Get Mystery Box with random crypto!

ምርጥ ፎቶዎች እና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዝማሬዎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ mertephoto — ምርጥ ፎቶዎች እና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዝማሬዎች
የቴሌግራም ቻናል አርማ mertephoto — ምርጥ ፎቶዎች እና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዝማሬዎች
የሰርጥ አድራሻ: @mertephoto
ምድቦች: ሙዚቃ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.01K
የሰርጥ መግለጫ

በዚኽ ቻናል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተዘጋጁ መዝሙራት እንዲሁም ሥዕለ ቅዱሳን እና ምርጥ እና የሚመቹ ደስ የሚሉ ፎቶዎች ይለቀቅበታል
ማንኛውንም ሀሳብ አስተያየት ካለ እንዲሁም አንዲለቀቅ የምትፈልጉትን ፎቶዎች እና መዝሙሮችን በዚህ ሊንክ አድርሱን 👉👉👉 @Mtrsetbot👈👈👈

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-27 17:07:51 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ


ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
ዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
ዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ
ቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ
ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
ዘማሪ ዲ/ን ሮቤል ማቲያስ
ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
ዘማሪት አቦነሽ አድነው
ዘማሪት ዶ/ር ሔለን ተስፋዬ

እና የሌሎችንም ...........

ዘማሪዎችን መዝሙሮች እና አዳዲስ
መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር OPEN
የሚለውን ይጫኑት።

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
88 views14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 17:07:50 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ


ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
ዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
ዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ
ቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ
ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
ዘማሪ ዲ/ን ሮቤል ማቲያስ
ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
ዘማሪት አቦነሽ አድነው
ዘማሪት ዶ/ር ሔለን ተስፋዬ

እና የሌሎችንም ...........

ዘማሪዎችን መዝሙሮች እና አዳዲስ
መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር OPEN
የሚለውን ይጫኑት።

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
80 views14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 23:16:26
490 views20:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 23:15:25 ❖የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ትንሣኤና ዕርገት
⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳


ነሐሴ 16 ቀን አስደናቂውን የእመቤታችንን የዕርገቷን በዓል ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን በታላቅ ድምቀት ታከብራለች፤ የቅድስት ድንግል ማርያም መላ ዕድሜዋ 64 ሲኾን ይኸውም በእናት ባባቷ ቤት 3 ዓመት፤ በቤተ መቅደስ 12 ዓመት፤ ጌታን ፀንሳ በቤተ ዮሴፍ 9ወር ከ5 ቀን፤ ከልጇ ጋር 33 ዓመት ከ3 ወር ከቆየች በኋላ፤ ዓለምን ለማዳን በዕለተ ዓርብ በመስቀል በተሰቀለ ጊዜም የሚወድዳት እናቱን ለሚወድደው ደቀ መዝሙር ለዮሐንስ “እነኋት እናትኽ” በማለት አደራ በመስጠት በዮሐንስ በኩል ለሚወድደን ለእኛ የአደራ ልጆቿ እንድንኾንና የአደራ እናታችን እንድትኾን ታላቅ ስጦታን በቀራንዮ በእግረ መስቀል ሥር ሰጠን (ዮሐ ፲፱፥፳፮‐፳፯)፡፡

❖ በዚኽም መሠረት ሐዋርያትም ከአምላካቸው የተሰጠቻቸው የአምላካቸውን እናት ይዘው ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ 72ት ቋንቋ ገልጾላቸው ታላቅ መንፈሳዊ ኀይልን ሰጣቸው (የሐዋ 1፥14)፤ ዮሐንስም በእናትነት የተቀበላት ቅድስት ድንግል ማርያምን በቤቱ 15 ዓመት አኑሯታል፡፡

❖ በነገረ ማርያም በብራናው ላይ እንደተጻፈ 64 ዓመት ሲመላት ልጇ ክርስቶስ ለእናቱ ተገልጾ ከኀላፊው ዓለም ወደ ማያልፈው ሰማያዊዉ ዓለም ሊወስዳት እንደኾነ ነገራት፤ ርሷም ይኽነን ለሐዋርያት ነገረቻቸው፤ እነርሱም “አይቴ ተሐውሪ እግዝእትነ” (እመቤታችን ወዴት ትኼጃለሽ) ብለው ሲጠይቋት “ኀበ ጸውአኒ ወልድየ” (ልጄ ወደ ጠራኝ) በማለት ወደዚያኛው ዓለም የመኼጃዋ ጊዜ እንደደረሰ ነገረቻቸው፤ ይኽነን ሰምተው “ወበከዩ ኲሎሙ ሐዋርያት” ይላል ሐዋርያት በእጅጉ ዐዘኑ አለቀሱ፡፡ ያን ጊዜ ቅዱሳን መላእክት ተገልጸው ሐዋርያትን ማዕጠንታቸውን ይዘው ደስ አሰኝተው እንዲሸኝዋት እንጂ እንዳያዝኑ እንዳያለቅሱ በመንገር አረጋጓቸው፡፡

❖ ጌታም እናቱን “እኔ ኹሉን መጋቢ የኾንኹትን ያጠቡ ጡቶሽን የተባረኩ ናቸው፡፡ እንዲኹም በከፍታ ቦታዎች ወደሚገኙ ሰማያዊ ስፍራዎች ወስጄሽ በአባቴ በመልካም ነገሮች እመግብሻለኊ፡፡ እስከዚያው በጉልበትሽ ላይ ያስቀመጥሺኝ ድንግል እናቴ ማርያም ሆይ በኪሩቤል ሠረገላ ላይ በማኖር ከእኔና ከቸሩ አባቴ ጋር ወደ ሰማያት እወስድሻለኊ፡፡

❖ በመጠቅለያ ጨርቆች እንደጠቀለልሽኝ ኹሉ የእኔ ድንግል እናት ማርያም ሆይ በወለድሽኝ ዕለት በከብቶች በረት ከላም እና አህያ ጋር በአንድ ላይ ከብበውኝ እንዳኖርሽኝ ኹሉ (ኢሳ ፩፥፫፤ ሉቃ ፪፥፯)፤ እኔ ደግሞ ዛሬ ከእኔ ጋር ከሰማያት ባመጣዋቸው በሰማይ መጐናጸፊያ ሰውነትሽን እጠቀልለዋለኊ፤ ከዚያም ከሕይወት ዛፍ ሥር አስቀምጠዋለኊ፣ ኪሩቤልም በሰይፈ ነበልባላቸው እንዲጠብቁት አደርጋለኊ (ዘፍ ፫፥፳፬)፡፡

❖ የተባረከችውን ነፍስሽን የሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም መንበር በተሸፈነችበት መሸፈኛዎች እንድትሸፈን አደርጋለኊ፡፡ እኔን በሚያሳድድበት ጊዜ ሥርዓት አልባውን ሄሮድስ በመፍራት ወደ ግብጽ ምድር እንደተሰደድሽው ኹሉ (ማቴ ፪፥፲፫-፲፰)፤ መላእክቶቼ ኹልጊዜም በክንፎቻቸው እያጠሉብሽ እና መልካም ዝማሬያቸውን እንዲዘምሩልሽ አደርጋለኊ” አላት፡፡

❖ ይኽነንም ልጇ እያላት ጥር 21 እሑድ ዕለት በልጇ ፈቃድ በመዐዛ ገነት፣ በመዝሙረ ዳዊት፣ በይባቤ መላእክት የእመቤታችን ነፍሷ ከሥጋዋ ተለየች፤ ጌታም እንደ በረዶ ጸዐዳ የኾነውን የድንግል ማርያምን ነፍስ በዕቅፉ ውስጥ እንደያዘ ለነፍሷ የከበረ ሰላምታውን ሰጥቶ ባማረው ሸማ ጠቅልሏት ለሊቀ መልአኩ ለቅዱስ ሚካኤል በብርሃናማ ክንፎቹ እንዲሸከማት ሰጠው፡፡

❖ ሊቁ ቅዱስ ያሬድም ይኽነን ይዞ በድጓው ላይ “ፃኢ እምሊባኖስ ሥነ ሕይወት ርቱዕ አፍቅሮትኪ ቡርክት አንቲ እምአንስት ማኅደረ መለኮት ሰላም ለኪ፤ ማርያም እመ አምላክ ወልድኪ ይጼውዐኪ ውስተ ሕይወት ወመንግሥተ ክብር” (የሕይወት ደም ግባት የአምላክ እናት ከሊባኖስ ውጪ፤ ፍቅርሽ የቀና ነው፤ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ፤ የመለኮት ማደሪያ ሰላምታ ላንቺ ይገባል፤ የአምላክ እናት ማርያም ሆይ ልጅሽ ወደ ዘላለማዊ ሕይወትና ወደ ክብር መንግሥት ይጠራሻል) በማለት አመስጥሮታል፡፡

❖ ቅዱሳን ሐዋርያትም ሥጋዋን በክብር ገነዘዋል፤ ከኢትዮጵያ ሊቃውንት መኻከል ስለዚኽ በቅዱሳን ሐዋርያት ስለተደረገው የከበረ የሥጋዋ ግንዘት ቅዱስ ያሬድ አምልቶ አስፍቶ የጻፈ ሲኾን፤ በነሐሴ ፲፭ በአጫብሩ ድጓ ውስጥ በአስደናቂ መልኩ እንዲኽ ተጽፈዋል፡-

╬ “ሐዋርያት አመድበሉ
ሥጋ ድንግል ጠብለሉ
በሰንዱነ ብርሃን ዘላዕሉ
ልብሳ ተካፈሉ”
(ሐዋርያት ተሰበሰቡ፤ ከላይ በመጣ በፍታ (መጐናጸፊያ) የድንግል ሥጋን ጠቀለሉ፤ ልብሷንም ተካፈሉ)

╬ “በደመና ተጋቢኦሙ ሐዋርያት ለድንግል ንጽሕት
ገነዝዋ በክብር ወበስብሐት
ለቀበላሃ ወረዱ ኀይላት
ወቀበርዋ ውስተ ገነት”
(ሐዋርያት በደመና ተሰብስበው ንጽሕት ድንግልን በክብር በምስጋና ገነዟት፤ ለአቀባበሏ ኀይላት ወረዱ፤ በገነት ውስጥም ቀበሯት)

╬ “ተጋቢኦሙ ሐዋርያት እምኲለሄ
በደመናት ዘምሉእ ሡራኄ
ገነዙ በክብር ወበስባሔ
ሥጋ ድንግል ዘይምዕዝ እምርሔ”
(ብርሃንን የተመላ በኾነ በደመናት ሐዋርያት ከአራቱ ማእዝን ተሰብስበው ልብን ከሚመስጥ ሽቱ ይልቅ የሚሸትት የድንግልን ሥጋ በክብርና በምስጋና ገነዙ)

╬ “ተጋቢኦሙ በደመና ሰማይ
ሐዋርያት ሥርግዋን በዕበይ
ገነዝዋ ለድንግል በብዙኅ ግናይ
ዳዊት ዘመራ በመሓልይ”
(በገናንነት የተጌጡ ሐዋርያት በሰማይ ደመና ተሰብስበው ድንግልን በብዙ ምስጋና ገነዟት፤ ዳዊትም በምስጋና አመሰገናት፡፡)

╬“ተጋቢኦሙ አርድዕተ ወልዳ
በደመና ብርሃን ጸዐዳ
ገነዝዋ በስብሐት ለጽርሕ ሳይዳ”
(ጸዐዳ በኾነ በብርሃን ደመና የልጇ ደቀ መዛሙርት ተሰብስበው፤ ውቢቱ አዳራሽን በምስጋና ገነዟት)

╬ “ተጋብኡ በቅጽበት ለግንዘተ እሙ ቅድስት
ብፁዓን ሐዋርያት
ቦኡ ኀቤሃ በሰላም አምኁ ኪያሃ
በስብሐት ገነዙ ሥጋሃ”
(ንኡዳን ክቡራን ሐዋርያት ቅድስት የምትኾን የጌታ እናቱን ለመገነዝ በቅጽበት ተሰበሰቡ፤ ወደ ርሷ ገብተው በሰላምታ ርሷን እጅ ነሧት፤ ሥጋዋንም በምስጋና ገነዙ) በማለት ሊቁ ማሕሌታይ በሐዋርያት እጅ የተደረገ የሥጋዋን ግንዘት አምልቶ አስፍቶ ጽፏል፡፡

❖ ሐዋርያት በታላቅ ግርማ በአምላክ እናት ሥጋ ፊት ምስጋናን እያሰሙ ዝማሬን እየዘመሩ ሥጋዋን እጅ እየነሡ ጌቴሴማኒ ሊቀብሯት ሲኼዱ አይሁድ አይተው ለምቀኝነት አያርፉምና ቀድሞ ልጇ ሞተ፣ ተነሣ፣ ዐረገ እያሉ እያስተማሩ ኖሩ ከመቃብሩም ተአምራት ይደረጋል፤ አሁን ደግሞ ርሷ ሞተች፣ ተነሣች፣ ዐረገች ብለው ሊያስተምሩ አይደል፤ “ንዑ ናውዒ ሥጋሃ ለማርያም ምስለ ዓራታ” በማለት እናቃጥላለን ብለው በምቀኝነት ተነሡባቸው፤ ታውፋንያ የሚባል ከአይሁድ ወገን በድፍረት የአልጋዋን አጎበር ሊነካ ሲሞክር ቅዱስ ገብርኤል በሰይፈ እሳት ቀጣው፡፡

❖ ያን ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ በዕለተ ዐርብ ከአምላኩ በስጦታ የተሰጠችውን የአምላክ እናትን ሥጋዋን በድፍረት ሊነኩ መምጣታቸውን አይቶ “ይቤ ዮሐንስ ወኢይገድፍ ምዕቅብናየ ወዘንተ ብሂሎ ወድቀ በላዕሌሃ” ይላል (ዐደራዬን አላፈርስም፤ ከርሷ ጋር እሞታለኊ በማለት ይኽነን ተናግሮ በላይዋ ላይ ወደቀ፡፡ ከዚያም “ወወረዱ ሚካኤል ወገብርኤል እምሰማይ በዐቢይ ግርማ” ይላል ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል በታላቅ ግርማ ወርደው የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥጋዋንና ቅዱስ ዮሐንስን በደመና ነጥቀው በገነት በሕይወት ዛፍ ሥር አኖሯት፡፡
518 views20:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 12:09:51
985 views09:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 12:04:22 #ቡሄ

ቡሄ ማለት በራ, ብርሃን ደማቅ ማለት ነዉ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በአል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡
✿ወቅቱ የክረምት ጨለማ አልፎ የብርሃን ወቅት ሰማይ ከጭጋግነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቅት ነዉ፡፡ ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት ዶሮ ከጨኽ የለም ለሊት እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልልም ሊጥ ተቦካክቶ ዳቦ የሚጋገርበት *ሙልሙል* የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል፡፡

#ጅራፍ

✿ በደብረ ታቦር በዓል በትዉፊት መልኩየሚታየው ሚስጥር በእየሩሳሌም ስለሆነዉ የጌታችን ሚስጥራዊ ሞቱ ነዉ፡፡

*ጅራፍ መግመድ እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት አይነት ሚስጥር ይዞ የሚከናወን ትዉፊት ተግባር ነዉ፡፡
-የመጀመሪያዉ ግርፋቱን ፡ ሞቱን እናስብበታለን፡፡እንዲሁም ድምፁን ስንሰማ የባህሪ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታዉሰናል፡፡

#ችቦ

ችቦ የጌታችን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነዉ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን አናከብራለን፡፡ የዚህ ትዉፊት የት መጣ ግን በብርሃን ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ቀርተዋል አና ከወላጆቹ ከመንደር ችቦ ለኩሰዉ ልጆቻቸዉን ፍለጋ ሄደዋልና ታሪክን እያዘከርን በዓላቱን እናከብራለን፡፡

#ሙልሙል

✿በችቦ ብርሃን ልጆቻቸዉን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘዉላቸዉ ወጥተዋል፡፡
ስጦታው ቤተሰባዊነትን, ፍቅርን, እና መተሳሰብን መግለጫ ነዉ፡፡ወደ ቤታችን ቡሄ እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም ዘምረዉ እንዳበቁ የሚሰጥ #ሙልሙል ዳቦ አለ፡፡ህፃናቱም ሊዘምሩ ሲመጡ ዳቦ መሰጠት ልማዳዊ ብቻ አደለም ፡፡ ህፃናቱ የደቀ መዛሙርቱ ምሳሌዎች ናቸዉ፡፡

መዝሙራቸዉ ደሞ ሀዋርያት " የምስራች" ይዘዉ የመምጣታቸው ምሳሌ ነዉ፡፡

✿ ሀዋርያት በገቡበት አገር አስተምረዉ አጥምቀዉ የፀጋ ልጅነትን አሰጥተዉ በረከት አድለዉ እንደሚሄዱም ልጆቹ ዘምረዉ ከመስግነዉ መርቀዉ ዉለዱ ክበዱ ሀብት አግኙ የመንግሥት ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ይላሉ፡፡

፡፡
867 views09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 11:45:55
1.6K views08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ