Get Mystery Box with random crypto!

'አባቴ ስንት አመት ላልቅስ? ዋንጫውን እፈልጋለሁ' ከሜሲ ልጅ ቲያጎ የተጻፈ ደብዳቤ የ10 አመቱ | ስፖርት ዞን sport zone

"አባቴ ስንት አመት ላልቅስ? ዋንጫውን እፈልጋለሁ" ከሜሲ ልጅ ቲያጎ የተጻፈ ደብዳቤ

የ10 አመቱ የሜሲ ልጅ ቲያጎ ከፍጻሜው ጨዋታ አንድ ቀን በፊት ይህን ደብዳቤ ለአባቱ ለሊዮ ጽፎ ነበር።
እናቱ አንቶኔላ ደብዳቤውን በማህበራዊ ድረገጾች ይፋ አድርጋው ነበር።

ቲያጎ "የተወለድኩት ከዲዬጎ ማራዶና፣ ሊዮኔል ሜሲ እና ማልቪኖች ምድር ነው (ማልቪኖች = እንግሊዞች በፎክላንድ ደሴቶች ባደረጉት የ74 ቀናት ጦርነት ህይወታቸውን ለአርጀንቲና የሰው 649 የአርጀንቲና ጦረኞችን ለማለት ነው)"

"የተወለድኩት መቼም ከማልዘነጋት የዲዬጎ ማራዶና፣ ሊዮኔል ሜሲ እና የማልቪኖች ምድር ነው!

ብዙ ልነግርህ አልችልም፤ ምክንያቱም የውስጥ ስሜቴን ስለማይገልጽልኝ። ብዙ ግዜ አልቅሻለሁ

ማራካኛ ላይ ብራዚልን በኮፓ አሜሪካው አሸነፋችሁልንና እንባዬ ቆመ

አሁን ደግሞ ሌላ ተስፋ ሰጥታችሁናል፥ ይኼን ዋንጫ ለ3ኛ ግዜ አገሬ እንድታነሳ እፈልጋለሁ! የአለም ሻምፒዮን እንድንሆን እፈልጋለሁ። ዲዬጎ ማራዶና፣ ዶን ዲዬጎ እና ላ ቶታ (ዶን ዲዬጎ እና ላ ቶታ በህይወት የሌሉ የዲዬጎ ቤተሰቦች ናቸው) ከገነት ሆነው፥ ሊዮኔል እያሉ በደስታ አንተን ሲደግፉ ማዬት እፈልጋለሁ"

ሌላው በህይወት ያለው የአርጀንቲና ማልቪን - ሊዮኔል ሜሲ የልጁንም፣ የአርጀንቲናንም ጥያቄ ዛሬ መልሷል

የቲያጎ እንባ ቆሟል! ከሮዛሪዮ እስከ ቡዌኖስ አይረስ አንገታቸው ቀጥ ብሏል። ዲዬጎ፣ ዶን ዲዬጎና ላ ቶታም በገነት ደስታቸው ይሆናል