2022-09-18 20:15:07
የ 2014 የስፖርት ዞን ሽልማት በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የስፖርት ዞን የታሪክ አሻጋሪ የሆኑ ግለሰቦችን እውቅና ሲሰጥ ስድስት ግለሰቦችን ተሸላሚዎች አድርጓል።
በዚህም መሰረት :-
በሽልማት ስነ-ስርዓቱ ላይ የባህል እና ስፖርት ሚንስተር አቶ መስፍን ቸርነት ፣ የፌዴሬሽን ዋና ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ጨምሮ የስፖርቱ ቤተሰቦች በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።
በመጀመሪያው የሽልማት ስነ-ስርዓት የአፍሪካን የነፃነት እግር ኳስ ያጀቡ አፓርታይድን በስፖርቱ የተዋጉት ክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ የታሪክ አሻጋሪ ሽልማት ሲያሸንፉ ልጃቸው አማካኝነት በስፍራው ተረክቧል።
ከዚህ ባለፈም ከሐዋሳ ከተማ ጋር የመጀመሪያውን የሊግ ዋንጫ ያሳኩት እና በብሔራዊ ቡድን በረዳት አሰልጣኝነት የሰሩት አሰልጣኝ ከማል አህመድ ሌላኛው የታሪክ አሻጋሪ ተሸላሚ ሆነዋል።
ሶስተኛው የታሪክ አሻጋሪ ተሸላሚ የሆኑት በአትሌቲክሱ ዘርፍ እንደ ሀይለ ገ/ስላሴ ፣ ደራርቱ ቱሉ እና ብርሀኔ ሀደሬ የመሳሰሉ ሯጮችን ለሀገሪቱ ያበረከቱት ዶ/ር ወልደ መስቀል ኮስትሬ ተሸልመዋል።
ዶ/ር ወልደ መስቀል ኮስትሬ ሀገራቸውን በአምስት ኦሎምፒክ ሲመሩ ሀያ ስምንት ሜዳሊያዎችን ሲያስገኙ የስፖርት ዞን የታሪክ አሻጋሪ ተሸላሚ ሲሆኑ በህይወት ባይኖሩም ልጃቸው ያቆብ ኮስትሬ በስፍራው የአባቱን ሽልማት ተረክቧል።
በአራተኛ የታሪክ አሻጋሪ ሽልማት አሸናፊ ዘርፍ ጋዜጠኛ እና የእግር ኳስ ታሪኮችን ሰንዶ ያዘጋጀው ገነነ መኩሪያ ተሸላሚ ሆኗል።
በአምስተኛው የታሪክ አሻጋሪ የህይወት ዘመን ሽልማት በአትኬቲክሱ ዘርፍ በኦሎምፒኩ የሀገሩን ባንዲራ ያውለበለበው ምርፅ ይፍጠር ሲሸለም ልጁ ቢንያም ምርፅ በስፍራው በመገኘት ሽልማቱን ወስዷል።
2.4K viewsKidus, 17:15