Get Mystery Box with random crypto!

ሩዲገር በብቃቱ ጫፍ 6 ጨዋታዎች ፣ 6 ሽንፈቶች – በቀኝ መስመር ተከላካይነት የተጫወተበት የሽቱ | @mensurabdulkeniofficial

ሩዲገር በብቃቱ ጫፍ

6 ጨዋታዎች ፣ 6 ሽንፈቶች – በቀኝ መስመር ተከላካይነት የተጫወተበት የሽቱትጋርት የ2013 ዲኤፍቢ ፖካል ፍፃሜ ተሳትፎና በቼልሲ ቆይታው ከአምስት ዓመታት በፊት 3ለ0 የተረታበትን ጨምሮ አንቶኒ ሩዲገር ባቫሪያኑን በገጠመባቸው ጨዋታዎች በሙሉ ተሸንፏል።

አሁን ግን ጀርመናዊው ከዓለም ምርጥ ተከላካዩች ተርታ የተሰለፈበት ወቅት ነው። የሚጫወተው ደግሞ በቻምፒዮንስ ሊግ ታሪክ ዋንጫዎችን በማሸነፍ አቻ ባልተገኘለት ሪያል ማድሪድ!

ለረጅም ጊዜያት ከኳስ ውጪ በሚፈጥራቸው ያልተለመዱ እንቅስቃሴዎች የተጋጣሚዎችን ትኩረት ለመስረቅ በመሞከር ይበልጥ ይታወቃል። በመልበሻ ክፍል አድማቂነቱም ብዙዎች ያነሱታል። እነዚህ ጉዳዮች ግን የጨዋታ ላይ ብቃቱን ከፍታ አሳንሰውበታል።

በኤደር ሚሊታዎ ጉዳት ምክንያት ከአማካይ ስፍራው ተጫዋች ኦሬሊዮ ቾዮሚኒ ጋር የተጣመረበት ዓመት ለቶኒ የሚፈትነው አልሆነም። በዚህ ወር ኤርሊን ሃላንድና ሮበርት ሌቫንዶቭስኪን ያቆመው ተፋላሚ ተከላካይ ቀጣይ የቤት ሥራ የወቅቱ የቡንደስሊጋ ምርጥ አጥቂ ሃሪ ኬን ነው። የሩዲገር በባየርን የመሸነፍ ታሪክ እዚህ ጋር ያበቃ ይሆን?