዋበል ጀማአ ያስገኝለታል ይህም በሱ ላይ መሰደቅ ይሆናል, ምክንያቱም እሱ ከሱ ጋር ሆኖ ባይሰድግ ኖሮ ሰዋበል ጀማአ አያገባኝም ነበር, ይህም በሌላ ሰው ስራ መጠቀም ማለት ነው ጉዳዩም ግልፅ ነው.
11:አንድ ሰው እዳ ኖሮበት ሌላ ሰው ከከፈለለት ከእዳው ይጠራል, ይህም በሌላ ሰው ስራ መጠቀም ለመሆኑ ግልፅ ነው.
12:አንድ ሰው የሰው ሀቅ እና በደል እያለበት ከሞተ እና ባለ ሀቆች እንዲሁም ተበዳዮች አፉ ብለዉት ይቅር ካሉት ከወንጀሉ ይጠራል, ይህም በሌላ ሰው ስራ መጠቀም ማለት ነው.
13:አንድ ሰው ጥሩ ጎረቤት ካለው በዛ ጎረቤቱ በህይወትም ሆነ ከሞተ ቡኃላም እንደሚጠቀም ከኡለሞች በተለያዩ መንገዶች ተዘግቧል, ይህም በሌላ ሰው ስራ መጠቀም እንደሆነ ግልፅ ነው.
14:አንድ ሰው የተወሰኑ ሰዎች ቁጭ ብለው አላህን እያወሱ መጥቶ ቢቀላቀላቸው በነሱ ምክንያት ይማራል, በሃሳቡን ከነሱ ጋር ባይሆንም እነሱ ለተቀመጡለታ አላማ ባይቀመጥ እንኳ, ለሌላ ጉዳይ በመጣበት ጉዳይ ቢቀመጥም, እነሱ ነይተው በተቀመጡበት እሱ አብሯቸው ተጠቀመ, ይህም በሌላ ሰው ስራ መጠቀም መሆኑ ግልፅ ነው.
15:አላህ በቁርአን ውስጥ እንዲህ ይላል,
(وما كان الله ليعذبهم وأنت فيهم)
እርሶ በውስጣ ቸው እስካላችሁ ድረስ አላህ አይቀጣቸውም ማለቱ,
(ولولا دفع الله الناس بعضهم ببعض)
ይህ ማለት አላህ በከፊል ሰዎች ጥሩ ስራ እና እና በረካ ከከፊል ወንጀለኞች ቅጣቱን ይመልሳል, ይህም በሌላ ሰው ስራ መጠቀም ለመሆኑ ግልፅ ነው.
16:ዘካቱል ፊጥርን ብንመለከት አንድ ሰው ከህፃን ልጆቹ እና ከሚቀልባቸው ሰዎች ዘካቱል ፊጥርን ያወጣል, የሚወጣላቸው ሰዎች ባልሰሩት ስራ የመነዳሉ በዚህም ይጠቀማሉ, ይህም ባልሰሩት ስራ እና በሌላ ሰው ስራ መጠቀም ለመሆኑ ግልፅ ነው.
17:ሕፃን እና እብድ ንብረት ካላቸው ወሊዮቻቸው (አሳዳሪዎቻቸው)ከንብረቱ ዘካ ያወጡለታል, ሕፃን እና እብዱም በዚህ ይጠቀማሉ, ይህም በሌላ ሰው ስራ መጠቀም ለመሆሁ ግልፅ ነው.
18:ሰላቱል ጀናዛ በሞተ ሰው ሲሰገድ እና ዱዐ ሲደረግለት ይሄ የሞተው ሰው በህይወት ባሉ ሰዎች ሰላት እና ዱዐ መጠቀሙ ግልፅ ነው ይህም በሌላ ሰው ስራ ለመጠቀም ግልፅ ነው::
በዚህ ጉዳይ ያሉትን ማስረጃ እንሰብስብ ከተባለ ቦታው ስለማይበቃ ከወዲሁ እንመለስ እና በሌላ ርዕስ እንገናኛለን ኢንሻ አላህ.


https://t.me/yenebiyu_wedaj_yeulemoch_akbari