Get Mystery Box with random crypto!

ያዕቆብ ከቤርሳቤት ያዕቆብ ከቤርሳቤት ወደ ካራን ሲሄድ የለውም ነበረ አማካሪ ዘመድ ፀሐይ | መዝሙር

ያዕቆብ ከቤርሳቤት

ያዕቆብ ከቤርሳቤት ወደ ካራን ሲሄድ
የለውም ነበረ አማካሪ ዘመድ
ፀሐይ ጠልቃ ነበር ከዚያ እንደ ደረሰ
ከእራሱም በታች ድንጋይ ተንተራሰ


ሕልምንም አለመ ታላቁን እራዕይ
መሰላል ተተክሎ ከምድር እስከ ሰማይ
ሲወጡ ሲወርዱ መላእክት በእርሷ ላይ
እግዚአብሔርም ቆሞ ከላይ ከጫፏ ላይ፤
……….አዝ…………….
የአባቶችህ አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ
ይህንን ምድር ለእርስትህ እሰጥሃለሁኝ
ዘርህ እንደ አሸዋ በምድር ይዘራል
በአራቱም ማእዘን ሕዝብህም ይሆናል
……….አዝ…………….
አበው በምሳሌ እንደ ተናገሩት
ከምድር እስከ ሰማይ አምላክ የዘረጋው
በላይዋ ተቀምጦ በግልፅ የታየባት
የያዕቆብ መሰላል እመቤታችን ናት፤
……….አዝ…………….
ሰማይና ምድር የሚታረቁባት
ወልደ እጓለ እመሕያው የተወለደባት
መላእክት ከሰማይ በአንድ የዘመሩባት
ታላቋ መሰላል እመቤታችን ናት፤

መዝሙር


@MezmurB
@MezmurB

@biniy27