Get Mystery Box with random crypto!

አትጠራጠር! ፨፨፨////፨፨፨ ቀንህ እስኪመጣ ቀናቶችህ ላይ ስራ፤ ያቀድከው እስኪሆን፣ ያሰብከው እ | Mental Counsel ETH | ምክረ-አዕምሮ™

አትጠራጠር!
፨፨፨////፨፨፨
ቀንህ እስኪመጣ ቀናቶችህ ላይ ስራ፤ ያቀድከው እስኪሆን፣ ያሰብከው እስኪሳካ፣ የምታልመው ከግብ እስኪደርስ ጥረትህን ቀጥል። ቀንህ በምኞት ብቻ ውጤት እንደማያመጣ ታውቃለህ፤ ህይወትህ በሃሳብ ብቻ እንደማይቀየር ትረዳለህ፤ ችሎታ፣ ተሰጦንና አቅምን መተንተን ጉዞህን እንደማያቀል ታውቃለህ። ዛሬ ላይ መሆን፣ ዛሬን መኖርና ዛሬን መበርታት ለአላማህ መሳካት ትልቁና ወሳኙ እርምጃ ነው። ወሳኙ ተስፋህ የእግዚአብሔር ፍቃድና ያንተ ጥረት ነው። ቀና የምትልበት ቀን እንደሚመጣ አትጠራጠር፤ ካሰብከው ልኬት በላይ እራስህን የምታገኝበት ወቅት እንደሚፈጠር አትጠራጠር። ያቀድከው ሁሉ ሲሳካ ትመለከታለህ፤ የለፋህበት እቅድ፣ ዘመንህን የጨረሰው የእውቀት አሰሳ፣ የጥበብ ፍለጋ፣ ደጋግሞ የፈተነህ ውጫዊ ጫናና ግፊት አንድ ቀን ይክስሃል።

አዎ! ጀግናዬ...! አትጠራጠር! ሁን ካልከው በላይ እንደሚሆንልህ ያመንከው፣ ልብህን ያዘጋጀህለት፣ ውስጥህን ያሰናዳህለት ነገር በእርግጥም ሆኖ ትመለከተዋለህ። የያዙትን የያዙ፣ ያወቁትን የተረዱ፣ የሚሰሙትን የተገነዘቡ ሚዛን ያላቸው፣ እራሳቸውን የሚያውቁ፣ በጥረታቸው የሚደሰቱ፣ ለእያንዳንዱ እርምጃቸው ትኩረት የሚሰጡ ሰዎች ከማያቋርጥ ጥረታቸው እኩል ልባዊ እምነታቸው፣ የውስጥ ተነሳሽነታቸውና የማይናወጥ ፍላጎታቸው ለስኬት ያበቃቸዋል። በሁለት ሃሳብ ረጅም ርቀት አትጓዝም፤ እያወላወልክ ለግብህ አትበቃም። ሁሌም ቢሆን ቆራጥ ልብ ለውሳኔ የፈጠነ ነው፤ አዋጩን መንገድ ለመከተል የተጋ ነው። ትኩረቱ የሚታይ ለውጥና ግልፅ ተግባር ላይ ነው።

አዎ! እራስን እንደመጠራጠር የኋሊት ጉዞን የሚያፈጥን፣ ከህልም የሚነጥል፣ እውነተኛውን አቅም አሳስሮ የሚያስቀርና ተስፋ ቢስ የሚደርግ አሉታዊ አስተሳሰብ የለም። ከተጠራጠርክ አትጀምረው፤ ከጀመርከው ግን አትጠራጠር። እራስህ ውስጥህ በምትፈጥረው ሃሳብ የችሎታህን ሃይል አትግታ። የጥርጣሬህ መንስኤ የእውቀት ማነስ ከሆነ ተማር፣ እውቀትህን ጨምር፤ የፍላጎት ማነስም ከሆነ እራስህን ደጋግመህ ጠይቀው፤ ድክመትና ስንፍናህም ቢሆን ቆም ብለህ አስብ። በጥርጣሬና በሁለት ሃሳብ ግን የትም እንደማትደርስ ተገንዘብ። ሩጫ ጀምረህ በመጨረስህ ብትጠራጠር፡ አንድ ወይ ካሰብከው ሰዓት ዘግይተህ ትጨርሳለህ ወይም እንደውም ሳትጨርሰው ትቀራለህ። ጥርጣሬ በተመሳሳይ ሁኔታ አንድም ሸክም ሌላም መሰናክልህ ይሆናልና እምነትህ ላይ ስራ፣ የስኬትህን እውንነትም በቅርበት ተመልከት።
ውብ ደማቅ ቀን ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel