Get Mystery Box with random crypto!

የኋላ ማርሽ ነቅለናል' የአዲስ አበባዋ አዲስ ኪዳን ካህናት ቤ/ክ ትናንት ከሰዓት የ2014 ዓም መ | MARSIL TV MEZMUR®✅

የኋላ ማርሽ ነቅለናል"
የአዲስ አበባዋ አዲስ ኪዳን ካህናት ቤ/ክ ትናንት ከሰዓት
የ2014 ዓም መልካም ወጣት ወደ ተለወጠ ህይወት
መክፈቻ ደማቅ በዓል አስተናግዳለች።
የፊታችን እሁድ በሐዋሳ ከተማ 1ኛ ዙር የሚጀምር ሲሆን
ከ25ሺ በላይ የተመዘገቡ ወጣቶች በ7 ዙር ይሰለጥናሉ።
መክፈል ለማይችሉ ወጣቶች ትናንት የነበረው ጉባኤ ድጋፍ
የሚሆን ገንዘብ አሰባስቧል።
በየ አመቱ ሲደንቃችሁ በየ ሶስት ወሩ 30ሺ ለማሰልጠን
ዕቅድ ተይዟል። የት? ካላችሁ በአዲስ አበባ።
ይሕ ብቻ ሳይሆን ኃላፊነቱ የጋራ እንደ መሆኑ ሁሉም
የመንፈሳዊ አገልጋዮች የሚያሰለጥኑበት እንደሚሆን ወደ
ፊት ይጠበቃል።
አምና 25ሺ ወጣቶች ወደ እግዚአብሔር መንግስት
መጨመራቸው የተነገረ ሲሆን፦
ቅዱሳን በዘንድሮው መልካም ወጣት ይህ ቁጥር በእጥፍ
እንዲጨምር እና ከተመዘገቡት መካከል 5ሺህ በላይ
ወጣቶች ወደ ነፍሳቸው እረኛ ወደ ጌታ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ
እንዲመጡ አጥብቃችሁ ፀልዩ ተብላችኋል።
ማን ነበር? የሚለውን መዘርዘር ይከብዳል። በአጭሩ ማን ቀረ
ይሻል ይሆን? ምስሉ ከስር ይናገራል።
ለማንኛውም እንዲ እንደ አካል በጋራ ስንደምቅ እንዴት
እንደሚያምርብን።
የነበረውን የአምልኮ መንፈስ እና በተወደዱ የእግዚአብሔር
ሰዎች የቀረቡ መልዕክቶች፣ ፀሎት እና ትንቢታዊ አዋጆችን
ከቪዲዮው ብትመለከቱ ታተርፋላችሁ።
ጠላት (ዲያቢሎስ) የፈለገበት ሄዶ መደፋት ይችላል።
ወንጌል፣ ፍቅር፣ አንድነት፣ መተሳሰብ ወዘተ. . . ወይ
ይቀጥላል፤ ወይ ደግሞ ይቀጥላል።
የመግቢያ ርዕሱ ከአገልጋይ ዮናታን አክሊሉ ንግግር የተወሰደ
ነው።
መልካም የ2014 መልካም ወጣት ወደ ተለወጠ ህይወት
አብይ ታደለ /ኪያ/
#share #share #share

@marsilchannel