Get Mystery Box with random crypto!

ለምን ጠላኽኝ ለምን ጠላኽኝ ወንድሜ ያንድ አባት ልጆች እኮነን ለምን ጠላኽኝ ወንድሜ ያንድ እናት | 💜 ...ማርያምን ...🕯

ለምን ጠላኽኝ

ለምን ጠላኽኝ ወንድሜ ያንድ አባት ልጆች እኮነን
ለምን ጠላኽኝ ወንድሜ ያንድ እናት ልጆች እኮነን
ብዙ ነው መንግስቱ አብረን እንወርሳለን
ሰፊ ነው ግዛቱ አብረን እንወረሳለን
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የተካፈልኩትን ንብረት አጥፍቼ ብመለስ ዛሬ
አባቴ ናፍቆኝ ብመጣ ልቤን አንገቴን ሰብሬ
ለሁላችንም ይበቃል ብዙ ነው የሱ መንግስት
አይክፋህ ባክህ ወንድሜ ፍቅር ይበልጣል ከሀብት
፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ፊትህ በሃዘን አይጥቆር ድንጋዩን ጣለው ወንድሜ
ተቅበዝባዥ እንዳያደርግህ እጅህ ቆሽሾ በደሜ
ልብህን መልካም ብታደርግ ያንተም መስዋት ያርጋል
ጌታ ለሁሉም እኩል ነው መታዘዝ ንጉስ ያደርጋል
፡፡፡፡፡፡፡፡
ብልጥ ሰለህንሁ አይደለም የተባረኩት በጌታ
ጽኑ መሻቴን አይቶ ነው በኩር ያደረገኝ ስመታ
የበቀል ጦርህን ሸሽቼ በባእድ ሀገር ብኖርም
በልጅ በትዳር ባርኮኛል አብረን እንኑር በሰላም
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ለምን ጠላኽኝ ወንድሜ ያንድ አባት ልጆች እኮነን
ለምን ጠላኽኝ ወንድሜ ያንድ እናት ልጆች እኮነን
ብዙ ነው መንግስቱ አብረን እንወርሳለን
ሰፊ ነው ግዛቱ አብረን እንወርሳለን

#ሼር_አርጉት
@Mezmure_tewahdo