Get Mystery Box with random crypto!

፫. ማታ ውኃ አብዝቶ አለመጠጣት ሕልመ ሌሊትን ለማስታገስ አንዱ መፍትሔ ማታ ውኃ አብዝቶ አለ | መርጌታ ሚካኤል የበሀል ህክምና

፫. ማታ ውኃ አብዝቶ አለመጠጣት
ሕልመ ሌሊትን ለማስታገስ አንዱ መፍትሔ ማታ ውኃ አብዝቶ አለመጠጣት
ነው፡፡

፬. መስገድ ሰላም
ጤና
ፍቅር በያላችሁበት ተመኝን ለሀገራችን ሰላሙን ያምጣልን

ዛሬ #ሕልመ ሌሊት
#ሴት ዓይነ ጥላ
#ወንድ ዓይነ ጥላ
#ሴት ዛር
#ወንድ ዛር እናያለን

ከዝሙት አጋንንት እና ከዝንየት በተጨማሪ በሕልመ ሌሊት የሚፈትነን ክፉ አጋንንት የትኛው ነው?

፩. ሴት ዓይነ ጥላ
ሴት ዓይነ ጥላ ያለችበት ወንድ በሕልመ ሌሊት መከራውን ነው የምታበላው፡፡
ዓይነ ጥላዋ ስለምትቀናና ስለምትወደው ሌሊት እየመጣች በተኛበት ትገናኘዋለች፡፡ እጅግ የሚያጸይፈው ደግሞ ሴት ዓይነ ጥላ ወንድን
የምትፈትነው
#በእናቱ
#በእህቱ
#በአክስቱ
#በዘመዱ
#በሥራ ባልደረባው
#በሚያውቃት እና በማያውቃት ሴት እየተመሰለች በሕልመ ሌሊት ትመታዋላች፡፡
አንዳንዱ ላይ ባስ ስትል #በእንስሳት እየተመሰለች ትፈትነዋለች፡፡

ብዙ ወንዶች ሌሊት በተኙበት ከሴት ጋር ገሃድ የሚመስል ግንኙነት ሲፈጽሙ
ቀለል ስለሚያደርጉት፤ ባስ ካለም ፈተና እንጂ ሴት ዓይነ ጥላ መሆንዋን
አያውቁም፡፡
ዓይነ ጥላዋ ወንድን በሴት አምሳል እየመጣች ሁሌ የምትፈትነው
ከሆነ የችግሩ ሰለባ የሆነው ሰው #በመንፈሳዊ ሕይወቱ ታዝለዋለች
#ጸሎት ታስተወዋለች
#ከቤተ ክርስትያን
#ከጸበልታስቀረዋለች
#በሆነው ባልሆነው ዘሩን በማፍሰስ ዘሩን ደካማ ታደግበታለች፡፡
#የመውለድ እድሉን ታጠብበታለች #ሲብስም ልጅ እንዳይወልድ ታደርገዋለች
#ለመካንነት ትዳርገዋለች፡፡

፪. ወንድ ዓይነ ጥላ
ወንድ ዓይነ ጥላ ያለባቸው ወይም የሚያንዣብብባቸው ሴቶች በሕልመ ሌሊት ይመታሉ፡፡
የሴቶች ከወንዶች የሚለየውና የሚከፋው ዓይነ ጥላው እንደ ባል
አድርጓቸው እጮኛና ትዳር እንዳይዙ ከማድረጉ ባሻገር ሌሊት እየመጣ
በሚገናኛቸው ወቅት ዓይነ ጥላዊ መርዙን በማህጸናቸው ውስጥ በማስቀመጥ
እንደ ጽንስ ሆኖ ሊቀመጥ መቻሉ ነው፡፡

በዚህም ሴቶቹ እጮኛ አይዙም፣ትዳር
አይመሠርቱም ምናልባት ትዳር ቢይዙም ትዳራቸውን በተለያየ ምክንያት
መበጥበጡ እንዳለ ሆኖ ማህጸናቸውን በመዝጋት ለልጅ አልባነት ሊዳርጋቸው
ይችላል፡፡
ማህፀናቸውና አፍረታቸው ላይ በመቀመጥም የሩካቤ ፍላጎታቸውን
በመግደል፣የሴትነት ስሜታቸውን በማጓደል ደመ ቀዝቃዛ ያደርጋቸዋል፡፡

ወንድ ዓይነ ጥላው ልክ ወንዶቹን እንደሚፈትነው ሁሉ ሴቶቹንም፦
#በአባታቸው
#በወንድማቸው
#በአጎታቸው
#በቅርብ ዘመዳቸው
#በሚያውቁትና በማያውቁት ሰው እየተመሰለ ይገናኛቸዋል፡፡
ዓይነ ጥላውም ይህንን ልምድ
ያደርገውና ሴቶቹን የሌሊት መጠቀሚያው ያደርጋቸዋል፡፡

ዓይነ ጥላው አንዳንዶቹን ገና ብቅ ሳይሉ፣ምኑንም ሳይለዩ ከሕፃንነታቸው ጀምሮ ይገናኛቸዋል፡፡ ሌሎቹን ደግሞ ለአቅመ ሄዋን ሲደርሱ መገናኘት ይጀምራል፡፡
ሲብስበት ካገቡ በኃላ ባል እያላቸው እየመጣ ይገናኛቸዋል፡፡ አላፍር ሲል ደግሞ እድሜ ሲገፋ፣ስሜት ሲጠፋ እየመጣ ይገናኛቸዋል፡፡ በዚህም ለሕልመ ሌሊት ይዳርጋቸዋል፡፡

፫. ሴት ዛር
ሴት ዛር ያለችበት ወንድ ልክ እንደ ዓይነ ጥላው ሁሉ ሌሊት እየመጣች ወንዱን ትገናኘዋለች፡፡ ሴት ዛር ከዓይነ ጥላ የሚያከፋት ምንም ሴት ዛር ብትሆን ቀኒታ ስለሆነች ጾታ አትመርጥም፡፡

ወንዱን ለሕልመ ሌሊት እና ለሩካቤ ሥጋ ስንፈት ትዳርጋለች፡፡ ሴቶችን ደግሞ ሌሊት እየመጣች በመደበት፦
#ከባላቸው ጋር ሩካቤ እንዳይፈጽሙ
#በባላቸው ዘንድ እንዳይወደዱ
እንዲጠሉ
#ለሩካቤ ሥጋ መስእብ እንዳይኖራቸው ታደርጋለች፡፡

ዓይነ ጥላ በተለይ ሴት ዛር ያለችበት ወንድ መንፈሷ የሕልመ ሌሊት ሰለባ
ከማድረጓም ባሻገር አካላዊ እና ስሜታዊ ጉዳት ታደርስበታለች፡፡ ይህም ወንዱ
እስኪቱ/ብልቱ/ ለግንኙነት ዝግጁ እንዳይሆንና እስኪቱ እየተሸበሸበ ወደ ፍሬው ማህደር እንዲገባ ታደርጋለች፡፡ በቀላሉ እስኪቱን ታመነምናለች፡፡

፬. ወንድ ዛር
ወንድ ዛር ያለባት ሴት ልክ እንደ ወንድ ዓይነ ጥላ ሁሉ ሴቷን ሌሊት እየመጣ ይገናኛታል፡፡ አንድ ሴት ሌሊት እየመጣ የሚገናኛት ወንድ ዓይነ ጥላ ይሁን ሴት ዓይነ ጥላ በምን ትለያለች ካልን ወንድ ዛር ከሆነ ሁሉም በሕልሟ ያለ ፈቃድዋ በግድ እያስገደደ እያስፈራራ ነው የሚገናኛት፡፡ የማታውቀው ኃይለኛ ወንድ በግድ ሲገናኛት ታያለች፡፡

የወንድ ዛር ከዓይነ ጥላው የሚከፋው ሴቷን እንደ ሕጋዊ ባል አድርጎ ማስቀመጥ፣አብሯት ሌሊት በሕልሟ በመማገጥ መኖር ነው ዓላማው፡፡
ወንድ ዛር ያለባቸው ሴቶች
#እጮኛ አይዙም
#ትዳር አይመሠርቱም
#ትዳር ቢይዙም ዛሩ ማሕፀናቸው ላይ ቁጭ ብሎ ልጅ እንዳይወልዱ ያደርጋል #ቢያረግዙም ጽንሱን በደም በመምታት ሊያስወርድ ይችላል፡፡
#እንዲሁም ዛሩ አፍረታቸው ላይ
በመቀመጥ፣ስሜት ቀስቃሽ ገላቸው ላይ በመቆናጠጥ ስሜት አልባ
ያደርጋቸዋል፡፡
#ሩካቤ ሥጋ ቢፈጽሙም ምንም ስሜት እና ደስታ የላቸውም፡፡

ውድ የጥበብ ቤተሰቦች በአንድም በሌላ ከዝሙት አጋንንት ሌላ
#ሴት ዓይነ ጥላ
#ወንድ ዓይነ ጥላ
#ሴት ዛር
#ወንድ ዛር ካለብን የሕልመ ሌሊት ሰለባ ነው የምንሆነው፡፡ እነዚህ
አጋንንት በሥጋዊም በመንፈሳዊም ሕይወታችን የሚያደርሱብን የሕይወት
መቃወስ እንዳለ ሆኖ ለሕልመ ሌሊት ይዳርጉናል፡፡

ውድ የጥበብ ቤተሰቦች ሕልመ ሌሊት (ዝንየት) በተደጋጋሚ ሲፈትነን እግዚአብሔር እንደተወን ቤተ-ክርስትያን
እንዳንገባ፣ እንዳልተፈቀደልን መቁጠር የለብንም፡፡ ይልቁን ፈተና እንደሆነ
አውቀን አጋንንቱን ልንዋጋ ይገባናል፡፡
ሱባኤ ስንገባ ወንድ ሴት ሳይል በሕልመ ሌሊት ምናልባት የሚፈትነን አጋንንት ስለሚኖር እረሳችንን ለፈተና ዝግጁ አድርገን ልንጀምር እንጂ በአጋንንት ፈተና ልንደናበር አይገባል፡፡

የሕልመ ሌሊት መፍትሔ ምንድን ነው?
፩. ጸሎት
ሕልመ ሌሊት የሚያስቸግረን ከሆነ ማታ የእለት ውዳሴ ማርያም ከበረታን
ከመዝሙር ዘጠና ጋር ጸልየን መተኛት፡፡ እመቤታችንን የዝንየት አጋንንቱን
እንድታስርልን እንድታርቅልን መማጸን፡፡ ያኔ በሌሊት በተቃራኒ ጾታ እየተመሰለ
የሚፈትነን የሕልመ ሌሊት አጋንንት (ዝንየት) ሲርቀን በሰላም መኖር
እንጀምራለን፡፡ ብርቱ ጸሎት እንኳን ከሕልመ ሌሊት ከገሃነመ እሳት
ይታደገናልና በርትተን እንጸልይ፡፡ ማታ ማታ ውዳሴ ማርያም፣አርጋኖን የቻልነውን
ያህል ብንጸልይ የእመቤታችን ጥበቃ እናገኛለን፡፡

፪. ሕልመ ሌሊት እንደመታን ተመልሶ አለመተኛት ብዙዎቻችን ሕልመ ሌሊት ሲመታን ተስፋ በመቁረጥ ተመልሰን በዛው እንተኛለን፡፡ ይሄ ድርጊታችን አጋንንቱን ከማስደሰቱም በላይ ለነገ የልብ ልብ ይሰጠዋል፡፡ እኛ በሕልመ ሌሊት ምክንያት ጸሎቱን ትተን ‹‹ጠዋት ታጥቤ እጸልያለሁ›› በሚል ስንፍና ከተኛን አጋንንቱ እየደጋገመ እየመታን ሕልመ ሌሊቱን ጸሎት ለማስታጎያ ያደርግብናል፡፡ ስለዚህ ሕልመ ሌሊት እንደ መታን ፈጥነን በመነሳት ከቻልን ሰውነታችንን መታጠብ ካልቻልን አንቀጸ ሥጋችንን በመታጣብ ጸሎታችንን መጸለይ፡፡