Get Mystery Box with random crypto!

#ቤተ_ክርስቲያን_የመሳለም_ሥርዓት ጠዋትና ማታ ቤተ ክርስቲያን ለመሳለም መትጋት ያስፈልጋል። ( | 💜 ...ማርያምን ...🕯

#ቤተ_ክርስቲያን_የመሳለም_ሥርዓት

ጠዋትና ማታ ቤተ ክርስቲያን ለመሳለም መትጋት ያስፈልጋል። (ምሳ.8:34)
ወደ ቤተክርስቲያን ሲገባ ከቅፅረ ቤተክርስቲያን በር ላይ ሲደርሱ መሳለም ይገባል።

መዝ.28፥2፣ 95፥9፣ ኤር.26፥2፣ ሕዝ.46፥3፣ ፊልጵ 2፥9-10
ሁላችሁም አስተውሉ ስንሳለም እንደት ነው????

መጀመሪያ ቀኝ እጅን ላይ ዋ ጣታችንን ቀጥ እናደርጋለን
ከዛ እረጅም ወይም የመሀል ጣታችንን እጥፍ እናደርጋለን ከ ዋ ጣት ጋር ስናገናኘው መስቀል ይሰራል ከዋላ ያሉትን ሁለት ጣቶች እንዲመቸን አጠፍ አጠፍ እናደርጋቸዋለን።

#ምሳሌያቸው

በቀኝ እጅ መሳለማችን ገነትን በመሻት ወይም እግዚአብሔር በገነት ስለሆነ ያለው ገነትን ለማመልከት ነው።

መስቀል መስራችን ደግሞ መዳናችንን ለማመልከትና እንደተሰቀለ ለመመስከር ነው።

ስንሳለም በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ማለት አለብን።
ትርጉሙም፥ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ነው ማለት ነው።

ስንሳለም፥ መጀመሪያ መስቀል እንደሰራን በቀኝ እጃችን ግንባራችን ላይ እናደርጋለን።

#ምሳሌው፥ እግዚአብሔር በሰማይ እንደሚኖር እንደማይመረመር ለመግለፅ ነው።

ከዛ፥ ወደ ታች እደረታችን እና ሆዳችን አካባቢ እናደርጋለን።

ምሳሌው፥ ጌታ ከሰማየ ሰማያት መውረዱን ከድንግል ማርያም መወለዱን ለመግለ ነው።

ከዛ፥ ወደ ግራ ጎንአችን ከጡታችን በላይ እናደርጋለን።

#ምሳሌው፥ አዳም አባታችን የሞትን ሞት እንደሞተ እና ሲኦል እንደ ገባ ለመግለፅ ነው።

በመጨረሻም፥ ወደ ቀኝ ጎናችን እናደርጋለን።

#ምሳሌው፥ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምን ከገነት ይዞ ጠላታችን ዲያቢሎስን አስፎ ወደ ገነት መግባቱን ለመግለፅ ነው።

ወደ ቤተክርስቲያን ሲገቡ ጫማን አውልቆ ወገብን ታጥቆ አደግድጎ መግባት ነው። ጫማ አድርጎ ቤተ ክርስቲያን መግባት ክልክል ነው።
ዘፀ 3፥5- ዮሐ.ሥ 7፥33
ኢያ 5፥ 15 ፍት፡መን፡12

ሃሳብን በመንፈሳዊ ነገር ወስኖ ወደ ውጪ ወደ አለማዊ ነገር እንዳይሄድ መግታትና መቆጣጠር ያስፈልጋል።
ከካህን ቀርቦ መስቀል መሳለምና በረከትም መቀበል ያሻል።

በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተስለው የሚገኙትን የሥላሴን ፣ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ፣ የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያምን ፣ የመላእክትን ፣
የነቢያትን ፣ የፃድቃንን ፣ የሰማዕታትን ፣ የደጋጎች ቅዱሳንን ሥዕሎች እጅ መንሳትና የአክብሮት ስግደት መስገድ ይገባል።

በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አስተውሉመሳቅ
ሥለ አለማዊ ሥራ መነጋገር ክልክል ነው።

ከገቡ በኋላ:ዝምታ:ፀጥታ
ፍርሃት የእግዚአብሔርን ምህረት በጥብዓተ ልብ መፈለግ አለብን።

ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን የመዘምራንን ማሕሌት፣ የቅዱሳን መላእክትን ምስጋና ፣ የነቢያትን ትንቢት ፣ የሐዋርያትን ስብከት መስሚያና የልዑል እግዚአብሔርን ነገር መማሪያ ቦታ ስለሆነች ነው።

ከዚህም በላይ የሥጋ ወደሙ ምስጢር የሚፈፀምበት ቦታ ስለሆነች ነው።
ዘሌ. 26፥2

#አስተውሉ
አጭርና ያደፈ ልብስ ለብሶ ወደ ቤተክርስቲያን መሔድ ክልክል ነው። ረዘም ያለ እና ንፁህ ልብስ ለብሶ መሔድ ያስፈልጋል።
ዘፀ. 19፥10-11

በተለይ #ሴቶች እራሳችንን ተከናንበን እንዲንፀልይ ታዘናል።

በመጨረሻም ወደ ቤተክርስቲያን ባዶ እጅ መሔድ አይገባም ። መባዕ፣ ምፅዋት ይዞ መሔድ ይገባል። ዘጸ.34፥20
ወሰብሐት ለእግዚአብሔር
shear አርጉት!


ለመቀላቀል
@Mezmure_tewahdo
@Mezmure_tewahdo

ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ