2022-02-05 08:09:19
The Golden political generation, Failed ?
በኦሮሞ ልሂቃን መካከል ንግግር ለማድረግ ሽርጉዱ ተጀምሯል።አንድ ሁለት ሶስቴ ውስጥ ለውስጥ ሙከራዎች መካሄዳቸውንና ይሄ ነው የሚባል የጎላ ነገር እንዳልተገኘ ቢታወቅም፤ ለቀጣዩ ግኔ እንደሚሳካ ተስፋ በማድረግ ከሁለት ዓመት በፊት በወቅቱ የነበረውን የኦሮሞ ልሂቃን ፍትጊያ ለማሳየት ሞክሬ ነበር፤ አሁን ሙሉ ለሙሉ የሀይል ሚዛኑ ተጠቃሎ የዶ/ር አብይ እጅ ላይ የገባ ቢሆንም ወደ ዃላ መለስ ብለን ስናስተውለው ግን አሁን የሆነው ሁሉ የሚሆን አይመስልም ነበር። ጊዜውን ማስታወስ ለሚሻ ቀጣዩን ጽሁፌን ያንብብ -)
...
የኦሮሞ ፖለቲካ በዚህ ዘመን የገጠመው አይነት የልሂቃን ስብስብ ገጥመውት የሚያውቅ አይመስለኝም ፈጽሞም። ይሄ 𝐎𝐫𝐨𝐦𝐨 𝐆𝐨𝐥𝐝𝐞𝐧 𝐏𝐨𝐥𝐢𝐭𝐢𝐜𝐚𝐥 𝐀𝐠𝐞 የሚባለው አይነት ነበር። ነገር ግን እርስ በርስ መስማማት አቅቷቸው በኢትዮጵያዊያን ሁሉ ድጋፍ ይዘው፤ ከስልሳዎቹ ትውልድ እስከ ቁቤ ጀነሬሽን የደረሰ፣ ከኦነግ መስራቾቹ ሌንጮ ለታ፣ ዶ/ር ሌንጮ ባቲ፣ ዳውድ ኢብሳ.... እስከ ጀነራል ከማል ገልቹ፤ ከዶ/ር መራራ ጉዲና እስከ ዶ/ር አብይ፣ ለማ መገርሳ፣ ጃዋር፣ ታከለ ኡማ የደረሰ የተለያየ የእድሜ የብቃት፣ የአተያይ፣ የተቀባይነት ደረጃ ያላቸው ልሂቃንን የያዘ ትውልድ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ የብሄሩን ፖለቲከኞች ይዞ ስልጣን ቢይዝም ቅሉ አብሮ በመስራት በመስማማተሰ ሊዘልቅ የቻለው ወራትን ብቻ ነው። ይሄ ስብስብ ቢጠቀምበት ከሀገር ውስጥ ድጋፍ አስከ ዓለም አቀፍ የኖቤል ሽልማት የያዘና በምዕራባዊያኑም መልካም ስምና ሙሉ ድጋፍ የያዘ ነበር።
እነዚህ የብሄሩ ልሂቃን የመጡበትን ብሄር ብሎም መላን የኢትዮጵያ ህዝቦችን በሙሉ እምነትና ድጋፍ ይዘው ሳሉ፤ በቅናት፣ በስልጣን ጥማት፣ በአካባቢያዊነት (ጎጥ) ፣ በመሳሰሉ ርካሽ አስተሳሰቦች ተራኩተው ለመጡበት ብሄር ለመላው ኢትዮጵያዊ የጸጥታና የሰላም ስጋት የሆኑበት ደረጃ ላይ ተደርሷል።
...
በዶ/ር አብይ እና በአቶ ለማ የሚመራው መንግስት ስልጣኑን እንደያዘ ሰሞን ያደረገው ነገር የኦሮሞም ይሁን የሌላ ብሄር ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ወደ ሀገር ቤት ማስገባትና ለተወሰኑት ስልጣን ማጋራትን ነበር የመጀመሪያው እርምጃው ያደረገው። የኦነጉን ጀነራል ከማል ገልቹን የኦሮሚያ ጸጥታና ደህንነት ሃላፊ፣ የኦነግ መስራቾቹን ዶ/ር ሌንጮ ባቲ እና አቶ ሌንጮ ለታ የጠ/ሚ አማካሪ፣ጃዋር ምሃመድንም ቢሆን ይሄ ነው ተብሎ በይፋ ያልተገለጸ ነገር ግን ሶስቱ በጋራ እየተመካከሩ እየሰሩ እንዳሉ የሰላሙ ሰሞን እራሱ ጃዋር እንደተናገረ ይታወስ፣ ሌሎች ብዙ የኦሮሞ ተቃዋሚ የነበሩ በክልሉም በፌደራልም ስልጣን ይዘው እንዲመሩ ተደረገ።
...
የመጀመሪያው ፍትጊያ በአቶ ዳውድ ኢብሳ በሚመራ ኦነግ እና በአቶ ለማ መገርሳ ከሚመራው የኦሮሚያ ክልል በዃላም ከፌደራል መንግስቱ ጋር ገጠመ። አቶ ዳውድ ታጣቂዎቻቸውን ማን ፈቺ ማን አስፈቺ ስሉ በአንድ ሀገር ሁለት የታጠቀ ሀይል እንደሚኖር በድፍረት ተናገሩ። እነሆ ወለጋ ላይ የመጀመሪያው መሳሪያ መማዘዝ በኦሮሞ መሪዎችና በኦሮሞ ተቃዋሚዎች ተጀመረ። በጊዜው ጃዋር አሰላለፉን ከነ ዶ/ር አብይ ጋር በማድረግ የአቶ ዳውድ ኢብሳን ዘገን ትጥቅ እንዲፈታ በህዝብ ፊት ያሳጣ በቃላትም ይጠዘጥዝ ነበር።
...
ሁለተኛው ልዩነት በዶ/ር አብይ እንዲሁም በለማ መገርሳ የሚመራ መንግስትና ስልጣን ሊያጋራ ከውጭ አስገብቶ የኦሮሚያ ክልል የጸጥታና ደህንነት ዘርፍ አላፊ ባደረጉት ጀነራል ከማል ገልቹ መካከል ሆነ። ጀነራል ከማል ገልቹ በተመሳሳይ ጊዜ በአቶ ዳውድ ኢብሳ ከሚመራው ኦነግ ጋር ሌላ ከባድ ጸብ ነበርው። እንደውም የአቶ ዳውድ ኦነግ በመንግስት ላይ ማቄም የጀመረው እንዴት እኛን ጥሎ የጀነራል ከማል ገልቹን እነግ አስጠጋ ከሚል ነው። ወደ ቀደመነገራችን ስንመለስ ጀነራል ከማል ገልቹ ለክልሉ ፕሬዘዳንት ለማ መገርሳ አልታዘዝ በማለት የራሱን መዋቅር በክልሉ ደህንነትና ፖሊስ ላይ መገንባት ጀመረ። አያያዙ አላምር ያለው የክልሉ ፕሬዘዳንት ለማ መገርሳ የኦዴፓ ስራ አስፈጻሚም ሆነ ማዕከላዊ ኮሚቴ ሳያውቅ በሁለት መስመር ደብዳቤና በራሱ ቲተርና ፊርማ ከስልጣኑ አባረረው። ጀነራል ከማል ገልቹ የወራት ያህል ቆይቶ በዃላም ተጣልቶ የወጣበትን የመንግስት ሚስጥር በየሚዲያ ይነዛው ጀመር።
..
ሶስተኛው በጃዋር ሞሃመድና በኦዴፓ ባለስልጣናት የጀመረ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ጋር የደረሰ ነበር። ጃዋር እነ ዶ/ር አለሙ ስሜን፣ እነ ታዬ ደንደአን... ወዘተ በአደባባይ ስም ሲያጠፋና ሲዘረጥጥ የተመለከቱ አስከትሎም ከዃላ በነ ጠቢባ ሀሰን በኩል ሊዘውራቸው እንደፈለገ የገባቸው ዋናዎቹ ዶ/ር አብይ እና ለማ መገርሳ የፊት ለፊት ጸብ ከጃዋር ጋር ገጠሙ። ሰንሰለቱን ለመበጣጠስ በሚል ወ/ሮ ጠቢባ ሀሰንና የመሳሰሉ የክልሉ ክፍተኛ ባለስልጣናትንና የከተማ አስተዳደሮች ከስልጣናቸው በማንሳት አየር ላይ አንሳፈፉ። ጃዋርም በሚዲያውና በጀሌዎቹ ታግዞ የስም ማጥፋት ዘመቻውን ተያያዘው። በኦዴፓ ውስጥ ያሉትንና አመራሮች በመጠቀም ጠ/ሚ ዶ/ር አብይን ከኦዴፓ ሊቀመንበርነት ለማንሳት የውስጥ ለውስጥ ቅስቀሳና ዘመቻ ጀመረ፤ ዶ/ር አብይን ከኦዴፓ ሊቀመንበርነት ጨፌ ኦሮሚያ ካስነሳው ኢሚዲየትሊ ከጠ/ሚስትርነቱም ይነሳል። የተሰራው ፎርሙላ ይህ ነበር። ዶ/ር አብይ በበኩሉ ድምጹን አጥፍቶ ውስጥ ለውስጥ እንዴት እንደሰራው በማይታወቅ ሁኔታ 8 የክልል ፓርቲዎቹን አፍርሶና አዋህዶ ፓርቲውን መስርቶ የፓርቲው ሊቀመንበር ሆኖ ቁጭ አለ። ጨፌ ላይ የታሰበው ሴራ ላያንሰራራ ተመታ። ዶ/ር አብይ በጣም ጥቂቶች ኢትዮጵያዊም በታሪኳ አግኝታ የማታውቀውን የአለም የኔቤል ሽልማት በማድረግ በአለማ አቀፍ ደረጃ ስሙንያ ክብሩን አሳድጎ ቁጭ አለ።
...
አራተኛ ዶ/ር አብይ 8 ፓርቲዎቹን አስተባብሮ የራሱን ፓርቲ መመስረቻው ጫፍ ላይ ተሰሚነቴ ቀነሰ ሁሉም ዶ/ር አብይን ብቻ ነው የሚሰሙት... የተከዳሁ አይነት ስሜት የያዘው ለማ መገርሳ በውሰሰጡ የያዘውን ቁጣ ይዞ ወደሚዲያ ወጣ። የለማና የዶ/ር አብይ የረጅም አመት የትግል አጋርነት በወንበር ምክንያት ታላቅ ስንጥቅ ገጠመው።
....
አምስተኛ ዶ/ር አብይን ለመጣል በዘመነ ወያኔ በስደት ኤርትራ በረሃ እርስበርሳቸው መስማማት አቅቷቸው የወለጋና የአርሲ ፥ ሌላ ጊዜ የባሌ የሀርርጌ እያሉ ሲጨፋጨፉ የነበሩ ቡድኖች ተስማምተው ከአንድም ሶስት አራት ተማማሉ ተፈራረሙ። በወራት ስምምነቱ ፈርሶ እርስ በርሳቸው ወደፊት በሚኖረው የስልጣን ድልድል መጠዛጠዝ ጀመሩ።
...
አሁን ያለው ሁኔታ።
አሁን ከአንድ ማህበረሰብ ወጥተው ስልጣን ይዘው ሙሉ የህዝብ ድጋፍ ኖሯቸው በተረጋጋ ሁኔታ ሀገር መምራት ያልቻሉበት ደረጃ ደርሰዋል። ለዚህ ተጠያቂ ደግሞ እራሳቸው የኦሮሞ ተቃዋሚ ልሂቃንና ፖለቲከኞች እንጂ ሌላ ማንም አይሆንም። በቅናትና ዘለፋ የተጀመረው መነታረክ ወደ ግድያና ጦር ማማዘዝ ሄዶ የመንግስት ባለስልጣናቶች በገዳይ እስኳዶች እየታደኑ የሚገደሉበት፤ በሴራ ታዋቂ ገሰለሰቦች አርቲስቶች ሳይቀር ተገድለው ሀገር ለማፍረስ እርስ በርስ ለመጫረስ የተቻለውን ሁሉ ማድረግ ደረጃ ላይ ተደርሷል። ከኢትዮጵያዊነትም ከኦሮሞነት ወርደው አካባቢያዊነት እና ደምና አጥን ቆጠራ ከዛም ብሄርና ማንነት መካካድንና መንሳትን የፖለቲካ መቀስቀሻ አድርገው የሚሄዱበት፣ 7 ሺ የኦሮሞ ወጣት ተገብሮ ነው ይሄ ለውጥ ያመጣናው እንዳልተባለ ዳግም 7ሺ ወጣቶችን የጨረሰውን ስብስብ ወደ ስልጣን ለመመለስ የገዛ
417 views05:09