Get Mystery Box with random crypto!

መምህር አካለወልድ

የቴሌግራም ቻናል አርማ memiheraka — መምህር አካለወልድ
የቴሌግራም ቻናል አርማ memiheraka — መምህር አካለወልድ
የሰርጥ አድራሻ: @memiheraka
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.40K
የሰርጥ መግለጫ

የመምህር አካለወልድ ONLINE

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-07-10 19:49:02 Dear visual basic application project participants the voting system end tomorrow morning 2:30 local time good luck !
1.2K viewsመለዓከገነት, 16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 19:47:32
ትኩረት
ለትምህርት ቤታችን ተማሪዎች በሙሉ
የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በበርካታ ቀውሶች ውስጥ የታጀበ ሁኖ ወደ ማጠቃለያ ምዕራፍ የደረሰ ቢሆንም መምህር አካለ ወልድ በጠንካራ መምህራኖች እና ተማሪ ወላጆች ወኔ የገጠመንን መሠረታዊ ችግር በመቋቋም ማንኛውም የመማር ማስተማር ስራ ያለ አንዳች እንከን እስከ መጨረሻው የትምህርት ጊዜ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ማግኘት ያለባቸው እውቀት ያለመሰሰት ሲተገበር የቆየ ሲሆን ቀሪ ሁለት ሳምንት ያለምንም የትምህርት ጊዜ ብክነት የሚተገበሩ ሲሆን ሁሉም የትምህርት ቤቱ ተማሪዎችን በመደበኛ የትምህርት ሰአት በመማሪያ ክፍል እና በትርፍ ሰአት ደግሞ በትምህርት ቤቱ ቤተ መፅሐፍት በቂ ዝግጅት እንድታደርጉ ትምህርት ቤቱ ያሳስባል ።
መምህር አካለ ወልድ ትምህርት ቤት
1.2K viewsAndargie Afrie, 16:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 19:37:18 ጥሩ የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎችን ለውጤት የሚያበቁ 10 ወሳኝ ክህሎቶች


ከታች በአጭሩ የተዘረዘሩት 10 ክህሎቶች ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች በትምህርታቸውና በቀጣይ ህይወታቸው ላይ ስኬትን እንዲጎናፀፉ የሚረዱ የህይወት ክህሎቶች ናቸው፡፡ በቀጣይም በኮሌጅ በሚኖራቸው ህይወት አላስፈላጊ ከሆነ ግራ መጋባት ይታደጓቸዋል፡፡ እነዚህ ክህሎቶች እንደማንኛውም ክህሎት ራስን በማስገዛትና ደጋግሞ በመሞከር ከራስ ጋ ማዋኃድ ይቻላል፡፡
ክህሎት #1 – የጊዜ አጠቃቀም ክህሎት
ማንኛውም ሰው በእያንዳንዱ ቀን ውስጥ 24 ሰዓታት አሉት፡፡ በነዚህ 24 ሰዓታት ውስጥ የምንሰራቸው ስራዎች ታዲያ አንዳችን ከሌላችን የተለየን እንድንሆን ያደርጉናል፡፡ አንድ የሀይ-ስኩል ተማሪ በአማካይ በሳምንት 35 ሰዓታትን በትምህርት ገበታ ላይ ያሳልፋል፡፡ በተቃራኒው የኮሌጅ ተማሪ ከ20-25 ሰዓታትን ብቻ በሳምንት በትምህርት ያሳልፋል፡፡ ስለሆነም አሁን ሀይ-ስኩል እያለ ጊዜውን በአግባቡ፤ በፕሮግራም መጠቀም የቻለ ተማሪ ኮሌጅ ገብቶ የሚኖረውን ተጨማሪ 15-20 ሰዓት ማስተዳደር አይከብደውም፡፡ በተቃራኒው ሀይ-ስኩል ላይ ያለ ፕሮግራም መኖርን የለመደ ተማሪ ኮሌጅ ሲገባ የሚኖረውን የተንጣለለ ጊዜ በሚያጓጉ ግን አላስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ሊያባክነው ይችላል፡፡
ጊዜን በአግባቡ ለመጠቀም ያስችል ዘንድ የእለት ዕቅድ ማውጫ ደብተር/አጀንዳ በማዘጋጀት እያንዳንዷን ቀን ፕሮግራም በማድረግ መጠቀም ብልህነት ነው፡
ክህሎት #2 – በቋሚነት የማጥናት ክህሎት
በቋሚነት የማጥናት ልማድ ያለው ተማሪ በፈተና ወቅት አይጨናነቅም፡፡ ይህ ክህሎት ካላችሁ በጣም ጥሩ…ከሌላችሁም አሁን ጀምራችሁ የዚህ ወሳኝ ክህሎት ባለቤት መሆን ይቻላል፡፡
ይህ ክህሎት ያላቸው ተማሪዎች
• ሁሌም የክፍል ትምህርቶቻቸውን ገብተው ይከታተላሉ (አይፎርፉም)
• የቤት ስራዎቻቸውን በእለቱ እና በአግባቡ ተከታትለው ይሰራሉ
• የየእለቱን ትምህርት በየቀኑ ቢያንስ አንድ ጊዜ በጥሞና ያነባሉ/ያጠናሉ

ክህሎት #3 – ተጨባጭ እቅድ የማቀድ ክህሎት
ይህንን ክህሎት ለማዳበር የራስን አቅም መፈተሽና ራስን ጠንቅቆ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ማንኛውንም እቅድ ከማቀዳችን በፊት በትክክል ያቀድነውን ለመፈፀም የሚያስችል የጊዜና የሁኔታ ግብአቶች እንዳሉን እርግጠኛ መሆን አለብን፡፡ ከአቅማችን በላይ የምናቅድ ከሆነ ጭራሹኑ ተዳክመን እንዳንቀር በአቅማችን ልክ ማቀድ አለብን፡፡
ክህሎት #4 – የጥሞና ክህሎት
ይህ በተለይ ለሀይ-ስኩል ተማሪዎች ከባድ ነው፡፡ በተለይ ዘመኑ በቴክኖሎጂ በተጥለቀለቀበት በዚህ ጊዜ፡፡ ሆኖም ይህ ክህሎት ያላቸው ልጆች ከትምህርታቸው ባሻገር ያሉ ሌሎች ስኬቶችንም ደራረበው ይቀዳጃሉ፡፡
ይህንን ክህሎት ለማዳበር አንዱና ዋነኛው መንገድ በክፍል ትምህርት ጊዜ አስተማሪውን በሚገባ ማዳመጥ ነው፡፡ የጥሞና ክህሎት ያለው ተማሪ አስተማሪዎቹ የሚያስተምሩትን ትምህርት በሚገባ የሚረዳ ሲሆን ካልገባው ደግሞ ይጠይቃል፡፡ አስተማሪው ሲያስተምር ያልገባው፤ አልገባኝም ብሎም ጥያቄም የማይጠይቅ ተማሪ ግን ሀሳቡ በሌሎች ጉዳዮች ቶሎ ይሰረቃል፡፡ በቀጣይ ውጤቱም ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል፡፡
ክህሎት #5 – አሪፍ ኖት የመያዝ ክህሎት
አንድ አስተማሪ በክፍል ውስጥ ሲያስተምር በደቂቃ በአማካይ ከ150-200 ቃላትን ያወራል፡፡ ይህን ሁሉ ተከታትሎ መፃፍ አድካሚ ብቻ ሳይሆን የማይቻል ነው፡፡ ጠቃሚ የሆኑትን መርጦ መፃፍ ደግሞ ልምምድ የሚፈልግ ግን ለተማሪው ስኬት ወሳኝ የሆነ ክህሎት ነው፡፡
የኖት አያያዝ ብቃትህን ለመለካት ባለፈው አመት የተፈተንካቸውን ፈተናዎች ይዘህ ጥያቄዎቹን ደብተርህ ላይ ካሉት ኖቶች ጋር አመሳክር፡፡ ጥሩ ኖት የመያዝ ክህሎት ካለህ አብዛኛዎቹ ጥያቄዎችና መልሶቻቸውን ደብተርህ ላይ ታገኛቸዋለህ፡፡ ካልሆነ ግን ለቀጣይ አመት ይህን ክህሎት ለማዳበር ራስን ማዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡ ሆኖም ግን የተማሪ ዋነኛ አላማው እውቀትን ገብይቶ ፈተናዎችን ማለፍ በመሆኑ ይህን ክህሎት እስክታዳብር ጥሩ ኖት ከሚይዙ የክፍል ጓደኞችህ ደብተር እየተዋስክ ማጥናትና ማለፍ ግድ ይላል፡፡
ክህሎት #6 – የቤት ስራን በወቅቱ የመስራት ክህሎት
መምህራን የቤት ስራን የሚሰጡት በምክንያት ነው፡፡ የቤት ስራዎችህን በአግባቡና በወቅቱ መስራት በትምህርት ጉዳዮች ላይ በራስ መተማመንህን የሚጨምሩልህ ሲሆን በተጨማሪም አስፈላጊ የሆነውን እውቀት በቀላሉ በአዕምሮህ ተቀርፆ እንዲቀር ያግዝኃል፡፡
ክህሎት #7 – በየእለቱ የማንበብ ክህሎት
የየእለቱን ትምህርት ለማንበብ የግድ ፈተና እስኪደርስ መጠበቅ ሞኝነት ነው፡፡ በየእለቱ የተማርከውን ሳይረሳህ በፊት በቀን ቢያንስ አንድ ጊዜ ገረፍ ገረፍ ማድረግን እንደ ልምድ ካዳበርከው በፈተና ሰሞን የሚኖርብህን መጨናነቅ ያስቀርልኃል፡፡ በተጨማሪም በክፍል ውስጥ ሰምተኸው ያልፃፍከው ነገር ካለ ኖቶችህን እንድታደራጅና ሙሉ መረጃ እንዲኖርህ ያግዝኃል፡፡
ክህሎት #8 – ራስን የማደራጀት ክህሎት
ይህ ክህሎት ከትምህርትም ባሻገር በሌላው የህይወት ክፍል ላይ ተፅእኖ አለው፡፡ የዚህ ክህሎት ባለቤቶች የትምህርት መማሪያ ደብተሮቻቸው፤ መፅሀፍቶቻቸው፤ እርሳስና እስክርቢቷቸው በስነስርአት በአንድ ቦታ ተደራጅተው ይገኛሉ፡፡ ከትምህርት ቤት ወደቤት ሲመጡ ዩኒፎርማቸውን በስርአት አጣጥፈው ያስቀምጣሉ ጠዋት ሲወጡም ያስቀመጡት እቃ ባለበት ሳይተራመስ ይጠብቃቸዋል፡፡
ክህሎት #9 – ራስን የማነቃቃት ክህሎት
ትምህርትን በደንብ ለመከታተልና ብሎም ጥሩ ውጤት ለማምጣት ውስጣዊ መነቃቃት ወሳኝ ስነልቦናዊ ፋይዳ አለው፡፡ ትምህርቱን ወይም አስተማሪውን ባንወደውም እንኳ ተሸንፈን ላለመቅረት ያለ የሌለ ኃይላችንን አሰባስበን ራሳችንን አነቃቅተን መግፋት አለብን፡፡ ይህንን ክህሎት በትምህርት ቤት ማዳበር ከቻልን በቀጣይ ህይወታችን ብዙ የህይወት ችግሮችን ማሸነፍ እንችላለን፡፡
ክህሎት #10 – ጀምሮ የመጨረስ ክህሎት
አንድን ነገር ከጀመርን በኋላ አለመጨረስ በሂደት የተሸናፊነት መንፈስ በውስጣችን እንዲዳብር ያደርጋል፡፡ ስለሆነም የማሸነፍ ስነልቦናችን እንዲዳብርና በራስ መተማመናችን እንዲጎለብት ጀምሮ የመጨረስን ክህሎት ልናዳብር ይገባል፡፡ ትምህርት ለዚህ ክህሎት መዳበር ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ ትምህርት አንዴ ከጀመርነው ወደድንም ጠላንም መጨረስ ግድ ይላል፡፡ አለበለዚያ ግን የዘመናት ልፋታችን መና የሚቀር ይሆናል፡፡ እንደምንጨርሰው እርግጠኛ ከሆንን ደግሞ በተቻለን መጠን በጥሩ ውጤት ለመጨረስ መጣር ያስፈልጋል፡፡ የወላጆችን ገንዘብና የራሳችንን ጊዜ ማጥፋታችን ካልቀረ አቅማችን በፈቀደልን ልክ ጥሩ ውጤት አምጥተን ለመጨረስ መስራት ያስፈልጋል፡፡
953 viewsAndargie Afrie, 16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 16:34:31 I think no 6 is the better one
1.2K viewsABBITTY, 13:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ