Get Mystery Box with random crypto!

#UPDATE #EHRC በማህበራዊ ሚዲያ የተለቀቀው ቪድዮ ' ... በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ የሚታ | EMK Channel

#UPDATE #EHRC

በማህበራዊ ሚዲያ የተለቀቀው ቪድዮ

" ... በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ የሚታየው ከሕግ ውጭ የተፈጸመ የግድያ ድርጊት (Extra-judicial killings) ኢሰመኮ መጋቢት 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ሪፖርት ላይ የተካተተ ነው።

የኢሰመኮ የምርመራ ሪፖርት ከምስክሮች እና በስፍራው በመገኘት በመስክ ምልከታ ያሰባሰበውን መረጃ መሰረት በማድረግ፣ ድርጊቱ በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ደዋ ጨፋ ወረዳ ልዩ ቦታው እንቶሊ አካባቢ በታኅሣሥ ወር 2014 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሳምንት (ቀኑ በትክክል ያልታወቀ) መፈጸሙን፤ እንዲሁም በወቅቱ በነበረው መረጃ መሰረት የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በሁለት የጭነት መኪኖች ጭነው ያመጡዋቸውን እና ወደ 30 የሚጠጉ የኦነግ ሸኔ አባሎች ናቸው ያሏቸውን ሰዎች በጅምላ በጥይት ደብድበው መግደላቸውን ይገልጻል። 

ኢሰመኮ ተንቀሳቃሽ ምስሉን ከተመለከተ በኋላ ባደረገው ተጨማሪ ማጣራትና የቴክኒክ ምርመራ፣ በመስክ ምርመራ በለየው ስፍራና በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ ያለውን ስፍራ በቴክኒክ ምርመራ በማነጻጸር፣ እንዲሁም ምስሉ የተቀረጸበትን ቦታ ለማነጻጸርና ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የቴክኒክ ምርመራዎችን በማድረግ፤ ከዚህ በላይ የተገለጸው በኢሰመኮ ምርመራ የተዘገበው ከፍርድ ውጭ የተፈጸመ የግድያ ድርጊት የሚያመለክት ተጨማሪ ማስረጃ ስለመሆኑ በምክንያታዊ አሳማኝነት አረጋግጧል "

#ኢሰመኮ

@tikvahethiopia