Get Mystery Box with random crypto!

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፣ # ለመረጃ_ያህል 1.ግቢው ሁለት ካምፓ | Mekdela Amba University Registrar and Alumni Directorate Office

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፣ # ለመረጃ_ያህል
1.ግቢው ሁለት ካምፓስ ያለው ሲሆን ዋናው ግቢ ቱሉአውሊያ(Natural Science campus) እና ሁለተኛው መካነ ሠላም(Social Science campus) ናቸው።

2. መንገድን በተመለከተ
# ለዋናው_ግቢ

#ከአዲስ አበባ እና በአዲስ አበባ ለምትመጡ
ከ #አዲስ_አበባ አቀስታ በሚለው ከ ላምበረት መናኸርያ ተነስታችሁ መምጣት ትችላላችሁ( 478 KM- ምሽት 12:00-12:45 በ #TATA BUS ትደርሳላችሁ)
ወይም ደግሞ መጀመሪያ ወደ ደሴ(400KM) ትመጡና (በተለይ ለዘመናዊ ባስ ተጠቃሚዎችና ከ አዲስ አበባ ወደዚህ ማለትም ደብረ ብርሃን፣ ሸኖ፣ ደብረ ሲና፣ሸዋሮቢት,,,,,,መስመር ላላችሁ) ከዚያ ወደ ግቢው (78KM) ከደሴ መናኸሪያ ጊምባ(ቱሉ አዉሊያ) በሚል ሚኒባስ መምጣት ትችላላችሁ

#ከባህዳር እና በባህርዳር መስመር የምትመጡ ተማሪዎች ከባህርዳር ወደ መካነ ሠላም(Social Science campus) ከዚያ ቀጥላችሁ ናቹራል ግቢ(ከባህዳር - መካነ ሠላም 281 km)
(መካነ ሠላም-ቱሉ አውሊያ(natural Science campus) 100 km )

#በጎንደር እና ከጎንደር የምትመጡ ሁለት አማራጭ አላችሁ
1- ጎንደር-ባህርዳር-መካነ ሠላም-ቱሉአውሊያ
2-ጎንደር-ደሴ-ቱሉ አውሊያ(ጎንደር-ደሴ 510 km) እና (ደሴ-ቱሉአውሊያ 78km) በ ወረታ,ወልድያ, መስመር ላላችሁ ይሄን ተጠቀሙ
የመጀመሪያው ግን ይመረጣል!
2.ወደ ሶሻል ግቢ:-

ከአዲስ_አበባና በአዲስ አበባ የምትመጡ ከአዲስ መካነ ሠላም ብላችሁ መሳፈር ትችላላችሁ(9:00 ትደርሳላችሁ)

#ከባህርዳር መስመር የምትመጡ ከ ባህርዳር ተነስታችሁ በ ሞጣ፣መርጡ ለማርያም፣ መካነ ሰላም ትደርሳላችሁ።
3. በ ዋናው ግቢ(Natural Science) የሚሠጡ ዲፓርትመንቶች
COLLEGE OF NATURALAND COMPUTATIONAL SCIENCE (Bsc)
#Computer science
#Physics
#Biology
#Chemistry
#Maths
#Geoogy
#Statistics

COLLEGE OF AGRICULTUREAND NATURAL RESOURCE

#Natural Resource Management
#Agricultural economics
#Forestery
#Horticulture
#Animal science
#Plant Science
#Rural Development and Agricultural Extension


Social Science Mekane selam Campus

#Economics
#Management
#Marketing mgt
#Accounting
#Geography
#History
#Amharic
#English language
*** ማሳሰቢያ

ከሶሻል ወደ ናቹራል ወይም ከናቹራል ወደ ሶሻል የሚደረግ ቅያሬ(ዝውውር) የለም።
ከዩኒቨርስቲ ዩኒቨርስቲ(እርስ በርስ) መቀያየር የሚባል ነገር የለም፣ አሳማኝ መረጃ ካለ ትምህርት ሚኒስቴር በመሄድ ማመልከትና መቀየር ይቻላል።
ለ ዓ.ም አዲስ የሚጨመሩ ዱፓርትመንቶች ይኖራሉ።

3.የአየር ሁኔታ

Natural science-Main Campus
ብርዳማ ስለሆነ ብርድልብስና ጃኬት የግድ ያስፈልጋል

Social Science Mekane selam campus
መካከለኛና ተስማሚ የአየር ፀባይ ስላለው ብርድንም ሙቀትንም ያማከሉ አልባሳት ያዙ::
ሁለቱም ካምፓላ ፍፁም ሰላማዊ የመማር ማስተማር የሚካሄድበትና ለተማሪዎች ጊዜያቸውን፣ጉልበታቸውን እውቀታቸውን የሚለግሱ መምህራን እና ሰራተኞች የሚገኙበት ዩኒቨርስቲ ነው::
ለማንኛውም ጥያቄ፣ጥቆማ፣አስቱታየት @aben21REG ላይ text ማድረግ ትችላላችሁ፣
#Mekdela_Amba_University_Registrar_office ይህን ቻናል ይቀላቀሉ https://t.me/MAUREG1