Get Mystery Box with random crypto!

“ንግባእኬ ፡ ኀበ ፡ ጥንተ ፡ ነገር' “ወደ ቀድሞ ነገር እንመለስ' በሚል ርእስ በሐመረ ብርሃን | መሠረተ ግእዝ | Meserete Ge'ez

“ንግባእኬ ፡ ኀበ ፡ ጥንተ ፡ ነገር"

“ወደ ቀድሞ ነገር እንመለስ" በሚል ርእስ በሐመረ ብርሃን የብራና ሥራዎች ድርጅት ዐውደ ርእይ ተካሄደ ።

በዐውደ ርእዩ የብራና ሙሉ ዝግጅት እና የቅዱሳን ሥዕላት በብራና ላይ እንዴት እንደሚሳሉ የሚያሳይ ትዕይንት ሲሆን ፤ የሀገራችንን የቀድሞ የብራና ሥራ ዳግም ወደ አሁኑ ዘመን የሚመልስ ሥራ ነው ።

ሐመረ ብርሃን የተመሠረተው ከአራት ዓመታት በፊት ሲሆን ዋና ዓላማ አድርገው የተነሡት ከአባቶች የተማሩትን ጥበብ በማወቅ ለትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ ነው ። ወደፊትም ማኅበሩን ወደ ሥልጠና ማዕከል ለማሳደግም ትልቅ ሥራ እየሠሩ ይገኛሉ። በዚህ በአራት ዓመት ጊዜያቸውም አንድ ዓመት ከስድስተ ወር የፈጀ ውስጡ በሐረግና በሥዕላት የተዋበ መሉ የቅዳሴ መጽሐፍ በብራና አዘጋጅተዋል። በተጨማሪ የተለያዩ መጻሕፍትን እና ቅዱሳን ሥዕላትን በብራና አዘጋጅተው ለዕይታ አቅርበዋል።


የሐመረ ብርሃን አድራሻ ፦ ፒያሳ አሮጌው ፓስታ ቤት ግቢ ውስጥ


መጋቢት ፮ ቀን ፳፻፲፭ ዓመተ ምሕረት
................................
መሠረተ ፡ ግእዝ
@MesereteGeez
@MesereteGeez @MesereteGeez