Get Mystery Box with random crypto!

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥ ተገለፀ። ትምህርት ሚኒስቴር በኦን ላይ | 𝗘𝗧𝗛𝗜𝗢 𝗔𝗠𝗔𝗭𝗢𝗡 𝗦𝗧𝗢𝗥𝗘 🇪🇹🛒

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥ ተገለፀ።

ትምህርት ሚኒስቴር በኦን ላይን ሊሰጥ የነበረውን የ2012ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥ አስታውቋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) በኦንላይን ለመስጠት የታሰበው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በኮሮና ምክኒያት መፈተኛ ታብሌቶች በግዜ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት ባለመቻላቸው ፈተናውን በወረቀት ለመስጠት መወሰኑን ገልፀዋል።

በዚህም መሰረት የ2012ዓ.ምሀገር አቀፍ ፈተና የካቲት 29, 2012ዓ.ም እንደሚሰጥ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

ከየካቲት 21-27,2013ዓ.ም ፈተናው እና የመልስ መስጫ ወረቀቶች ወደ ዞኖች እንደሚደርሱም በመግለጫው ላይ ተገልጿል።

የ2012ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በኦንላይን ለመስጠት ትምህርት ሚኒስቴር ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱ የሚታወስ ነው።

@MEREJAET @MEREJAETHIO_BOT #SHARE