Get Mystery Box with random crypto!

«#አንተ አንባቢ ሆይ አንብብ ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን» «ቅዱስ ቁርዓንን» #ትቀራለህ | 💎🇸🇦🌹የሰለፊ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው

«#አንተ አንባቢ ሆይ አንብብ ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን»

«ቅዱስ ቁርዓንን»
#ትቀራለህ (ታነባለህ)?

      ለምንያህል ጊዜ? ቢያንስ በቀን የተወሰነ ጊዜ የንባብ ልምድ ብታደርግ መልካም ነው።
  
                
                 ↷⇣ ⇣↷

«ቅዱስ ቁርዓንን» ያነበበ ልቡ ጀገነ። ወዳጄ ቁርዓን አዘውትረህ የምታነብ ከሆነ (በኒያ) ልብህ ያንበሳ ሊሆን ነው። ሲቀጥል ካ‘ንድ «አላህ» በቀር ማንንም የማትፈራ የማንንም እርዳታ የማትፈልግ ያደርግሃል።

               
                 ↷⇣ ⇣↷

«
#አላህን» የፈራ ደግሞ

      " ሰው ይወደዋል ፣
           ያቀርበዋል ፣ ያከብረዋል።
ወንድሜ
#በዱንያ "ላይ ብትሰማው ብታነበው እማይሰለች ነገር ቢኖር «#ቅዱስ #ቁርዓን» ብቻ ነው።
                   
                 ↷⇣ ⇣↷

ቁርዓን አይሰለችም እናም አዘውትረው!
     
#ባገኝኸው አጋጣሚ ከ «ከቁርዓን» ጋር ተገናኝ። ያኔ በህይወትህ ላይ ታላቅ ለውጥ ታያለህ። ቁርዓንን በቅጽበት ለመረዳት አለመቻልህ አያሳስብህ። ቅዱስ ቁርዓንን ባነበብክ ቁጥር በዝግታ እየጠራህ‘ና እየጸዳህ ትመጣለሀ።
    "
#በከሰል ማዳበሪያ" ውስጥ ውሀ ከቧንቧ ሞልተህ ወደ ቤት ለማድረስ ብትሞክር እየተንጠባጠበ ፈሶ እንደሚያልቅ ታውቃለህ!?

                ↷⇣ ⇣↷

እያወ‘ክም ቢሆን ከ‘ንደገና ሞክር። አሁንም አሁንም እየሞላህ ወደ ቤት ለመውሰድ ታገል። አሁንም በማዳበርያው ቀዳዳ ውሀው መፍሰሱ አይቀርም። ነገር ግን በተደጋጋሚው ያልተሳካ የውሀ ቅጂ ሙከራህ አንድ ነገር አስተውል።
ያ ጥቀርሻ የመሰለው "የ#ከሰል ማዳበርያ" እየጠራ ነው።

«ቅዱስ ቁርዓንም» እንዲሁ ባነብብነው ቁጥር ያነፃናል ፣ ያጠራናል እና "ሳንታክት «ቁርዓንን» እናንብብ።


በቴሌግራም ይ ላ ሉን!
      
                 ↷⇣ ⇣↷ 
https://t.me/menhajselefiya123

                 ↷⇣ ⇣↷ 
https://t.me/menhajselefiya123