Get Mystery Box with random crypto!

#ሰላም እንደምን ሰነበታችሁ የዚህ የጥበብ ቻናል ተከታታዮች እንኩአንን #ለደብረ_ታቦር ቡ | መዝገበ ጥበበ

#ሰላም እንደምን ሰነበታችሁ የዚህ የጥበብ ቻናል ተከታታዮች

እንኩአንን #ለደብረ_ታቦር ቡሄ በአል በሰላም አደረሳችሁ/አደረሰን።

#ደብረ_ታቦር ከዘጠኙ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አበይት በዓላት አንዱ ነው። ቡሄ ማለት ብርሃን፤የደመቀ፤የጎላ ማለት ነው።ይህም ስያሜ በደብረ ታቦር የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ ጋር የተያያዘ ስያሜ አለው። የችቦ ማብራት ትውፊትም ከዚሁ ጋር የተያያዘ ነው።

#ደብረ_ታቦር ማለት የታቦር ተራራ ማለት ነው ተራራው ከገሊላ ባሕር በስተምስራቃዊ ደቡብ በኩል ይገኛል።መሳ.4፥6-14 ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል፤ጌታችን ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል ብሎ ደቀ መዛሙርቱን በጠየቃቸው ጊዜ አንዳንዶች መጥምቁ ዮሐንስ ይሉታል። ሌሎች ኤልያስ ነው፤ይሉታል።ሌሎችም ኤርምያስ ነው ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ ብለውት ነበር።እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ ሲላቸው ቅዱስ ጴጥሮስ "አንተ የህያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ " ብሎ መልሶለታል።ይህ በሆነ በስድስተኛው ቀን ከሐዋርያት መካከል ሥስቱን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ከወጣ በኋላ ብርሃነ መለኮቱን ገለጠላቸው ከዚያም ሙሴን ከመቃብር ኤልያስን ከብሔረ ህያዋን ጠርቶ ያመጣቸው ሙሴ ክብርህን አሳየኝ ብሎት ነበር (ዘጸ. 33፥17-23) ጌታችን ግን በህይወተ ሥጋ እያለ እኔን ሊያይ የሚቻለው ማንም የለም ቢለውም ከመቃብር አስነስቶ ልመናውን ፈጽሞለታል።

ስለ እርሱም ማንነት ግራ ለተጋቡ ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስ ገልጾለት እንደተናገረው የህያው እግዚአብሔር ልጅ እንጂ ከነቢያት አንዱ አለመሆኑንና ለዘለዓለምም ሰዎች በዚህ እንዳይሰናከሉ በተግባር አስተምሯቸዋል።ከዚያም ደመና ጋረዳቸውና አብ ከሰማይ "የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት" ሲል መሰከረ።ማቴ 17፥2 ሉቃ 9፥29።

እግዚአብሔር አምላክ ከበአሉ ረድኤት በረከት ያሳትፈን። አሜን!