Get Mystery Box with random crypto!

' እርስ በእርስ የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ መቀያየር አይቻልም ' - ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት | Mekdela Amba University Registrar and Alumni Directorate Office

" እርስ በእርስ የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ መቀያየር አይቻልም " - ትምህርት ሚኒስቴር

የትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ማደረጉ ይታወቃል።

መደባውን ተከትሎ ከዚህ ቀደም እንደነበሩ ጊዜያት ሁሉ አንዳንድ አካላት " ተማሪዎችን እና ወላጆችን ገንዘብ ክፈሉ ምደባ እናስተካክላለን ፣ ወደ ፈለጋችሁበት እንድትመደቡ እናደርጋለን " በሚል የማጭበርበር እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው።

በሌላ በኩል አንዳንድ ተማሪዎች እና ወላጆች የዩኒቨርሲቲ እርስ በእርስ መቀያየር ይቻል እንደሆነ ጥያቄ አቅርበዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንዳሳወቀው ተማሪዎች ምደባን ተከትሎ ከማንኛውም ህገወጥ ድርጊት ላይ ከተሰማሩ አካላት እራሳቸውን እንዲጠብቁ ፤ ምደባ እንቀይራችኃለን የሚሉትም ሀሰተኞች መሆናቸው እንዲሁም እርስ በእርስ ምደባ መቀያየር የሚባል ነገር እንደሌለ አስገንዝቧል።

በዚሁ አጋጣሚ ዩኒቨርሲቲዎች በአጭር ጊዜ ተማሪዎችን እንዲጠሩ አቅጣጫ በመቀመጡ ተማሪዎች እና ወላጆች አስፈላጊውን ዝግጅት ታደርጉ ዘንድ መልዕክት እናስተላልፋለን።

@tikvahethiopia