Get Mystery Box with random crypto!

በፈተናሸ አትውደቂ! ፨፨፨፨///////፨፨፨፨ በየዋህነትሽ እንዳትጠለፊ፣ ባስቀመጥሽው ማጣሪያ ተጣር | Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™

በፈተናሸ አትውደቂ!
፨፨፨፨///////፨፨፨፨
በየዋህነትሽ እንዳትጠለፊ፣ ባስቀመጥሽው ማጣሪያ ተጣርተሽ እንዳትቀሪ፣ በመረጥሽው መንገድ እንዳትሰናከይ እራስሽን ጠብቂ። ፈታኞች ሁሉ የፈተኑትን ፈተና ቢፈተኑ ላያልፉ ይችላሉ፤ ፈራጆች ሁሉ የፈረዱት ፍርድ ቢፈረድባቸው አሜን ብለው ላይቀበሉ ይችላሉ። አንቺ የማታልፊውን መሰናክል ለአጋርሽ አታስቀምጪ፤ አንቺ ብትገቢ የማትወጪው አዘቅት ውስጥ ወዳጅሽን አታስገቢ። ከባዱን ሁኔታ በንግግር ማቅለል እየተቻል በማይታይና በተሰላ መንገድ መጓዝሽን አቁሚ። አብሮሽ ላለ ሰው ካንቺ በላይ የሚቀርበው ሰው እንደሌለ አስቢ። ነገሮችን የምትመለከቺበትና የምትረጂበት መንገድ አንዳንድ ጉዳዮችን ይባስ ሊያወሳስብ እንደሚችል ተገንዘቢ። ፈተና ችግርን ቢጨምር እንጂ ችግርን አይፈታም፤ ፈተና ጥርጣሬን ቢጨምር እንጂ ግንኙነትን አያጠራም። የሌለ እምነትም በፍፁም በፈተና ሊመጣ አይችልም።

አዎ! ጀግኒት..! በፈተናሽ አትውደቂ! እራስሽ አስበሽ፣ መርጠሽና አቅደሽ ባዘጋጀሽው የታማኝነት ፈተና ቀድመሽ አለመታመንሽን አታሳዪ። ማንኛውም ሰውን ለመገምገም የሚሞክር ሰው አስቀድሞ እራሱን ማየትና እራሱን መገምገም ይኖርበታል። ማንም በሰፈረው ቁና ሳይሰፈር የሚቀር ሰው የለም። የጀርባ ሩጫ ብዙ ዋጋ ሊያስከፍልሽ እንደሚችል እወቂ። ለብቻሽ የምታሴሪው ሴራ፣ በጨለማ የምትፈፅሚው ተግባር፣ በወዳጅሽ ላይ የምትመሰጥሪው ሚስጥር ያለሽን ሁሉ ሊያሳጣሽ እንደሚችል ጠንቅቀሽ አወቂ። እያንዳንዱ ግንኙነት ችግርን በየደረጃው እየፈታና እያቃለለ መሔድ ባለበት ወቅት ችግር ላይ ሌላ ችግር፤ ውስብስብ ሌላ ትብትብ አትጨምሪ። ሁሌም ቢሆን በጀረባ ከመሔድሽ በፊት በፊትለፊት የሚደረገውን ንግግርና ውይይት አስቀድሚ።

አዎ! ጀግናዬ..! ፍፁም ሆነህ ፍፁም አትፈልግምና ከወዳጅህ እንከን ለማውጣት፣ ድክመትን ለመመልከት አትፍጠን። የተበላሹ ነገሮችን ለማስተካከል ግዴታ ሁሉም ነገር አንተ ባልከው መንገድ መሆን የለበትም። አንተ ጋር የሌለ ነገር ምናልባትም ሌላ ሰው ጋር ሊገኝ ይችላልና በፍቃድ ባዘጋጀሀው ፈተና ለአመታት የለፋህበትን ግንኙነት እንዳታጣ ተጠንቀቅ። ማወቅ የምትፈልገውን ጠይቀህ እወቅ፤ መረዳት የሚገባህን ቀጥታ ተረዳ። የተፈጠሩ ክፍተቶችን የተለያዩ ምክንያቶችን እየደረደሩ ይባስ ከማስፋት ይልቅ፣ መንስኤውን መርምረህ እወቅ። ስህተቶችን ለማረም እንጂ ለማባባስ አትሞክር። በማይሆን ፈተናም የእራስህንም ሆነ የግንኙነትህን ውድቀት አታፍጥን።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel