Get Mystery Box with random crypto!

#ውትድርናውንናወታደሩንበልኩ ▬▬▬▬▬▬▬▬ #የውትድርና ሀሁው እንኳን ገና በቅጡ ሳይገባኝ ... | Moha Mossen መሐመድ ሐሰን

#ውትድርናውንናወታደሩንበልኩ
▬▬▬▬▬▬▬▬
#የውትድርና ሀሁው እንኳን ገና በቅጡ ሳይገባኝ ... ያኔ ገና ልጅ እያለሁ ልክ እንደዛሬዎቹ ታላላቆቼ አስብ ነበር። ወታደርንና ወታደርነትን መደገፍና መፈለግ ጦርነትን መደገፍ ይመስለኝ ነበር። ታዲያ ያኔኔኔ ነው።
ግን ደግሞ የጦርነት ሳይንሱ ሀሁ ሲገለጥ ሌላኛውና ትልቁ እውነት ይገለጥልናል። ይህንን ሀይል አብዝተን የምንፈልገው፣ የምናከብረው፣ የምንገነባው፣ የምንደግፈው ጦርነትንና እልቂትን ለማስቀረትም መሆኑ ነው። እውነተኛ ሰላምን ለማምጣት ነው። ለመዋጋት ሳይሆን ውጊያን ለማስቀረትና ሳይዋጉ ለማሸነፍም ጭምር ነው።

አሁን የተገነባውንና እየተገነባ ያለውን ሰራዊት ጥንካሬም የምለካው ባለፉት አራት አመታት ባደረገው ሳይሆን ባላደረገውና ባስቀረው ውጊያ ነው። ከጠላቶቹ ጋር ተታኩሶ ካስመዘገበው ድል በላይም በኛው በኩል የተዘራበትን መርዝና ሴራ ተቋቁሞ እዚህ በመድረሱ ነው። ባይሆንማ ባለፉት አራት ዓመታት የራሱን የመከላከያ ሀይል በዚህ ደረጃ ሊያፈራርስ የታገለ የሌላ ሀገር ዜጋ ማግኘት እስኪቸግረን ድረስ፣ ያልተወረወረበት አንካሴ አልነበረም። ነገር ግን የኛኑ ፍላጎት ከመተግበርና የወረወርንበትን ሁሉ መልሶ ከመወርወር ይልቅ ለመቆሚያነት፣ ለልበ ሰፊነት መደላድል አድርጎ በመጠቀሙ እያሸነፈ እዚህ ደርሷል። መጠንከሩንም ሆነ ባለመዋጋት ማሸነፍ መቻሉን በተግባር አሳይቷል።
እናም መከላከያን አብዝተን የምንደግፈው የሰላም ደጋፊ ስለሆንን ነው።
ከዚህ ውጪ ከሳይንሱም ከሀቁም ሩቅቅቅ የሆናችሁ፣ ቢያንስ የኛን መረዳት በናንተ ጠማማና ጉድለት ለመጀቦን አትጣጣሩ። ከመከላከያ በተቃራኒ ቆሞና ያለመከላከያ ሰራዊት የሚከበር ሰላምም የሚኖር ሀገርም የለምና፣ በቅጡ ባልገቧችሁ ውድ ሀብቶች አትሸቅጡ። #ጎሽ #ግፋ እያለ ጦርነትን የጎሰመ ያለ አታስመስሉት። እሱን የሚፈልግ ኢትዮጵያዊ ያለ ማስመሰልም ኢትዮጵያውያንን ካለማወቅ የሚመጣ ነው። ግን ግን ፍርሃታችሁንና ከርሳችሁን የሀገር ሚዛን አድርጋችሁ አታቅርቡልን።
#ክብርለፀጥታሀይላችን
#ኢትዮጵያዊነትአሸናፊነት
#መከላከያለሰላሜ