Get Mystery Box with random crypto!

ዮሐንስ 13 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³⁴ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ፥ እንደ ወደድኋችሁ እናንተ ደግሞ | MARSIL TV WORLD WIDE

ዮሐንስ 13
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁴ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ፥ እንደ ወደድኋችሁ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ።
³⁵ እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ።
³⁶ ስምዖን ጴጥሮስም፦ ጌታ ሆይ፥ ወዴት ትሄዳለህ? አለው። ኢየሱስም፦ ወደምሄድበት አሁን ልትከተለኝ አትችልም፥ ነገር ግን በኋላ ትከተለኛለህ ብሎ መለሰለት።
³⁷ ጴጥሮስም፦ ጌታ ሆይ፥ አሁን ልከተልህ አለመቻሌ ስለ ምንድር ነው? ነፍሴን ስንኳ ስለ አንተ እሰጣለሁ አለው።
³⁸ ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰለት፦ ነፍስህን ስለ እኔ ትሰጣለህን? እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሦስት ጊዜ እስክትክደኝ ድረስ ዶሮ አይጮኽም።

@marsilchannel