Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ለገባችሁ የተውሂድ እና የሱና   ተቆርቋሪዎች የሸርክ እና የቢደዓ ጠላቶች  በ | [መንሀጁል አንቢያዕ]

አዲስ ለገባችሁ

የተውሂድ እና የሱና   ተቆርቋሪዎች የሸርክ እና የቢደዓ ጠላቶች  በሙሉ ሳታነቡ አትለፉ

አሰላሙ ዐለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካትሁ

እነሆ እንደሚታወቀው ሸዋሮቢትን አቅጣጭታ የምትገኘው በኬሚሴ ዞን ውስጥ በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በጥቁሬ ቀበሌ የሚገኙት የአህለሱና ወልጀመዐ ማህበረሰቦች የመስጅድ ግንባታ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ግሩፕ

  ታሪካቸውን በጥቂቱ

በዚች ቀበሌ በጣም ታዋቂ የሆነው የአህለሱና ወልጀምዐ ታጋይ
በዋነኝነት ሸይኽ ሙሀመድ ኑር ነው። ይህ ሸይኽ ዳዕዋውን ከጀመረ ከ20 አመት በላይ ሆኖታል። ነገር ግን ይች ሰፊ የሆነች ቀበሌ ጠንካራ በሆኑ ሱፍዮች እና አህባሾች የታጨቀች ነበረች ዳእዋውን አያደረገ በቀጠለበት ሰአት ይህንን የተውሂድ ጥሪ ካልተውክ ከእድር እናስወጣሀለን በማለት ዛቱበት ነገር ግን የእሱ መልስ እንዲያውም ከዚች ቡድንተኝነት ከበዛባት እድራችሁ ብወጣ እኔ ነኝ ተጠቃሚ የምሆነው ነበር ያላቸው በጣም ከሚያስገርመው ነገር የዚች ቀበሌ ቃዲ ነበር እስከዛች ሰአት ድረስ እነሱ ግን ይህም ሳይበቃቸው ልጅ ቢድር ማንም ሰው ቢሞትበት እሱን አንድ ሰው እንዳይረዳው በሚል ህዝቡ ላይ በቤተሰቦቹ ላይ ሴራ ቀጡ ይህም ሳይበቃቸው መሬቱንም እስከመቀማት ደረሱ ወደየት ይኬዳል ቢከስ ዳኞቹ እነሱ አሏሁል ሙስታዐን

➲ ይህም ሳይበቃቸው አሸባሪ ነው በማለት ብዙ ስቃይን አደረሱ ይህ ሁሉ ግን የነብያቶች ሱና መሆኑን ተረድቶ የተውሂድ ጥሪውን ቀጠለ ብዙ ሰለፍዮችንም አፈራ በሰርግ ሰበብ በሰደቃ ሰበብ ከሸዋሮቢት ፋርቃን መስጅድ ዳዒዎችን እየጠራ በዋነኝነት ኡስታዝ ሙሀመድ አሚንን እንዲሁም ከሰንበቴ፣ ከባልጭ ዳዒወችን በመጥራት ትልቅን ገድል ፈፀመ ሰለፍዮች እየበዙ ሲመጡ ቤት ተከራይተን ቂርአት እንዲሁም ጁሙዓ እስከማቋቋም ደረስን ነገር ግን ይህ ደስ ያላስባላቸው ሱፍዮች አሸባሪ ናቸው በሚል በ 2012 እስር ቤት ከተቱን የወረዳው ሀላፊ ቀበሌ ድረስ በመንጣት ህዝቡን ሰብስቦ ችግራቸው ምንድን ነው ብሎ ሀዝቡን ጠየቀ። ይህ የሱፍያ ማህበረሰብ ችግር ናቸው ብሎ ከቀጠፋቸው ከባባድ ውሸቶች

1 አልቃኢዳ ቡድን ናቸው
2 ዳኢ ብለው የሚያመጧቸው ሰወች በመኪና ሙሉ መሳሪያ ነው የሚያስገቡት
3 ዳእዋ እያሉ ሸዋሮቢት እና ባልጭ ሰንበቴ እየሄዱ አማራ እና ኦረሞን ያጣላሉ ምስክር  እነሱ አሏሁል ሙስታዓን እናም ወረዳው ትንሽ ሱና የሸተተው ስለነበር በተውሂድ ሰወች ላይ የሚያሴሩት ሴራ መሆኑን በመገንዘብ ትንሽ ታስረው ተለቀቁ ከዚያም በገንዘባችን የተከራየነው ቤት ተዘጋብን ከዚያም ወረዳወቹ ያሉት ነገር ቢኖር ትንሽ እንኳ መስጅድ ሰርታችሁ ዳዕዋችሁን ቀጥሉ ነው ያሉት ትላንት በአንድ ሰው የጀመረው ዳዕዋ ሰለፍያ በዚች ቀበሌ ላይ ዛሬ በአሏህ ፍቃድ የተሻለ ለውጥ ይኖር ዘንድ የትም ቦታ የምትገኙ የተውሂድ ጉዳይ የሚያሳስባችሁ እህት ወንድሞቻችን ለዚህ የተውሂድ መስጅድ ስራ አሻራችሁን አሳርፉ በማለት ወደ ኸይር እንጠቁማችኋለን።

الَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَالَهُم بِاللَّيْلِ وَالنَّهَارِ سِرًّا وَعَلَانِيَةً فَلَهُمْ أَجْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ وَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ

እነዚያ ገንዘቦቻቸውን በሌሊትና በቀን በድብቅም በግልጽም የሚለግሱ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፡፡ በእነርሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም እነርሱም አያዝኑም፡፡


አቡል አባስ አሰለፍይ (ኑርየ አሊ አስፍው) ከሰለፊ ወንድሞቹ ጋር

አጠቃላይ እንቅስቃሴያችንን በሚከተለው ሊንክ ግሩፓችንን  በመቀላቀል ይከታተሉ!!!
      ➴➷➘➴➷➘
https://t.me/tikuremesgid