Get Mystery Box with random crypto!

ከሰለፎች የተገኙ የተክቢራ አይነቶች በነዚህ ውድ ቀናቶች ውስጥ ከሚፈፀ | 💎🇸🇦🌹የሰለፊ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው

ከሰለፎች የተገኙ የተክቢራ አይነቶች


በነዚህ ውድ ቀናቶች ውስጥ ከሚፈፀሙ ታላላቅ ኢባዳዎች ውስጥ አንዱ ተክቢራ ነው። አላህ በቁርአኑ መልእክተኛው በሀዲሳቸው ተክቢራ በማለት ላይ ከመጠቆምና ከማመላከት ውጪ ይህን ተክቢራ ይበል በሚል የመጣ የተክቢራ አይነት የለም። ስለዚህ አንድ ሰው በየትኛውም አላህ ማላቂያ ተክቢራ ማድረግ ይችላል። ነገር ግን ከቀደምት የዲን ሊቃውንቶች ከሰለፎቻችን የተገኙ የተክቢራ አይነቶች አሉ። እነሱን መጠቀም ግን የተሻለ ይሆናል። ከነዚህ ተክቢራዎች መካከል፦

①) አንደኛ
«الله أكبر، الله أكبر، لاإله إلا الله، والله أكبر، الله أكبر ، ولله الحمد»
ኡመር፣ አልይ፣ ኢብኑ መስኡድ፣ አቡሀኒፋ፣ ሰውርይ፣ ኢስሀቅ፣ ኢብኑ ተይምያ፣ ኢብኑ ረጀብ ሸኽ አልባንይና ኢብኑ ኡሰይሚን ይህንን መርጠዋል።
*ـ•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•ـ​*

②) ሁለተኛ
«الله أكبر كبيرًا، الله أكبر كبيرًا، الله أكبر وأجل، الله أكبر ولله الحمد»
ከኢብኑ አባስ ተወርቷል። ኢብኑ አቢሸይባ መርጦታል። አልባንይ ሶሂህ ነው ብለውታል
*ـ•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•ـ​*

③) ሶሰተኛ
«الله أكبر كبيرًا، والحمد لله كثيرًا، وسبحان الله بكرة وأصيلا»
ኢማሙ ሻፍእይና ኢማሙ ነወውይ መርጠውታል።
*ـ•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•ـ​*

④) አራተኛ
«الله أكبر، الله أكبر، الله أكبر، لا إله إلا الله، والله أكبر، ولله الحمد»
ከኢብኑ አባስ ተወርቷል።
*ـ•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•ـ​*

⑤) አምስተኛ
«لا إله إلا الله، والله أكبر، الله أكبر، ولله الحمد".»
ኡመርና ኢብኑ መስኡድ ብለውታል።
*ـ•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•ـ​*

⑥) ስድስተኛ
«الله أكبر، الله أكبر، الله أكبر»
ከኢብኑ አባስ፣ ከኢማሙ ማሊክና ሻፍእይ ተወስቷል።
*ـ•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•ـ​*

⑦) ሰባተኛ
«الله أكبر، الله أكبر، الله أكبر كبيرًا ".*»
ከሱፍያን ተወርቷል። ኢብኑ ሀጀር መርጦታል።
*ـ•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•ـ​*

⑧) ስምንተኛ
«الله أكبر، الله أكبر، الله أكبر، ولله الحمد، الله أكبر وأجل، الله أكبر على ما هدانا»
ከኢብኑ አባስ ተወርቷል። አልባንይ ሶሂህ ነው ብለውታል።
*ـ•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•ـ​*

በተገኘ አጋጣሚ እየቀያየርን በሆነ ጊዜ አንዱ በሌላ ጊዜ ሌላውን መጠቀም እንችላለን።http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

https://t.me/menhajselefiya123