Get Mystery Box with random crypto!

ማስታወሻ የዛሬዋ ምሽት የለይለተል ጁምዓ እና የረመዳን 23ተኛ ለሊት ነው:: አንዳንድ ፉቅሃዎች | MAJIF የሙስሊም ወጣቶች ማህበር

ማስታወሻ

የዛሬዋ ምሽት የለይለተል ጁምዓ እና የረመዳን 23ተኛ ለሊት ነው:: አንዳንድ ፉቅሃዎች የሁለቱ ቀናት መገጣጠም ለሊቱ የለይለቱል ቀድር ለሊት ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል

ኢብኑ ረጀብ ላቲፍ አል ማሩፍ ውስጥ ከኢብኑ ሁባይራህ የሚከተለውን ዘገባ አስፍረዋል:-

* የጁምዓ ምሽት ከረመዳን የመጨረሻዎቹ የዊተር ቀናቶች ጋር የሚገጥም ከሆነ ከሌሎቹ የበለጠ ለሊቱ ለይለቱል ቀድር ሊሆን ይችላል" ይላሉ

* ኢብኑ ተይሚያህም እንዲህ ይላሉ:-

"የጁምዓ ምሽት በመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ውስጥ ከአንድ የዊትር ሌሊቶች ጋር የሚገጥም ከሆነ ያኔ የበለጠ ለሊቱ የለይለቱል ቀድር ሊሆን ይችላል"

* የአለማቱ ጌታችን አላህ ሆይ የለይለቱል ቀድርን ደርሰን ከተቀበሉት እና ከተጠቀሙት መካከል አድርገን

ዶ / ር ሰይፍ አል ሱዋይዲ