Get Mystery Box with random crypto!

~فَإِنِّى قَرِيبٌ (እኔ ቅርብ ነኝ፡፡) وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِى عَن | 💎🇸🇦🌹የሰለፊ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው

~فَإِنِّى قَرِيبٌ (እኔ ቅርብ ነኝ፡፡)

وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِى عَنِّى فَإِنِّى قَرِيبٌ ۖ أُجِيبُ دَعْوَةَ ٱلدَّاعِ إِذَا دَعَانِ ۖ فَلْيَسْتَجِيبُوا۟ لِى وَلْيُؤْمِنُوا۟ بِى لَعَلَّهُمْ يَرْشُدُونَ

ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው)፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፡፡ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በኔም ይመኑ፤ እነሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡ ( አል- በቀራህ : 186)

➷የአሏህ መልዕክተኛ ሰላምና እዝነት በሳቸው ላይ ይሁንና እንድህ አሉ፦ የተባረከውና የላቀው ጌታቹህ  (ህያው ና ለጋሽ)ነው።

ባሪያው እጆቹን አንስቶ የለመነው እንደሆነ
ባዶ እጆቹን ሊመልሰው ያፍራል!

  ➷
#የመልካሞች_ጥሪ! (١)

بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَـٰنِ الرَّحِيمِ
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ
በጣም አዛኝ በኾነው እጀምራለሁ።

➷ብለሀትም ሀይልም በአሏህ ቢሆንጂ የለም።
አንተን ብቻ እንገዛለን አንተንም ብቻ እርዳታን
እንለምናለን አንተን ብቻ እናመሰግንሀለን
ስለፈጠርከን፣ ሰለለገስከን፣ ቀናውን መንገድ
ስለመራከን፣ ስላሳወቅከን፣ ከጥሜት
ስለጠበቅከን፣ ኢማንን ስለለገስከን፣
ኢስላምን ስለመረጥክልን፣ቁረአንን ስላወረድክልን፣ቤተሰብን ጤናንና ፀጋን
ስለለገስከን፣ አሏህ ሆይ! ምስጋና ይገባህ!

ጠላትን የምትገታልን ሪዝቃችንን የምታሰፋልን
ደህንነታችንን የምት ጠብቅልን ከመነጣጣል ያደንከን በመልካም የፈወስከን  ለጥያቄዎቻችን ሁሉ መልስ የሰጠከን

#ጌታችን_አሏህ_ሆይ! ተደራራቢ ምስጋና
ይገባህ።

በግልፅም በድብቅም ለብቻም ይሁን
በህብረት  በሂወት ላሉት ለሌሉትም
በቅርቡም በሩቁም ላለ በኛ ላይ ለዋልክልን
ወዴፊትም ለምትውለው ፀጋህ ጌታችን አሏሆይ ምስጋና ይገባህ ምስጋናችንን እስክትወድልን ከወደድክልንም በኋላ ምስጋና
ይገባህ።

➷በነብያችን በቤተሰቦቻቸው አንድሁም በባልደረቦቻቸው ሰላምና እዝነትህ ይውረድ

           ↷⇣ ⇣↷

https://t.me/menhajselefiya123
https://t.me/menhajselefiya123