Get Mystery Box with random crypto!

ክፍል አንድን በሚገባ ካወቅን የፊደሎቹ ስምና ቅርፅ ቢለያይም የሚሰጡን አገልግሎት ተመሳሳይ መሆኑን | ቁርአንን በቀላሉ ማንበብ እንድንችል አረብኛ ፊደሎችን ከእንግሊዝኛና አማርኛ ፊደሎችጋር ያላቸውን ዝምድና/ተመሳሳይነት እንወቅ

ክፍል አንድን በሚገባ ካወቅን
የፊደሎቹ ስምና ቅርፅ ቢለያይም
የሚሰጡን አገልግሎት ተመሳሳይ
መሆኑን እንረዳለን

የሆነ ነገር ለመፃፍ ስንፈልግም
በአረብኛ ከፈለግን በእንግሊዝኛ
ከፈለግን በአማርኛ ፊደል መፃፍ
የኛ ምርጫ ነው የሚሆነው

አንድ መሆናቸውን ለማረጋገጥ
ለምሳሌ ሙሀመድ የሚለውን
ስም በሶስቱም እንፃፈው

በአማርኛ ሙሀመድ
በእንግሊዝኛ Muhammed
በአረብኛ محمد

አንድን ሰው ከሶስቱ አንዱን ብቻ
መርጦ እንዲያነብልን ብናደርግና
የትኛውን መርጦ እንዳነበበም
ቢጠይቀን ራሱ ያነበበው ሰው
ካልነገረን በስተቀር ልናውቅ
አንቺልም ምክንያቱም ፊደሎቹ
ለንባብ ሲቀርቡ በመልክ እንጅ
በድምፅ ተመሳሳይ ናቸው