Get Mystery Box with random crypto!

✟አትቁረጡ ተስፋ✟ አትቁረጡ ተስፋ 'የእግዚዐብሄር ልጆቹ/2/ ከእናንተ አይለዩም 'የፍቅር አይ | መዝሙር

✟አትቁረጡ ተስፋ✟



አትቁረጡ ተስፋ 'የእግዚዐብሄር ልጆቹ/2/
ከእናንተ አይለዩም 'የፍቅር አይኖቹ/2/
ምድርና መላዋ ናትና የእግዚዐብሄር
በሰማያት አለ በቀላይ በባህር


በጥልቁ እንኻን ቢሆን ከእናንተ ጋራ ነው
ሞገዶች አትስጉ ሰላም የእግዚዐብሄር ነው
ጌታ አይረሣምና የእጆቹን ስራ
ይኸው በልጆቹ አይተናል ሲሰራ

አዝ______________

እንደ ጠላት ቢሆን እንደርሱ ጉልበት
ማን ነበር የሚኖር ዛሬን በህይወት
የሚያኖር ጌታ ነው የሚገልም ጌታ
ብርቱ እርሱ ብቻ ነው በምድር የበረታ

አዝ________________

በምስጋና ትኑር ፅኑ በፀሎት
በስሙ ታመኑ በፍፁም እምነት
ለእናንተ የምትሆን እግዚዐብሄር ቀን አለው
አትቁረጡ ተስፋ ሁሉም ሀላፊ ነው

አዝ________________

በትሆኑም ከጉድጓድ እሱ ያያችኻል
በማዳኑ ጥላ ይጎበኛችኅል
ገና ያበዛችኻል ከዚህም በላይ
ሁሉ ይቻለዋል ነውና አዶናይ


መዝሙር

Share Share Share Share


@MezmurB
@MezmurB
@MezmurB

@biniy27 @biniy27