Get Mystery Box with random crypto!

ቅዱስ ላሊበላ 23 ዓመት ሙሉ ካነጻቸው እጅግ ድንቅ 11 ቤተ መቅደሶች ውስጥ አንደኛውን በአባ ሊባ | ትምህርተ ሃይማኖት ርትዕት

ቅዱስ ላሊበላ 23 ዓመት ሙሉ ካነጻቸው እጅግ ድንቅ 11 ቤተ መቅደሶች ውስጥ አንደኛውን በአባ ሊባኖስ ስም ሰይሞላቸዋል፡፡ በዐፄ ገብረ መስቀል ያሠራላቸው ሌላኛው ገዳማቸው ትግራይ ተንቤን ውስጥ ይገኛል፡፡ እጅግ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ የሚታወቁት አባታችን እንደ ተስዓቱ ቅዱሳን ከሮም በመምጣት በሀገራችን ላይ ብርሃንን አብርተዋል፡፡ በመጨረሻም ጥቅምት 2 ቀን ተፀንሰው ሐምሌ 3 ቀን ተወለደው ጥር 3 ቀን ባላቅ ክብር ዐርፈዋል፡፡ ቅዳሴ ቤታቸው ደግሞ ሐምሌ 3 ቀን ነው፡፡ ይኸውም ለመጀመሪያ ጊዜ በዐፄ ገብረ መስቀል ጊዜ በስማቸው ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶ የተመረቀበት ዕለት ነው፡፡ የአባ ሊባኖስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡
ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን! እኛንም በአማላጅነታቸው የምንታመን የተዋሕዶ ልጆች የሆንን ሁላችንን ዛሬ ከአባ ሊባኖስ፣ ረድኤት በረከታቸውን ያሳድርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡
(ምንጭ፡- ገድለ አቡነ ሊባኖስ፣ ስንክሳር ዘወርሃ ጥር፣ የቅዱሳን ታሪክ)
Share
@meskal