Get Mystery Box with random crypto!

Mɪᴀ Cᴏᴍᴘᴜᴛᴇᴄʜ™ / ሚያ ኮምፒውቴክ /

የቴሌግራም ቻናል አርማ miacomputech — Mɪᴀ Cᴏᴍᴘᴜᴛᴇᴄʜ™ / ሚያ ኮምፒውቴክ / M
የቴሌግራም ቻናል አርማ miacomputech — Mɪᴀ Cᴏᴍᴘᴜᴛᴇᴄʜ™ / ሚያ ኮምፒውቴክ /
የሰርጥ አድራሻ: @miacomputech
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.70K
የሰርጥ መግለጫ

በቴክኖሎጂ ዙሪያ የማማከር ሰራዎችን እንዲሁም የኮምፒውተርና የቢሮ ማሽን ጥገና፣የኔቶርክ ዝርጋታ፣የደህንነት ካሜራና የአሻራ ማሽን አቴንዳንስ ገጠማ ሌሎች የቴክኖሎጂና ተዛማች እቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ሁሉንም አገልግሎቶች በድርጀታችን ሚያ ኮምፒውቴክ ያገኛሉ።
👉 አስተያየትና ጥያቄ ይጻፉልን
@MiaComputechSupport
👉 በስልክ ቁጥራችን ይደውሉ
📞 0933674790

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-15 08:15:48 ፌስቡክዎ መጠለፉን ለማወቅና ከጠለፋ እራስዎን ያውጡ!
1. Setting and Privacy ይግቡ
2. Setting ይንኩ
3. Security
4. Security and login
5. Where you are logged in ከዚህ ውስጥ በምን ሞባይል ወይም ኮምፒውተር፣ የት ቦታና ሀገር፣ በምን ብራውዘር፣ ወይም አፕልኬሽን፣ መቼ ቀን ከዚህ በፊት እንደከፈታችሁት ያሳያችኋል። ነገር ግን ደግሞ Active now በሚል በአረንጓዴ የተጻፈው አሁን የከፈታችሁበትን ይነግራችኋል። ከዚህ በታች የተዘረዘረውን Session ስትመለከቱ የናንተ ካልሆነና የሚያጠራጥር ከሆነ ከታች ላይ Logout All Sessions የሚለውን በመጫን Logout የሚለውን በመጫን እራስዎን ከጠላፋ ማውጣት ይኖርብዎታል።
የተጠለፈ መሆኑ ከተጠራጥሩ በፍጥነት Password መቀየር ይኖርብዎታል።
ከአምስተኛው ተራ ቁጥር በመቀጠል ካለው Step Where you are logged in በታች Login ከሚለው በታች Change password የሚለውን በመጫን current password እና New password በማስገባት Save Changes የሚለውን ይጫኑ።

በተጨማሪም Two factor Authentication On ቢያደርጉት ጥሩ ነው። ይህ On መሆኑ ምንም እንኳን የፊስቡክ አካውንትዎን Password ሰው ቢያውቅብዎ በስልካችሁ የሚላከውን Security code እስካላወቁ ድረስ መክፈትና መጠቀም አይችሉም። ስለዚህ On በማድረግ እንድትጠቀሙ እመክራለሁ። በፈለጋችሁ ሰአት Off ማድረግ የምትችሁ ይሆናል!

እራስዎን ከጠላፊዎች ይከላከሉ!



እንዲሁም ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን ቪዲዮዎችን ብትከታተሉ ምርጥ እውቀትን ልታገኙ ትችላላችሁ
አሁንም የቴሌግራምና የYouTube ቻናሌን Subscribe በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ።

የ YouTube ቻናል ሊንክ
https://youtube.com/channel/UC1p52jTI9znj-4tGkTIG67A

ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/MiaComputech
484 viewsedited  05:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 18:08:32 SSD and HDD ምንድንነው ልዩነታቸው?
SSD ማለት Solid State Drive ማለት ሲሆነ HDD ማለት Hard Disk Drive ማለት ነው።

HDD ኤችዲዲ ወይም ሃርድ ዲስክ ከመግነጢሳዊ ቴፕ የተሰራ እና በውስጡም ሜካኒካል ክፍሎችን የያዘ የመረጃ ማከማቻ መሳሪያ ነው።
ኤችዲዲ መረጃን ለማንበብ(Read) እና ለመፃፍ(Write) በሚሽከረከር ዲስክ ወይም በብረት ፕላስተር ማግኔቲክ የተሸፈነ ነው።

መረጃውን ለመድረስ በክንድ ላይ የተነበበ/የፃፈ ጭንቅላት ከተሽከረከረው ሳህን በላይ ይንሳፈፋል።
ሳህኑን ለማሽከርከር እና ክንዱን ለማንቀሳቀስ የሚያገለግል ሞተርን ያካትታል።

ለHDD ላፕቶፖች 2.5 ኢንች መጠን ያላቸው ሲሆን ለዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች 3.5 ኢንች ነው።
HDD በብዛት SATA («stands for "Serial Advanced Technology Attachment," or "Serial ATA") ኢንተርፊስን ይጠቀማሉ።

SDD ከHDS ጋር አንድ አይነት ተግባራትን ያከናውናል፣ ነገር ግን SDD መረጃን ለማከማቸት interconnected flash-memory chips (እርስ በርስ የተያያዙ ፍላሽ-ሜሞሪ ቺፖችን) ይጠቀማሉ።

ስሙ እንደሚያመለክተው solid-state drive ፣ ይህ ማለት በSSD ውስጥ ምንም ተንቀሳቃሽ ክፍሎች የሉም ወይም እንደ HDD የሚሽከረከር ዲስክ የለም።

SSD ከSATA Ports እና 2.5 ኢንች ፎርማት በHDS ምትክ በቀላሉ ከኮምፒውተር ጋር ማገናኘት ይቻላል።

እንዲሁም በሚኒ-PCI (Peripheral Component Interconnect) ኤክስፕረስ ማስገቢያዎች ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉ ሚኒ-SATA (mSATA) ያላቸው ትናንሽ SSDs አሉ።

አብዛኞቹ ዘመናዊ ላፕቶፖች SSD በ PCI Express Expansion slot ከገባ ወይም በቀጥታ በማዘርቦርድ ላይ በማገናኘት መጠቀም ይቻላል።

HDD ከSSD ርካሽ ነው
HDD ከSSD ዝቅተኛ የሆነ መረጃን Read/Write የማድረግ አቅም አለው
HDD ከSSD በይበልጥ ሀይል(ባትሪ) ይጠቀማል
HDD ከSSD ዲስኩ ስለሚሽከረከር ድምጽ የማሰማት ሁኔታ ይታያል
HDD ከSSD በጥንካሬ/ በቆይታ የተሻለ ነው
HDD ከSSD በክብደትና በአካላዊ ግዝፈት ይበልጣል

ኮምፒውተራችን SSD ወይም HDD Disk መሆኑን ለማርጋግጠ የWindows key + R ቁልፍ ስትጫኑ Run box ይመጣል ከዛም, dfrgui በመጻፍ Enter ይጫኑ.
Drive Media Type የሚል ቦክስ ይመጣል ከዛም የኮምፒውተር ዲስክ HDD ከሆነ Hard Disk Drive ወይም SSD ከሆነ Solid State Drive የሚል ይመጣል።

እንዲሁም ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን ቪዲዮዎችን ብትከታተሉ ምርጥ እውቀትን ልታገኙ ትችላላችሁ
አሁንም የቴሌግራምና የYouTube ቻናሌን Subscribe በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ።

የ YouTube ቻናል ሊንክ
https://youtube.com/channel/UC1p52jTI9znj-4tGkTIG67A

ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/MiaComputech
382 viewsedited  15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-19 16:43:36 በጣም ጠቃሚ የሆነ 20 የኮምፒውተር አቋራጮች
------------------------------
CTRL + A - Select all
CTRL + Z – Undo
CTRL + Y - Redo
CTRL + S – Save
CTRL + C - Copy
CTRL + V - Paste
CTRL + U - Underline
CTRL + X - Cut
CTRL + B - Bold
CTRL + D - Fill down cell
CTRL + E - Center Alignment
CTRL + F - Find
CTRL + G - Go to current
CTRL + H - Replace
CTRL + I -. Italic
CTRL + J - Full justification
CTRL + K - Create hyper link
CTRL + L - Left Alignment
CTRL + M - Tab
CTRL + N - New page
CTRL + O - Open
CTRL + P - Print
CTRL + R - Fill right cell
CTRL + S - Save
CTRL + U - Underline
CTRL + V - Paste
CTRL + X - Cut
CTRL + Y - Redo
CTRL + Z - Undo
እንዲሁም ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን ቪዲዮዎችን ብትከታተሉ ምርጥ እውቀትን ልታገኙ ትችላላችሁ
አሁንም የቴሌግራምና የYouTube ቻናሌን Subscribe በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ።

የ YouTube ቻናል ሊንክ
https://youtube.com/channel/UC1p52jTI9znj-4tGkTIG67A

ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/MiaComputech
2.0K viewsedited  13:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-17 09:36:56
#ነፃ_ዋይፋይ

ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ ፣ እንጦጦ ፣ አንድነት ፓርክ እና የወዳጅነት አደባባዮች በከፍተኛ ወጪ የዋይፋይ (WiFi) አገልግሎት ገንብቶ በነጻ ማቅረቡን ዛሬ ገልጿል።

Inbox https://t.me/MiaComputech_bot

Join us on https://t.me/MiaComputech
1.3K viewsedited  06:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-15 18:18:54
የምስራች ለድርጅት ደንበኞቻችን!
በርከት ላሉ ተከፋዮች በቀላሉ በአንድ ጊዜ ክፍያ በቴሌብር መፈፀም ተቻለ!

Inbox https://t.me/MiaComputech_bot

Join us on https://t.me/MiaComputech
1.3K viewsedited  15:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-31 22:26:42
ቴሌግራም በተጠናቀቀው 2021 / እ.አ.አ. / ድንቅ የሚባል አመትን እንዳሳለፈ የድርጅቱ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ፓቬል ዱሮቭ ዛሬ ምሽት አሳውቀዋል።

ጥር ወር ላይ በመላው ዓለም ላይ በብዛት ዳውንሎድ የተደረገ መተግበሪያ ፣ በጥቅምት ወር በአንድ ቀን ብቻ ከ70 ሚሊዮን በላይ አዳዲስ ተጠቃሚዎችን መቀበል የቻለ እንዲሁም በታህሳስ ወር በፍጥነት እያደገ ያለ መተግበሪያ ተብሎ መታወጁ ተገልጿል።

የድርጅቱ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ፥ " የእድገቱ ሁሉ ባለቤቶች ተጠቃሚዎቹ እንደሆኑ እናውቃለን " ያሉ ሲሆን በተጠቃሚዎች የሚሰጡትን አስተያየቶች በጥሞና በማድመጥ አመቱን ሙሉ ቴሌግራም ለተጠቃሚዎቹ የተሻለ እንዲሆን አድርገናል ብለዋል።

ቴሌግራም በተጠቃሚዎች ጥያቄ መሰረት በቻናሎች፣ ግሩፖች እንዲሁም የአንድ ለአንድ መልዕክ ልውውጥ ወቅት ሪአክሽን መስጫ ( ...) እንዲሁም የመልዕክት መተርጎሚያ የተካተተበት በዓመቱ 12ኛ ዋና ማሻሻያ ተደርጎበት ተለቋል።

አዲሱ የሪአክሽን ማሻሻያ የሚሰራው የቻናሉ ወይም የግሩፑ ባለቤቶች ክፍት ሲያደርጉ ነው። እንዴት ? (ወደ ቻናሉ /ግሩፕ በመግባት Edit የሚለውን መጫን ፣ በመቀጠል Enable Reactions የሚለውን ON ማድረግ እና የሚሰጡትን Reaction መምረጥ)

ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ዋናውን የቴሌግራም መተግበሪያችሁን (ባለ ሰማያዊ ምልክቱን) Update በማድረግ ማሻሻያዎቹን እንድትመለከቷቸው መልዕክት እናስተላልፋለን።

የቴሌግራም መተግበሪያችሁን Update ለማድረግ
https://play.google.com/store/apps/details?id=org.telegram.messenger

Inbox https://t.me/MiaComputech_bot

Join us on https://t.me/MiaComputech
1.5K views19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-22 13:25:59
ታላቅ ቅናሽ!
የዘወትር አገልጋያችሁ ኢትዮ ቴሌኮም ያልተገደበ ፕሪምየም ጥቅል አገልግሎት ላይ እስከ 34% የሚደርስ ታላቅ ቅናሽ በማድረግ በአነስተኛ ዋጋ ብዙ ይጠቀሙ ዘንድ ይጋብዝዎታል!
ጥቅሉን በማይ ኢትዮቴል እና ቴሌብር የሞባይል መተግበሪያ እንዲሁም በ*999# በቀላሉ ይግዙ ለወዳጅ ዘመድ በስጦታ ይላኩ፡፡

Inbox https://t.me/MiaComputech_bot

Join us on https://t.me/MiaComputech
1.2K viewsedited  10:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-26 21:40:22
ቲክቶክ ለወደድነው ቪዲዮ ገንዘብ ቲፕ የምናደርግበት አማራጭ እየሞከረ መሆኑን አስታወቀ።

አዲሱ የቲክቶክ አገልግሎትም በማህበራዊ ትስስሩ ላይ ተጭነው ለወደድነው ምስል ጉርሻ ገንዘብ (ቲፕ) ለመስጠት የሚያስችል መሆኑም ነው የተነገረው። “ቲፕ (tips)” የሚል አማራጭ የሚመጣው አዲሱ አገልግሎት 5፣ 10 እና 15 ዶላር ቲፕ ማደረግ ያስችላል ሲል ዘ ቨርጅ የተባለው ድረ ገፅ አስነብቧል።

ከአማራጮቹ ውጪም ቲፕ ማድረግ የሚፈልግ ሰው ዝቅተኛ ተብሎ ከተቀመጠው 1 ዶላር ጀምሮ እስከፈለገው የገንዘብ መጠን ድረስ ቲፕ ማድረግ የሚችል መሆኑም ታውቋል። በቲክቶክ ላይ በጉርሻ መልክ (ቲፕ) የተሰጠው ገንዘብ ሳይቆራረጥ ለባለ ተንቀሳቃሽ ምስሉ (ቪዲዮ ባለቤት) የሚደርስ መሆኑም ነው የተሰማው።

በቲክቶክ ላይ የጉርሻ (ቲፕስ) ተጠቃሚ ለመሆን ተጠቃሚዎች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች እንዳሉም ኩባንያው አስታውቋል። ከመስፈርቶቹ ውስጥ ተጠቃሚው ቢያንስ 100 ሺህ ተከታዮች ያሉት ሊሆን ይገባል የሚለው ዋነኛው ሲሆን፤ የቲክቶክ የእድሜ መስፈርት ማሟላትም ሌለኛው ነው ተብሏል።

በቲክቶክ ላይ ቲፕ የሚያደርግ ወይም ጉርሻ የሚሰጥ ሰው እድሜው ከ18 ዓመት በላይ መሆን አለበት የሚለውንም ኩባያው በመስፈርትነት አስቀምጧል። የቲክቶክ ቲፕ አገልግሎት አሁን ላይ በሙከራ ደረጃ የተሰወኑ ገጾች ላይ ብቻ መለቀቁ የነገረ ሲሆን፤ በምን ያክል ስፋት እና መቼ ሙሉ በሙሉ ይለቀቃል የሚለው ላይ ግን ኩባያው አስተያየት አልሰጠም።

Inbox https://t.me/MiaComputech_bot

Join us on https://t.me/MiaComputech
1.6K viewsedited  18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-06 22:31:18
ከአሁን በኋላ ሳይጠቀሙበት ጊዜው የሚያልፍ ጥቅል የለም ያለዎትን ቀሪ ጥቅልም ለሌሎች ማጋራት ይችላሉ ሲል ኢትዮ ቴሌኮም ገልጿል።

Inbox https://t.me/MiaComputech_bot

Join us on https://t.me/MiaComputech
1.9K viewsedited  19:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-21 08:11:13
የፕሪንተር ኮምፒውተር ማገናኛ ገመድ

ከፈለጉት አሁኑኑ ይደውሉልን

0973095944


tg://open?shop_id=1386483253&product_id=15147

Inbox https://t.me/MiaComputech_bot

Join us on https://t.me/MiaComputech
2.1K viewsedited  05:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ