Get Mystery Box with random crypto!

በመጅሊሱ መተዳደሪያ ደንብ ላይ ለመወያየት በዚህ 2 ቀን በስካይ ላይት ሆቴል ሲደረግ የነበረው ስብ | MEHUBA TUBE

በመጅሊሱ መተዳደሪያ ደንብ ላይ ለመወያየት በዚህ 2 ቀን በስካይ ላይት ሆቴል ሲደረግ የነበረው ስብሰባ ዛሬ ተጠናቋል። በዚህ ስብሰባ ተሳታፊ የነበሩ የነባሩ እስልምና (ሱፊ አሽዓሪይ ማቱሪዲይ) ወኪሎች በፍፁም የሀሳብ የበላይነት ስበሰባውን በማጠናቀቅ ዑለማ መምራት አይችልም መጅሊሱ የዑለማ ማህበር አይደለም ሲል የነበረው የወሃቢይ ቡድንን በመርታት ዑለማ ይመሩናል ወደ ሚል አቋም የወሃቢያው ቡድንን እንዲመጡ በማድረግ የዛሬው ስብሰባ ማሳረጊያ ላይ ወሃቢያ ዑለማ ይመራል የሚለውን ሃሳብ ተቀብለው ወጥተዋል።

እንዲሁም መጅሊሱ የአህሉሱና በመሆኑ አህሉሱና ማነው ሲባል አሽዓሪይ ማቱሪዲይ መሆኑን አምነው ሌላውንም ያካትታል ወደሚል የተሸናፊነት ስሜት ወርደው አህለሱና እኛ ነን ብሎ የሚናገር አንድ እንኳ የወሃቢይ ተወካይ ማግኘት ሳይቻል ቀርቷል።

25 ዑለማ ሰነዱን ማፅደቅ አይችልም እና ይችላል የሚል ተቃራኒ ሃሳቦች ተነስተው የዛሬውን ውሎ ረጅም ሰአት ፈጅተው ያለምንም ስምምነት ወሃቢያ25 ዑለማ ሰነዱን ያፀድቃል ሲል ነባሩ ሙስሊም 25 ዑለማ ማፅደቅ አይችልም ዑለማው ተሰብስቦ ነው ማፅደቅ ያለበት በሚል ተጠናቋል። 25 ዑለማ ሰነዱን የማፅደቅ ህጋዊም ሆነ ህዝባዊ መሰረት እንደሌላቸው በአፅንኦት ተነግሯል። ነገ 25 ዑለማ ሰነዱን ያፀድቃል የሚለው የተለመደው የወሃቢይ ማደናገሪያ ዜና ነው። 25 ዑለማ መጋቢት 17 ጀምሮ ባደረጉት ስብሰባ ሰነዱ በማን እንደሚፀድቅ ስምምነት ላይ ሳይደርሱ እንደተቋጨ ትላንት ከተነበበው 26 ገፅ የስብሰባቸው ቃለጉባኤ መረዳት ተችሏል። ስለዚህ 25 ዑለማ ሰነዱን የማፅደቅ ምንም አይነት መብት የላቸውም የሚለው ህጋዊና ሥርአትን የሚያስጠብቅ አካሄድ ነው።

የነባሩ እስልምና ወኪሎች በሚገርም ጨዋነትና በፍፁም የሃሳብ የበላይነት አጠናቀው ወጥተዋል።