Get Mystery Box with random crypto!

የአለም ዋግጫዉ ኮከብ ጎል አግቢ ማን ይሆን ? በኳታር አዘጋጅነት እየተደረገ የሚገኘዉ የአለም ዋ | ስፖርት ዞን sport zone

የአለም ዋግጫዉ ኮከብ ጎል አግቢ ማን ይሆን ?

በኳታር አዘጋጅነት እየተደረገ የሚገኘዉ የአለም ዋንጫ ሊጠናቀቅ ሁለት ቀናት ብቻ የቀሩት ሲሆን በፍፃሜዉ ፈረንሳይ ከ አርጀንቲና የሚያደርጉት ጨዋታ በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል።

ከፍፃሜዉ ጨዋታ ጎን ለጎን ደግሞ የአለም ዋንጫዉ ኮከብ ጎል አግቢ ሆኖ ማን እንደሚጨርስ ገና ያልተረጋገጠ ሲሆን የኮከብ ጎል አግቢነቱን እየመሩ የሚገኙት የሁለቱ የፍፃሜ ተፋላሚ ሀገራት የፊት መስመር ተጫዋቾች ናቸዉ።

አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል አንድሬስ ሜሲ እና ፈረንሳያዊዉ ወጣት ኪሊያን ምባፔ እያንዳንዳቸዉ አምስት አምስት ጎሎችን በማስቆጠር የመጀመሪያ ደረጃን የያዙ ሲሆን ጁሊያን አልቫሬዝ እና ኦሊቪየር ጅሩድ አራት አራት ጎሎችን በማስቆጠር የኮከብ ጎል አግቢነት ደረጃዉን ይዘዉ ይገኛሉ።

ማን የሚያሸንፍ ይመስላችኋል?