Get Mystery Box with random crypto!

ምርጥ ምሳሌያዊ ንግግሮች

የቴሌግራም ቻናል አርማ mirtababaloch — ምርጥ ምሳሌያዊ ንግግሮች
የቴሌግራም ቻናል አርማ mirtababaloch — ምርጥ ምሳሌያዊ ንግግሮች
የሰርጥ አድራሻ: @mirtababaloch
ምድቦች: ቋንቋዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.27K
የሰርጥ መግለጫ

በቻናሉ አዝናኝ እና አስተማሪ ምሳሌያዊ ንግግሮች ከሁሉም የአለም ክፍል ተተርጉሞ ይቀርባል
ለማንኛውም አስተያየት ሆነ ጥያቄ @mirtababaloch1bot ላይ ያገኙናል

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-08-01 16:32:57 ሰዎች በሁለት ይከፈላሉ: መንግስት ሰለነሱ ሚጨነቅ የሚመስላቸው እና አዕምሮ ያላቸው

#ናታን_ፍሬሰር @mirtababaloch
8.0K views13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-28 18:41:15 ለዝሆን እንቁራሪትን መግደል ጀግና አያስብለውም

#ታንዛኒያ @mirtababaloch
8.0K views15:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-26 18:29:28 በእምነት ተራራም ይገፋል

#ቻይና @mirtababaloch
7.7K views15:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-26 16:08:15 ጦርነትን የጃጁ ሽማግሌዎች አስጀምረውት፤
ገና ያልኖሩ ለጋ ወጣቶች ይሞቱበታል

#ሞዛምቢክ @mirtababaloch
7.6K views13:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-19 21:11:20
እንኳን አደረሰን ፤ አደረሳችሁ!

ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1442ኛው ዒድ አል አድሀ በዐል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን

ዒድ ሙባረክ መልካም በዐል

•═••• •••═• ​​

@mirtababaloch
7.6K views18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-18 21:05:47 በሰላም ጊዜ ልጅ አባቱን ፤
በጦርነት አባት ልጁን ይቀብራል

#Vijaya @mirtababaloch
7.0K views18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-17 18:52:34 ወንዶች የራሳቸውን ነፃነት ከመጠቀም በላይ የሴትን ነፃነት መገደብ ያስደስታቸዋል

#Normal_People(movie) @mirtababaloch
7.1K views15:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-16 20:39:00 ተአምር ፈልቋል በየመንገዱ

(በእውቀቱ ስዩም)

ዐይኔን ጨፍኜ -እስከምከፍተው
ስንቱ ታሪክ ነው- የተከሰተው
አፌ ላይ ሳይደርስ - ያፈስኩት ቆሎ
ስንቱ ተተክሏል- ስንቱ ተነቅሎ
በፊት በር ሲዘልቅ -ብስራት አብሳሪ
በጉዋሮ ገብቷል- መርዶ ነጋሪ ::

እባብ በረረ- ያለ ልማዱ
ርግብ መሬት ላይ -ሲሳብ በሆዱ
ተአምር ሞልቷል- በየ ሰከንዱ
ተአምር ፈልቋል- በየመንገዱ
አንዴ ከመላክ- አንዴ ከሰይጣን
ለመደነቂያ፥ ጊዜ ነው ያጣን፤
7.5K views17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-04-23 21:37:36
የረመዳን ወር በመጣ ጊዜ የጀነት በሮች ይከፈታሉ፤ የእሳት በሮች ይዘጋሉ፤ ሸይጣኖችም ይታሰራሉ።


#ነብዩ_መሀመድ(ሰዐወ) #mirtababaloch
17.4K views18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2019-10-28 19:25:22 ወቅታዊ ምርቃት... አሜን በል !
—----------------------------

ግንባርህን ከቄሮ ዱላ
የኪራይ ቤትህን ከደላላ
ጆሮህን ከመግለጫ
አውቶብስህን ካዲሳባ መውጫ
ያትርፍልህ !

አንገትህን ከገጀራ
አገርህን ከመከራ
ነፍስህን ከባለጊዜ
መንግስትህን ከድንዛዜ
ንብረትህን ከመንጋ አጥፊ
‹ኢሜልህን› ከጠላፊ
ያድንልህ!

እንደተኛህ ‹ሳትከበብ›
ቀን በቁምህ ‹ ሳትመረዝ›
እድሜህ ይርዘም እንዳባይ ወንዝ !
አገርህን ከግብፅ ዛቻ
ወጣትህን ከዘመቻ
ሰላምህን ከዓይን አውጣ
አዝመራህን ከአንበጣ
ያትርፍልህ!

ከመቅደስህ ቅዳሴ እንጅ
የዋይታ እንባ ከቶ አይፍሰስ
በሱብሂ አዛን እንጅ
ጧት ለመርዶ አትቀስቀስ

ዱኒያ ተትረፍርፎልህ
ርዚቅ ቤትህ ይከመር
በከሰረ የደም ምድር
አንደብር ሬሳ አትቁጠር
ከነጋልህ ቀንህ ይመር
ከመሸብህ ሰላም እደር !!


#አሌክስ_አብረሃም @mirtababaloch
21.6K views16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ