Get Mystery Box with random crypto!

ቀዳሜፀጋ ኢየሱስ ቀዳሜፀጋ ኢየሱስ የአብ የመኑ ክርስቶስ ጌታዬ አምላኬ ነህና ለስምህ ላቅርብ | መዝሙር

ቀዳሜፀጋ ኢየሱስ

ቀዳሜፀጋ ኢየሱስ
የአብ የመኑ ክርስቶስ
ጌታዬ አምላኬ ነህና
ለስምህ ላቅርብ ምስጋና

ውበትና ሞገሴ ግርማ ሆነህ ለነፍሴ
ሰማያዊ ጥበቤ ታበራለህ ለነፍሴ
የእግዚአብሔር አብ ቀኝ ከሞት ያዳንከኝ
ቀዳሚሁ ቃል ጌታ ተመስገን

ንጹህ በግ ክርስቶስ ኃጢያቴን ያስወገድከው
ይቅር ባይ ነህ አምላኬ ለኔ በደል የቆምከው
የእግዚአብሔር አብ ቀኝ ከሞት ያዳንከኝ
ቀዳሚሁ ቃል ጌታ ተመስገን

አለምን ካለመኖር በጥበብ አምጥተህ
መወለድ መሰቀልህ ይደንቃል ማዳንህ
የእግዚአብሔር አብ ቀኝ ከሞት ያዳንከኝ
ቀዳሚሁ ቃል ጌታ ተመስገን

በሞትህ ሞቴ ጠፍቶ ዛሬ በህይወት ቆሜአለሁ
የአብ ኃይሉ ጥበቡ አመሰግንሃለሁ
የእግዚአብሔር አብ ቀኝ ከሞት ያዳንከኝ
ቀዳሚሁ ቃል ጌታ ተመስገን

ዘማሪ ዲያቆን ቀዳሜፀጋ
መዝሙር

Share share share share


@MezmurB
@MezmurB
@MezmurB

@biniy27 @biniy27