Get Mystery Box with random crypto!

. ሀያላን አንድ #የመንፈስ አለም #ሚስጥር ልንገራችሁ… ━━━ | Maranatha tube

. ሀያላን አንድ #የመንፈስ አለም
#ሚስጥር ልንገራችሁ…
━━━━━⊱✿⊰━━━━━
በመንፈስ መሞላት እና ድንገተኛ ከባድ የእግዚአብሔር ሀይል ብሎም በፀሎት ስፍራችሁ ብቻ ሳይሆን በስራ ቦታችሁ፣በትምህርት ቤት፣በመኝታችሁ፣ትራንስፖርት ላይ፣መንገድ ላይ #Walk እያደረጋችሁ ሁሉ ሳይቀር በእንባ የምትሞሉበት የማያቋርጥ እግዚአብሔርን የመፈለግ ረሀብ በውስጣችሁ እንዲገባ ትፈልጋላችሁ?

ለጥያቄያችሁ መልስ ፍለጋ፣ከእጁ አንዳችን ነገር ለመቀበል፣ጎዶሎአችሁን ለመዘርዘር፣ለምሬት፣ከሌሎች ተሽሎ ለመገኘት፣አንዳች የሀይማኖት ስርአት ለመፈፀም ወዘተ… ብላችሁ ሳይሆን ማንነቱን ወዳችሁ ፊቱን ብቻ ተርባችሁ ልክ ለቀናት እህል ውሀ እንዳልቀመሰ እና እንደተራበ ሰው ሆናችሁ #በረሀብ እና በንፁህ ልብ ወደ ፀሎት ስፍራችሁ ግቡ

ሁሉ #Bonus ነው በመገኘቱ ውስጥ

ውዶቼ ገብታችሁ እዩት በህልውና ውስጥ ሁሉን ታገኛላችሁ ይገርማችኋል ሆኖም ግን ይቀልባችኋል ከመገኘቱ ውጪ አንዳች አያሰኛችሁም ምክንያቱም በእግዚአብሔር ክብር ፊት ልቆ ሊታይ የሚችል አንዳች ምድራዊ ሀይል የለምና!

“አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፤ ነፍሴ አንተን ተጠማች፥ ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች እንጨትና ውኃ በሌለበት በምድረ በዳ።”
— መዝሙር 63፥1

አባ አዎን ለኔ ግን ፊትህ ይሻለኛል ውዴ መገኘትህን ከእኔ አትውሰድብኝ!

ወይኔ አልገባችሁም ይሄን መልዕክት እንኳን በምን አይነት ህልውና ውስጥ ሆኜ እንደፃፍኩላችሁ! ህይወቴን ወደድኩት ካንተ የተነሳ መንፈስ ቅዱስ አወድሀለሁ!

ይሄን Text እያነበባችሁ በኢየሱስም በውስጣችሁ ረሀብ ገባ!

አገልጋይ መልካሙ ሙሉጌታ!

የክብሩ መገለጫ ሆናችሁ ማለፍ ለምትፈልጉ ብቻ
@HolyTubeEthiopia
@HolyTubeEthiopia‌‌