Get Mystery Box with random crypto!

ሌሊቱ ሰክኖ ጨረቃ በክዋክብት ተሽሞንሙኖ ጭርታው ሰፍኖ ባለበት ሁኔታ ቅፅበታዊውን ክስተት ጂብሪል | Mebruk muhammed @official

ሌሊቱ ሰክኖ ጨረቃ በክዋክብት ተሽሞንሙኖ ጭርታው ሰፍኖ ባለበት ሁኔታ ቅፅበታዊውን ክስተት ጂብሪል ዐ.ሰ ረሱልን ሰ.0.ወ አባንኖ በቡራቅ ተፈናጥጠው ወደ ላይኛው ግዛት ተሳፈሩ።
በሰባቱም ሰማይ የበር ዘቦች የሰይዲን የማርረግ ጉዞ አውቀው በጉጉት እየጠበቁ ነበር። ለሰይዳችንሰ.0.ወ በር ከመክፈት የበለጠ ምን ዕድል አልለ?። የመለኮች አለቃ ጂብሪል 0.ሰ አስከ አቅሙ ከንፎ ወራጅ ቢል ሰይዳችን ሰ.0.ወ የክብሩን መንገድ በነጠላ የእቀዘፉ ከአርሽ ደረሱ።
ጫማቸውን ሲያወልቁ ጀሊሉ ለምን አላቸው። ሙሳ አንተን ሊያወጋ ወደ ጡር ሲደርስ ጫማውን ስላወለቀ ነው አሉት። አልላህም እንዲህ አለ ፦ ሙሳ ማንነው አንተ ማንነህ ሙሳ እሱ ጠይቆ ነው እኔ ጋር የመጣው አንተ ግን እኔ ጠይቄህ ነው የመጣኸው፣ሙሳ እሱ ፈልጎ ነው የመጣው አንተ ግን እኔ ፈልጌህ ነው የመጣኸው፣ሙሳ እሱ ወዶ ነው የመጣው አንተ ግን እኔ ወድጄ ነው ያመጣውክ አላቸው ከነጫማቸው ወጡ ቀጠለና ትለገሳለህ ጠይቅ አላቸው እሳቸውም ፋጢማን አደራ፣አኢሻን አደራ፣ኸዲጃን አደራ አላሉም ኡመቲቲቲ (በምንም ሁኔታ ትዝየምንላቸው እኛን) አሉ አላህም አንተ የቂያም ቀን ኡመቲ ኡመቲ (ህዝቤ) ስትል እኔ ራህመቲ ራህመቲ (እዝነቴ) እላለሁ አላቸው