Get Mystery Box with random crypto!

አንድን ስልክ ኦሪጅናል መሆኑን እንዴት ማወቅ እንችላለን ? በብዙ መንገድ የአንድን ስልክ ኦ | 🇲oвιle 🇹єϲниιϲιαиѕ

አንድን ስልክ ኦሪጅናል መሆኑን እንዴት ማወቅ እንችላለን ?

በብዙ መንገድ የአንድን ስልክ ኦሪጅናሊቲ ማወቅ የምንችል ቢሆንም እኔ ግን በጣም ቀላሉን ዘዴ ልንገራቹ ፡፡
በመጀመሪያ cpu-z, cpu checker , device info … ከነዚ አፕዎች ዉሰጥ አንዱን በማዉረድ ከታች የተዘረዘሩትን ነገሮች ቼክ እናደርጋለን ፡፡

ማኑፋክቸር(manufacturer) : ለምሳሌ ሰልኩ ሳምሰንግ ከሆነ manufacturer የሚለዉ ሳምሰንግ ነዉ መሆን ያለበት ኮፒ ስልክ ከሆነ ሌላ ነገር ነዉ የሚለዉ ፣ በተመሳሳይ መልኩ ስልኩ Huawei ከሆነ manufacturer የሚለዉ Huawei & etc.

ሲፒዩ(cpu) : ይሄንን ስቴፕ ቼክ ስናረግ የስልኩን processor ማወቅ ይጠበቅብናል ወይም google ላይ የስልኩን specification…በማየት processor የሚለዉን ማስተያየት ይኖርብናል፡፡
ብዙ ሳምሰንግ ሰለኮች qualcom snapdragon, exynos ሲሆን ኮፒ ሳምሰንጎች ደሞ mtk,spd & etc ይላሉ፡፡

ይሄንን ስናይ ጎግል ላይ ካለዉ የሰልኩ ሰፔሲፊኬሽን(specification) በማየት የሰልኩን ሙሉ መረጃ(storage,ram,camera,battery &etc) በማመሳሰል ኦሪጅናል እና ኮፒ መሆኑን ማወቅ እንችላላን ፡፡

የስልኩን ስፔሲፊኬሽን ለማየት ጎግል ላይ ገብተን ለምሳሌ የsamsung A20s ማየት ከፈለግን
Samsung A20s full specification ብለን ሰርች በማረግ አፕሊኬሽኑ ላይ ያለዉን ኢንፎ በማመሳሰል በቀላሉ ማወቅ እንችላለን፡፡

ከተመቻቹና ጠቃሚ ሆኖ ካገኛቹት share ማድረግ እንዳይረሱ አመሰግናለሁ፡፡
ምንም አይነት ጥያቄ ካልዎት ኮመንት አድርጉኝ