Get Mystery Box with random crypto!

የትላንት ጨዋታ የግል ምልከታ ጥሩ ጨዋታ አይተናል ዩናይትድ ከዚህ በፊት ሲጫወት ከነበረው | Manchester United Fans Video Channel

የትላንት ጨዋታ የግል ምልከታ

ጥሩ ጨዋታ አይተናል ዩናይትድ ከዚህ በፊት ሲጫወት ከነበረው ጨዋታ የተሻለ መረጋጋት አይተንበታል ከኦናና በሚነሱ ኳሶች Build up አርጎ በመውጣት የአርሰናል ተጨዋቾችን ለማስከፈት ሙከራ ሲያረግ አስተውለናል ሆኖም የአርሰናል ተጨዋቾች አስተውላቹ ከሆነ ኦናናን በአንድ ተጨዋች ማለትም በኒኪቲያ እና ኦዴጋርድ እየተቀያየሩ ነበር ኦናናን press ለማድረግ ሲሞክሩ የነበረው አርሰናል ትልቁን ስራ መሀል ሜዳ ላይ ነበር ሲሰሩ የነበሩት ኳስ ከኦናና በሚጀመርበት ጊዜ መሀሉን በመዝጋት Build up ውጤታማ እንዳይሆን አርገውታል በዚም የተነሳ ኳስ አስጀምረን መሀል ሜዳ ላይ ነበር ምንቀማው ይሄ መሀል ሜዳ ላይ በ Tacticu ረገድ መበለጣችንን ነው ሚያሳየው አጥቂዎቻችን ጋር ኳስ በቶሎ አይደርስም ነበር ምናልባት መሀል ሜዳው ላይ የተቀናጀ እና Tactical Arrangement ብናረግ ኖሮ Effective ያደርገን ነበር.....

ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ እና ሊንድሎፍ ከወጡ በኃላ ሙሉ በሙሉ የዩናይትድ ጨዋታ ከኦናና ረጀም ኳስ ወደ አጥቂዎቻችን በመላክ ሲቀየር ተመልክተናል ምክንያቱም ማጓየርን ይዘን Build up እማይታሰብ ስለሆነ ባለቀ ሰዐት በተጨዋቾቻን Concentration ችግር እና አንድአንድ የዳኝነት ስህተቶች ታክለው ተሸንፈናል....ግን ደሞ ብዙ ተስፋ ሰጪ የሆኑ ነገሮችን አይተናል ዩናይትድ ከበረኛ ኳስን አስጀምሮ ሲጫወት አይተን አናውቅም የትላንቱ ውጤታማ ባይሆንለትም ግን ደሞ በጊዜ ሂደት ያሉት ችግሮች እና Tactical መዋቅሮች ታክለው ከጊዜ ወደጊዜ የተሻለና እርስ በእርስ የተጣጣመ ቡድን ማናይበት ምክንያት ምንድነው ?.....ትዕግስተኛ እና Logical ለመሆን እንሞክር...ሲሸነፍ እየጠበቀን ትችት ሲያሸንፍ ደሞ ሌላ ሰው አንሁን ከስሜታዊነት ወጥተን ምክንያታዊ ለመሆን እንሞክር እንደ ትክክለኛ ኳስ ተመልካች አቋም ይኑረን ....Just a matter of time

Møunt ነበርኩ አመሰግናለው .....

@Manchester_Unitedfansgoal